Get Mystery Box with random crypto!

ዘሪሁን ገሠሠ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
የሰርጥ አድራሻ: @zerihunkocha
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.77K
የሰርጥ መግለጫ

በመረጃ እንቀራረብ! በመረጃ እንተሳሰር!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-03 19:57:00
እነእስታሊን ግን ''ሼም'' የሚባለውን ነገር የሚያውቁት መቼ ይሆን ?

ህወሓት ሰሜን እዝን በጨፈጨፈና በሀገሩ ላይ ክህደት በፈፀመ ማግስት ፣ ' ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ'  ውስጥ ሆኖ ኤርትራን ''ኧረ ተበላሁ ድረሽልኝ!'' ያለው እናንተ ''መሽረፈት' የምትሉት ፣ አብይ አህመድ ነበር።

ያኔ እነስታሊን ገ/ስላሴ ፣ በአልጀርሱ ስምምነት መሠረት ተወስኖ ነገርግን በኢትዮጵያ ስር የቆዩ የተወሰኑ የባድመ ወረዳ ቀበሌዎችን '' አብይ የትግራይን ህዝብ ለማስጨፍጨፍ በእጅ መንሻነት  ሀገሩን ቆርሶ ለኤርትራ የሰጠ ባንዳ ነው! >> ብለው እሪሪሪ... ሲሉ ፣ የብልፅግና ሰዎች ደግሞ '' እኛ ለሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት ስንል ፣ ወያኔ በአለምአቀፍ ፍርድ ቤት ተወስኖበት ያልፈፀመውን ነው ተፈፃሚ ያደረግነው እንጂ አዲስ መሬት አልሰጠንም! >> የሚል ሙግት ያቀርቡ ነበር።

እንግዲህ ዛሬ '' ደፈረን ፣ አስደፈረን ፣ ጨፈጨፈን አስጨፈጨፈን ፣ ...'' ስትሉት የነበረው አብይ አህመድ ፣ ''አሰብ ወደብን ላስመልስ...!'' በሚል የድጋፍ መሠብሰቢያ ካርድ ፣ የምእራባውያኑ የውክልና ጦርነት አስፈፃሚ ሆኖ እልቂት ደግሶ ሲመጣ ፤ እናንተ የጥላቻ ለሀጫችሁን የምታዝረበርቡበት የአማራ ልሂቅ  ፣   << ገንጣይ አስገንጣዩ ወያኔ  የአሰብን ጉዳይ ጨምሮ የኤርትራን ሉአላዊነት ያወጀው በአለም አደባባይ ነው ! ስለዚህ የአንድን ሉአላዊ ሀገር ክብር ከመዳፈር ይልቅ ፣ ከኤርትራ ጋር ወደቡንም በፍቅር እንጠቀማለን ፣ ወጀቡንም አብረን እናልፋለን! >> ቢል ስህተቱ ምንድን ነው?

ይሄን ማለቱስ ከቀደመ አቋሙ ጋር በምን ይቃረናል? ገንጣይ አስገንጣዩን ትህነግስ በምን መልኩ ከተወቃሽነት ይታደገዋል ? በሁለት አመት ውስጥ የእናንተ የማይታረቅ ተቃርኖስ የሚታያችሁ መቼ ነው!

ግዴላችሁም ሼም የሚባለውን ነገር አልፎ አልፎ እንኳ እወቁት!
1.2K views16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 17:44:43
3.5K views14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 17:44:39 በ2023 በአለም ላይ ለጎብኝዎች በፍጹም ከማይመከሩና እጅግ አደገኛ ከተባሉ 10 ሀገራት ውስጥ ኢትዮጵያ አንደኛዋ መሆኗን ያውቃሉን ?

