Get Mystery Box with random crypto!

ቻይና በኦሮሚያ የዜጋዋን ግድያ ተከትሎ ለዜጎቿ ማስጠንቀቂያ አወጣች! //BBC// አንድ ቻይናዊ | ዘሪሁን ገሠሠ

ቻይና በኦሮሚያ የዜጋዋን ግድያ ተከትሎ ለዜጎቿ ማስጠንቀቂያ አወጣች! //BBC//

አንድ ቻይናዊ በኦሮሚያ ክልል ገብረ ጉራቻ ከተማ ከተገደለ በኋላ ቻይና በክልሉ ለሚንቀሳቀሱ ዜጎቿ ማስጠንቀቂያ ሰጠች።

ኤአፍፒ በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲን ጠቅሶ እንደዘገበው ሰኞ ጥር 22/2015 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ በሰሜን አቅጣጫ ገብረ ጉራቻ ከተማ 9 የቻይና ዜጎች በታጣቂ ቡድኖች ተኩስ ተከፍቶባቸው ነበር።

ተኩስ ከተከፈተባቸው ቻይናውያን መካከል አንዱ ሕይወቱ ማለፉን ሮይተርስ እና ኤኤፍፒ የዜና ወኪሎች በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲን ዋቢ አድርገው ዘግበዋል።

ኤምባሲው የዜጋውን መገደል ይፋ ባደረገበት መግለጫው፤ ጥቃቱን ያደረሰው ታጣቂ ቡድን ማን እንደሆነ እንዲሁም የጥቃቱ ዒላማ የሆኑት ቻይናውያን ማንነትንም አልገለፀም።

የቻይኛ ኤምባሲ መግለጫ አንድ ቻይናዊ መገደሉን ከመጥቀስ ውጪ፣ በሌሎች ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ ያለው ነገር የለም።

ከአዲስ አበባ 163 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኘው ከተማ በቻይናውያኑ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ኤምባሲው ባወጣው የጉዞ ማስጠንቀቂያ ላይ፤ “ከፍተኛ የአደጋ ስጋት ባለበት አካባቢ ከሆናችሁ፤ በአስቸኳይ ደኅንነቱ ወደ ተጠበቀ አካባቢ መውጣት አለባችሁ” ብሏል።

ኤምባሲው በኦሮሚያ ክልል እና በአጎራባች ክልሎች በጦር መሳሪያ የታገዘ ጥቃት፣ አፈና እና ዘረፋ የተስፋፋ ነው ብሏል።

ዘገባው ፦ የቢቢሲ ነው!