Get Mystery Box with random crypto!

ፅንፈኛ የጥላቻና የተቃርኖ ፖለቲከኞቹ - ኢትዮጵያን ወደፍርስራሽነት እየቀየሯት ነው! > ነ | ዘሪሁን ገሠሠ

ፅንፈኛ የጥላቻና የተቃርኖ ፖለቲከኞቹ - ኢትዮጵያን ወደፍርስራሽነት እየቀየሯት ነው!

<< ... ኢትዮጵያን ሳያፈርስ አይወርድም! >>

ነፍሳቸውን ይማርና ፥ ከአመታት በፊት እጅግ የማከብራቸው የቀድሞው የኢፌዴሬ ፕሬዝደንት የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጋር ፥ የታሪክ አጋጣሚ በአንድ የትግል መስመር አገናኝቶን ፥ ስለኢትዮጵያ የወቅቱና መፃኢ የፖለቲካ ሁኔታ በልምዳቸውና በትምህርት ካካበቱት እውቀት ብሎም ከግለ ታሪካቸው ጋር እያሰናሰኑ ፥ በርካታ ቁምነገር ያካፈሉብኝና የመከሩብኝ ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር፡፡

ከእርሳቸውም ጋር በነበረኝ ረዘም ያለ እድሜ ጠገብ የእውቀት ተሞክሮ የመካፈል አጋጣሚ ፥ ያካፈሉኝን ወሳኝ ቁምነገሮች መለስ ብዬ ሳሰላስላቸው ፥ በተለይም " ትህነግና ኦነግ የጥላቻና የሀሰት ትርክት እንደጡጦ እያጠቡ ያሳደጉት ይህ የኦሮሞ ትውልድ ፥ ፖለቲከኞቹ በጊዜ ወደሰዋዊና እንደሀገር ለመቀጠል ወደሚያስችል አስተሳሰብ ተመልሰው ካልገሩት በስተቀር ፥ ወደፊት ኢትዮጵያን በስቃይና በሰቆቃ ውስጥ እንኳ ሆናም እንደሀገር መቀጠል የማትችልበትን አውድ የሚፈጥር የፖለቲካ ኃይል እንደሚሆን " በብዙ አስረጂዎች የተደገፈ ትንቢታቸውንና መረዳታቸውን አካፍለውኝ ነበር፡፡

ዶ/ር ነጋሱ ጊዳዳ - " ዳንዲ - የነጋሶ መንገድ " በተሰኘው መፅሀፋቸው ፥ ዛሬ የጥላቻ ነጋዴዎች ፥ የሀገር መሀንዲሱ ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ላይ " የኦሮሞን ጡት ፣ ብልትና ፣ እጅ ቆርጧል! >> የሚል ሀሰተኛ ትርክት ፈጥረው ፥ ለዚህም "አኖሌ" የተሰኘ የጥላቻ ሀውልት አቁመው ፥ በ20ኛው ክ/ዘመን ህዝባቸውን በጥላቻ ትርክት አስክረው ፥ "ዳውን ዳውን ምኒሊክ" እያስባሉ ከሙታን ጋር በሚሰሩት የግብግብ ፖለቲካ ንፁሀንን ለሚፈጁ ፥ ዛሬአችንን የሚያጨልሙት ፥ ፅንፈኛ የኦሮሞ የፖለቲካ ቡድኖች ፥ " …ምኒሊክ ኦሮሚያ አልዘመተም፡፡ ጡት ስለመቁረጡም አንዳች የፖለቲካ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል የለም!" ሲሉ "ኩም" ያደረጉ የእውነት ሰውም ናቸው፡፡