በየአመቱ የሀገራትን የሰላምና ደህንነት ሁኔታ ተገምግሞ ደረጃ በሚሰጥበት The Global Peace Index እ.ኤ.አ በ2023 በተቀመጡ መመዘኛ መስፈርቶች መሠረት የ163 ሀገራትን ደረጃ ተለይቶ ይፋ ተደርጓል።

በዚህ የደረጃ ሠንጠረዥ መሠረት ከግርጌ ያሉት አስር ሀገራት << በአለም ላይ ለጉዞና ለጎብኚዎች ፍፁም የማይመከሩ አደገኛ ሀገራት >> ተብለው ተቀምጠዋል። በዚህ መሠረት ሀገራችን ኢትዮጵያ ከ163 ሀገራት በ2.80 የGPI ነጥብ 151ኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥና ከአፍሪካ 8ተኛ ተራ ቁጥር ላይ ሰፍራ በዝርዝሩ ውስጥ የተካተተች ሀገር ሆናለች።

ከዚህ ቀደም የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት በበኩሉ ፤ << ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ደረጃ-3/level 3 የጉዞ አማራጭ ሀገር ነች>> ሲል መመደቡ የሚታወስ ነው። ይህ ማለት << የሀገሪቱ ሁኔታ እስከሚስተካከል ድረስ ፍፁም ለጉዞና ለጉብኝት አትመከርም! >> እንደማለት ነው።

በGPI የደረጃ ሰንጠረዥ ላይ ፣ በሀገሪቱ ያሉ የሽብርና የእገታ ወንጀሎች መስፋፋት ፣ የእርስበርስ ግጭቶች ፣ ያልተረጋጋና ረፍት አልባ ህዝብ መኖሩ ፣ የወንጀል ድርጊቶች እየተበራከተ መምጣት ፣ በጎረቤት ሀገራት ድንበሮች አካባቢ ያሉ የደህንነት ስጋቶችና በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ችግሮች በቀጠና ተለይተው በዝርዝር ተቀምጠዋል።

በአለም ላይ ለጎብኚዎች መረጃ የሚሰጡ ድህረ-ገፆችና ሌሎች ሚዲያዎች ፣ አስጎብኚ ድርጅቶች ፣ የሀገራት ኤምባሲዎች ወዘተረፈ <<...According to GPI ranking, Ethiopia is considered one of the most dangerous countries in Africa. >> እያሉ ሲያስተጋቡ መመልከት ልብን ቢያሳምምም ፣ እውነታው ግን ይኸው ነው!

በሁለንተናዊ መልኩ ፣ ሁለንተናዊ በጎ ገፅታዋንና ክብሯን እያጣች ያለች ሀገር-ኢትዮጵያ!

Fact check links

https://travellersworldwide.com/most-dangerous-countries-in-africa/

https://reliefweb.int/report/world/global-peace-index-2023

https://www.gfmag.com/global-data/non-economic-data/most-peaceful-countries
3.5K viewsedited  14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 11:50:27 አስቸኳይ ልዩ መልዕክት

ሜክሲኮ ገነት ሆቴል አጠገብ የሚገኘው የፌዴራል ጊቢ ውስጥ ከተለያየ ቦታ የታፈኑ በርካታ አማራዎች አሉ። እነዚህ ታፋኞች ወራት ቢያስቆጥሩም ዘመድ አዝማድ ያሉበትን አያውቅም ፣ ፍርድ ቤትም አልቀረቡም። በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ የሚገኙ በመሆኑ ጉዳዩን ህዝብ እንዲያውቀው ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና የሚመለከታቸው አካላትም እንዲከታተሉት ተማፅኖ አቅርበዋል!
4.2K views08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 18:36:56
4.5K views15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 18:36:45 ኢትዮጵያ በ2023 በከፍተኛ ሁኔታ እየፈራረሱ ካሉ 12 የአለም ደካማ ሀገራት (fragile States) ተርታ ተመድባለች!

በየአመቱ ደካማ/የወደቀ (failed/fragile) መንግስት ያላቸውን ሀገራት መዝኖ በደረጃ የሚያስቀምጠው Fund for peace /FFP/ የተሰኘው አለምአቀፍ ተቋም እኤአ በ2023 አጠቃላይ የአለም ሀገራትን በተለያዩ መመዘኛዎች መዝኖ ደረጃቸውን አስቀምጧል ። በዚህም መሠረት እጅግ በጣም ከፍተኛ እና በጣም ከፍተኛ የወደቀና ደካማ መንግስት ካላቸው ሀገራት ተርታ ኢትዮጵያ ተካታለች።

