የአንተን በኑሮ ውድነት መጠበስና ብስቁልና ካልደረሰባቸው እንዴት ሊረዱልህ ይችላሉ?
እንዳይደርስባቸው ደግሞ ከዘረፋና ምዝበራው ባሻገር በዚህ መልኩ ህግ አውጥተው ራሳቸውን ይታደጋሉ፡፡
☞ በአዲስአበባ ለተሾሙ በየደረጃው ያሉ አመራሮች ከተማ አስተዳደሩ ቤት ያመቻቻል!
ከመደበኛ ደመወዛቸው ውጪ የሚከፈል የኃላፊነት አበልን በተመለከተ ፦
☞ ለከንቲባውና ለምክር ቤት አፈ-ጉባኤ - 18 ሺህ ብር
☞ ለም/ከንቲባውና በምክትል ማዕረግ ለተሾሙ አመራሮች - 17 ሺህ ብር
☞ ለከተማ አስተዳደሩ ካቢኔዎችና በቢሮ ሀላፊነት ደረጃ ለተሾሙ - 16 ሺህ ብር
☞ በም/ኃላፊዎች ፥ ኮሚሽነሮች ወዘተርፈ - 15ሺህ ብር
☞ ፅ/ቤት ኃላፊዎች ፥ የወረዳ ስራ አስፈፃሚዎች ፣ የኮሌጅ ዲኖች ፥ ወዘተርፈ - 14 ሺህ ብር
☞ የወረዳ ም/ኃላፊዎችና መሠሎች - 13ሺህ ብር
☞ የወረዳ ካቢኔ አባላትና በዚያ ደረጃ ለተሾሙ - 12ሺህ ብር ይከፈላቸዋል፡፡
ይቺን አሰራር ክልሎችና በተዋረድ ያሉት መንግስታዊ መዋቅሮችም እንደአዲስአበባ ራሳቸው ህግ አውጥተው በማፅደቅ ሲገለገሉ የሚያሳይ መረጃ ባላገኝም ፥ በግልፅም በውስጥም እንደሚሰሩባት የሚታመን ነው፡፡
ኢትዮጵያ መሪዎቿና ሰፊው ህዝቧ የተራራቁት በዚህ መልኩ ነው! ሠፊው ህዝብ አክርማና ስንደዶ አዋጥቶ የሰፋትን ኢትዮጵያ የተባለች ሞሰብ ፥ የሚመገቡባት ፖለቲከኞች ሲሆኑ የበይ ተመልካች የሆነውና የሚደክምላት ደግሞ ሰፊው ህዝብ ብቻ ነው!