Get Mystery Box with random crypto!

እኔ ሙስሊም ነኝ ፤ ሙስሊምነቴ ግን ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ሀቅን ከመናገር አያ | ዘሪሁን ገሠሠ

እኔ ሙስሊም ነኝ ፤ ሙስሊምነቴ ግን ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ሀቅን ከመናገር አያግደኝም!

// በጋዜጠኛ - #አብዱራዛቅ_መሐመድ//

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለሀገር የዋለችውን ውለታ ቆጥረን አንጨርሰውም። ኢትዮጵያ እንደሀገር አንድ ሆና እንድትቀጥል ቤተክርስቲያኒቷ ከፍተኛውን ሚና ተጫውታለች። ትልቅ መስዋእትነትም ከፍላለች፤ እየከፈለችም ትገኛለች።

ለቤተክርስቲያኒቷ ውለታዋን መመለስ ባይቻል ማዋከቡ እንደሀገር ዋጋ እንዳያስከፍለን እሰጋለሁ። ቤተክርስቲያኒቷን መንካት ማለት ሀገርን መንካት መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል።

ኢትዮጵያን ለማዳከም አለፍ ሲልም ለማፍረስ የሚፈልጉ የውስጥና የውጭ ኃይሎች ቀድመው ቤተክርስቲያኒቷን ካላፈራረሱ ውጥናቸው እውን እንደማይሆን ያውቃሉ። ታሪክም የሚነግረን አሁንም የምናየው ይህንኑ ነው።

አሁን የተፈጠረው ችግር የቱንም ያህል ከባድ ቢሆን አባቶች ዘንድ መፍትሄ አይጠፋም። ከታሪክ እንደተረዳነው ከዚህ በፊትም ቤተክርስቲያኒቷ ከባባድ ፈተናዎችን አስተናግዳለች። ሆኖም ግን በቅዱሳን አባቶችና በአማኙ ትእግስትና ጥረት ታልፈዋል።

አሁንም የተፈጠረው ችግር ለአባቶችና ለኃይማኖቱ ተከታዮች እንተውላቸው። ችግሩ በፖለቲካዊ ሳይሆን በቤተክርስቲያኒቷ አስተዳደራዊና ቀኖናዊ አካሄዶች እንደሚፈታ ተስፋ አደርጋለሁ።

የሌላ እምነት ተከታዮች ግን በማያገባን እየገባን የምንፈተፍተው ነገር ችግሩን የበለጠ ያባብሰዋል እንጂ መፍትሄ አያመጣም። አማኞቹ እርዳታችን በፈለጉ ሰዓት አለሁ ማለት ኢትዮጵያዊ ባሕላችን መሆኑ ሳንዘነጋ ማለት ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶችና ምእመናን ሀቀኛ ስለመሆናቸው ከዛሬ 1,400 ዓመታት በፊት የአላህ (ሱ.ወ) ቃል በሆነው ቅዱስ ቁርዓን እንዲህ ተመስክሮላቸዋል፦

" ... እነዚያ እኛ ነሳራዎች (ክርስቲያኖች) ነን ያሉት ወደ ሙዕሚኖች (ሙስሊሞች) የቀረቡና የተወደዱ ሆነው በርግጥ ታገኛቸዋለህ። ምክንያቱም በውስጣቸው የተለያዩ ቄሶችና መነኮሳት ስላሉና እነርሱም የማይኮሩና ሀቅ በመጣ ጊዜ የሚቀበሉ በመሆናቸው ነው” (ቅዱስ ቁርዓን ምእራፍ 5 ቁጥር 82)/(ሱረቱል ማኢዳሕ፥82)

#ሼር