እጅግ በጣም አስከፊ የመፍረስ አደጋ ውስጥ ከተካተቱት 12ቱ ሀገራት መካከል ወደ7 የሚሆኑት የአፍሪካ ሀገራት ሲሆኑ ከዚህም ውስጥ ኢትዮጵያ ፣ ደቡብ ሱዳን ፣ ሱዳንና ሶማሊያ የምስራቅ ሀፍሪካ ሀገራቶች ናቸው።

ለግዛት መፈራረስ/ State Fragility ዋና ዋና ምክንያቶች ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል፦ የአስተዳደር ድክመት/Weak governance ፤ የአስተዳደር አቅም ውስንነት (limited administrative capacity) ፤ ስር የሰደዱ ሰብአዊ ቀውሶች (chronic humanitarian crises) የማያቋርጡ ማኅበራዊ ውጥረቶች ( persistent social tensions) እና ብዙ ጊዜ ሁከት ወይም የትጥቅ ግጭት እና የእርስ በርስ ጦርነት (violence or the legacy of armed conflict and civil war) ከብዙ በጥቂቱ የሚገለፁ ናቸው።

የግዛት መፈራረስ/ State Fragility ምን ማለት ነው?

እንደ Fund for peace /FFP/ አገላለጽ ደካማ የሆኑና በመፈራረስ ላይ ያሉ ሀገራት በርካታ መገለጫ ባህሪያት ያሏቸውና በተለያዩ መንገዶች ሊገለፁ የሚችሉ ቢሆንም በጣም ከተለመዱት እየፈራረሱ ያሉ ሀገራት መገለጫ ባህሪያት መካከል አንዳንዶቹ የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ።

-የግዛቱን አካላዊ ቁጥጥር ማጣት ወይም በሕጋዊው የኃይል አጠቃቀም ላይ ያለው ጠቅላይነት / The loss of physical control of its territory or a monopoly on the legitimate use of force

-የጋራ ውሳኔዎችን ለመወሰን የህጋዊ ስልጣን መሸርሸር/ The erosion of legitimate authority to make collective decisions

-መሠረታዊ የህዝብ አገልግሎቶችን ለማቅረብ አለመቻል/ An inability to provide reasonable public services

-እንደ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሙሉ አባል ከሌሎች ሀገራት ጋር ጤናማና የተሳካ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማድረግ አለመቻል/ The inability to interact with other states as a full member of the international community. ከብዙ በጥቂቱ የቀረቡ ማሳያዎች መሆናቸውን ይገልፃል።

Fund for peace /FFP/ የሀገራቱን ደረጃ ለመለየት በመመዘኛነት ከተጠቀማቸው 12 መለኪያ መስፈርቶች መካከል ፦ መጠነ ሰፊ የሙስና ወንጀልና የወንጀል ባህሪ ፤ የዜጎችን ሁለንተናዊ ድጋፍ ማጣትና ግብር መሰብሰብ አለመቻል ፣ የዜጎች ያለፍላጎትና በአስገዳጅ የጥቃት ሁኔታ መፈናቀል ፣ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ውድቀት፣ በቡድን ላይ የተመሰረተ ኢ-ፍትሀዊነት ፣ ተቋማዊ ስደት/መፈናቀል ወይም መድልዎ ፣ ከባድ የስነ-ሕዝብ ጫናዎች ፣ አእምሯዊ ፍልሰት (brain drain) እና በተለያዩ ግዛቶች በተለያዩ ጊዜያት የሚፈፀሙ አሰቃቂና በጭካኔ የተሞሉ ወንጀሎችና ግጭቶች መበራከት የመሳሰሉት ይገኙበታል።

Fund for peace /FFP/ የልየታ ነጥብ መሠረት ከ100 ነጥብ በላይ ያገኙና እጅግ በጣም ከፍተኛና በጣም ከፍተኛ በሚል ደረጃ የተቀመጡት 12ቱ ሀገራት ፦ ሶማሊያ ፣ የመን ፣ ደቡብ ሱዳን ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፣ ሶሪያ ፣ አፍጋኒስታን ፣ ሱዳን ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ፣ ቻድ ፣ ሀይቲ ፣ ኢትዮጵያ እና ማይናማር ናቸው።
4.6K views15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 16:02:29
ሽመልስ አብዲሳ << ሞቼ ነው ቆሜ የሚፈታው? አይደለም መፈታት ዋስትናም አያገኝም! >> ብሎ የፎከረባቸው አዛውንቱ ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ ፥ ዛሬም ለ3ተኛ ቀን ረዥም ሰአት የፈጀውን የመከላከያ ምስክር ሲያሰሙ ውለዋል!

በዛሬው ችሎት ፦

የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ም/ዳይሬክተር - ረ/ፕ/ር አበባው አያሌው
የትምህርት ሚኒስትር - ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ
የታሪክ ምሁሩ - ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማሪያም

በችሎት ቀርበው የምስክርነት ቃል የሰጡ ሲሆን ፣ ከዚህ ቀደም በነበሩት ሁለት ችሎቶች የቀድሞ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ፣ ጋዜጠኛ መስከረም አበራ ፥ ከሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዶ/ር ዳንኤል በቀለን ጨምሮ ሌሎች በርካቶች ቀርበው የመከላከያ ምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል!

ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ በአገዛዙ ጥርስ የተነከሰባቸውና የሀሳብ ነፃነት መብታቸውን ተጠቅመው በእውቀትና በሙያ ያገኙትን እውነታ በሚዲያ በማጋራታቸው ብሎም የስርአቱን አስከፊነትና ህገወጥ ተግባራት በይፋ በሀሳብ በመሞገታቸው ፣ በአንባገነኖቹ ይህ እንደወንጀልና አሸባሪነት ተቆጥሮ ፣ በርካታ የክስ ዶሴ ተከፍቶባቸው በወህኒ ቤት እየተሰቃዩ እንደሚገኙ የሚታወስ ነው!

ፍትህ ለጋዜጠኛ ታዲዎስ ታንቱና በአንባገነኖች ወህኒ እየማቀቁ ለሚገኙ በቁጥር እጅግ በርካታ ለሆኑት የህሊና እስረኞች!
5.2K viewsedited  13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-29 21:33:29
ለሚረዳው ይህ መረጃ ብቻውን ብዙ ይናገራል!

<< የፕሬዝደንት ጆ ባይደን አስተዳደር ኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት ከሚጥሱ አገራት ዝርዝር ውስጥ ሊያወጣ መሆኑን ፎርይን ፖሊሲ ዘግቧል፡፡ በአሜሪካ ግምጃ ቤት ውስጥ ያሉ ምንጮቹንና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን የጠቀሰው ዘገባው ይህ በቅርቡ ሊሆን እንደሚችልና ለኮንግረስ አባላትም እንዲያውቁት መደረጉን አስረድቷል፡፡ ኢትዮጵያ ከዚህ ዝርዝር ውስጥ ከወጣች ከአሜሪካ የምታገኘውና የተቋረጠው የኢኮኖሚ እርዳታ እንደሚቀጥልም አስታውቋል፡፡ ይህ የአሜሪካ መንግስት ውሳኔ ሂውማን ራይትስ ዎችና ሌሎችም የመብት ተሟጋቾች ከሚያወጡት ሪፖርትና መግለጫ ተቃራኒ እንደሆነም ጨምሮ ዘግቧል፡፡ >> ዘ-ሀበሻ

አሜሪካ የምትፈልገው ''ቅጥረኛ ተዋጊና ጉዳይ አስፈፃሚ '' እንድትሆናት ብቻ ነው!' የአንተ መጨፍጨፍና የሚደርስብህን ገደብ የለሽ ሰቆቃ የምታስተጋባው እጅ ለመጠምዘዝ ያህልና ለፍጆታ እስከዋለ ድረስ ነው!
5.4K views18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-29 19:13:02
4.9K views16:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-29 19:12:57 የዝሆኖቹ የቀይ ባህር ፖለቲካዊ ትርምስና የቅጥረኛ ተዋጊዎቹ ጉዳይ!

ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ፣ አብይና ትህነግ ተፋቅረው ፥ አብይ ''በነፍሴ ድረሺልኝ!'' ያላትን ኤርትራ ሊወጉ ይችላሉ! የውክልና ጦርነቱ ምስራቅ አፍሪካን ወደትርምስ ቀጠና ይወስዳታል ብዬ ነበር!

''አማራውን አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ባንዲራ እያሳየን የአሰብ ወደብን ለማስመለስ ነው ካልነው ከጎናችን እናሰልፈዋለን!'' የሚል አደገኛ የአፍ ወለምታ በመድረክ ተነግሮ እንደነበርም ጭምር ምንጮቼን ጠቅሼ አጋርቼ ነበር።

ይኸው አሁን በሁለቱም ጎራ የውክልና ጦርነት ዝግጅቱ መጀመሩን እየተመለከትን ነው። ኤርትራ ድንበሯን ጠርቅማ ከዘጋች ወራት ተቆጥረዋል። የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተወካዮች ወከባና ክትትል በዝቶብናል እያሉ እዬዬውን አቅልጠውታል። ወዲህ ''ለቀይ ባህር በቀይ ባህር እንሞታለን!'' የምትል አስቂኝ ፕሮፓጋንዳ ብቅ ብቅ ማለት ጀምራለች። የሸለመጥማጡ አብይ ሁኔታ ያላማራት ኤርትራ ከህወሓት ጋር በተደረገው ጦርነት በነበራት አስተዋፅኦና በስምምነቷ መሠረት ለተኮሰችው እያንዳንዷ ጥይት ፣ ላወጣችው ሎጅስቲክና ደመወዝ ፣ ለከፈለችው ህይወት ሁሉ ሂሳብ አስልታ የጠየቀችው ገና የትህነግ ዳግም ወረራ ሊጀማምር አካባቢ ነበር። አብይ ይህን መክፈል ባለመቻሉ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ድብቅ ድርድር ተደርጎም ሳይቋጭ በነበረበት መክረሙ አይዘነጋም። ኤርትራ ከሳምንት በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከትኬት ሽያጭ የሰበሰበውን 2 ሚሊየን ዶላር ሳይቀር እንዳይንቀሳቀስ ያገደችው ''ይህ ሁሉ እዳ ሳይከፈለኝ!'' በማለት ይመስላል።

እጅ ጠምዛዦቹ ምዕራባውያን ከሳምንታት በፊት የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ፣ የምዕራባውያኑ ቁጥር አንድ ባላንጣ በሆኑት ሩሲያና ቻይና ያደረጉትን ይፋዊ ጉብኝት ተከትሎ ፣ የምስራቅ አፍሪካ ቅጥረኛ ተዋጊዎቻቸው (አብይና ትህነግን ጨምሮ ሌሎቹም) ይቺን ቀንድ ላይ ያለች ስትራቴጂክ ሀገር በቶሎ እንዳልነበረች አድርገው እንዲያጠፏት የተጣደፉም ይመስላል።

የቀይ ባህር ፖለቲካ ምዕራባውያኑንና ተቃራኒዎቻቸውን ለዘመናት የሚያራኩት ወሳኝ ጉዳይ መሆኑ ግልፅ ነው። ሩሳያና ቻይናን ጨምሮ የምዕራባውያኑ ባላንጣ ሀገራት በቀይ ባህር ፖለቲካው ውስጥ ድርሻቸውና የበላይነታቸው እየጎላ የመጣው በዚች በኢሳያስ ሀገር ሳቢያ እንደሆነ ያምናሉ። ስለዚህ ይቺን ሀገር ድራሿን ካላጠፉ የሚተኙ አይመስልም።

አብይ ጀነራሎቹን በሙሉ ሰብስቦ እየዶለተ ነው። በኤርትራ በኩል ያለው ወታደራዊ ዝግጅትም ገዘፍ ያለና በሎጂስቲክ የተጠናከረ መሆኑን ምንጮች እየገለፁ ይገኛሉ።

በዚህ መሀል የምዕራባውያኑ ቅጥረኛ ተዋጊ ኢትዮጵያውያንን በተለይም አዲስአበባ ላይ መኖር የተሳነውን አማራ ለመቀስቀስ '' ለቀይ ባህር በቀይ ባህር እንሙት!'' የሚል ጭዌ መሆኑ ያስቃል።

ለሁሉም ጊዜ መልስ አለው! ኢመቻችሁ!
5.3K viewsedited  16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