እንደውም ዶ/ር ነጋሱ በዚህ መፅሀፋቸው በገፅ - 150 ላይ ፦

<<…… እነ ሌንጮና ኦነግ የሚሰሩት ስራ እኮ መስመሩን የሳተ ነበር። የኦህዴድ ሴት ታጋዮች በኦነግ ጡታቸው ይቆረጥ ነበር። ወንዶች ደግሞ የጭናቸው ስጋ እየተቆረጠ ብሉት ይባሉ ነበር። በበደኖ በርካታ ሰዎች ከእነ ህይወታቸው በገደል እየተወረወሩ ተገድለዋል። ይሄ የተፈፀመው በኦነግ ወታደሮች መሆኑን የኦነግ አመራር አባቢያ አባ ጀበል ፓርላማ ቀርቦ አምኖ ነበር። ይሄ የተመዘገበ ታሪክ ነው……። >> ሲሉ ፥ በድፍረት በዘመናችን ከተፈፀሙ አሰቃቂ ጭፍጨፋዎች መካከል ኦነግ በበደኖና አርባጉጉ በአማራዎች ላይ ከፈፀመው የዘር ፍጅት ባሻገር ኦሮሞዎችን ሳይቀር ጡታቸውንና ብልታቸውን ሲቆርጥ ፥ ስጋቸውን ሲያበላ የነበረበትን ዘግናኝ ድርጊት ለታሪክ ምስክርነት ከትበው አልፈዋል፡፡

ሌላው ደግሞ ፦ ፕ/ር መራራ ጉዲና ያኔ እንደዛሬው በቤትና በመኪና "silent" ሳይደረጉ በፊት ፥ በተለያዩ ጊዜያት << ... ኦሮሞ አራት ኪሎ ከገባ ፥ አስከሬኑ ተጎትቶ ይወጣታል እንጂ ኢትዮጵያን ሳያፈርስ አይወርድም! >> ማለታቸው ይነገር ነበር፡፡

እናም የፖለቲካ ብስለት ባላዳበረ የልጅ አዕምሮዬ << እኚህ ፖለቲከኛ ህዝባቸው በጥላቻ ፖለቲከኞች የታነፀበትን እኩይ አመለካከት ምን ያህል ቢረዱት ነው ? >> ብዬ አሰላስል ነበር፡፡

ታዲያ! ሁለቱን አንጋፋ የነበሩና ከኦሮሞ ህዝብ መካከል የተገኙ የምናከብራቸው ፖለቲከኞች በዋቢነት ያነሳሁት ፥ ያኔ እነዚህ የፖለቲካ ሰዎች ይሰጡት የነበረው ሀሳብ ዛሬ እውን ሆኖ እያየነውና ሀገርን ወደፍርስራሽነት ለመቀየር ከጫፍ የደረሰ የፖለቲካ ቡድን ተፈጥሮ በመመልከታችን ነው፡፡ እውነት ለመናገር የኦሮሞ ፅንፈኛ ፖለቲከኞች ህዝባቸውን የሚቀርፁበት አመለካከት አይደለም ከስጋ ለባሽ ሰብአዊ ፍጡር ጋር ከአለማቱ ጌታ ጋር እንኳ የሚያግባባ አይደለም፡፡

ከሁሉም ተቃራኒ የመቆም አባዜ ፤ ከሙታን ጋር ህያዋንን ግብ ግብ ከቶ የሚያታግል ክፉ አመለካከት ፥ በተለይ አማራ "ነጭ" ካለ እነሱን "ጥቁር" የሚያስብል ክፉ መንፈስ ፥ እጅግ በጣም ይገርመኛል ፥ ያሳስበኛልም፡፡

እኔ የየትኛውንም ህዝብ ባህል ፣ ወግ ፣ ቋንቋ ፣ ማንነት ፣ ሀይማኖት ...ወዘተ አከብራለሁ፡፡ አመለካከት ግን አብሮ ለመኖር የሚያስችለን ወሳኙ መግባቢያ በመሆኑ መደገፍ ያለበትን እደግፋለሁ ፥ መታገል ያለብንን ደግሞ አምርሬ እታገላለሁ!

ነገርግን ላለመግባት ክርክርና ሙግት የሚገጥም ፥ ከእኛነት ይልቅ እኔነትና "ሁሉ የኔ" የሚያስብል ስግብግብ አመለካከት ፥ ሁልጊዜ በተቃራኒው የመረዳትና የመቆም አባዜ ፥ ትልቅ ህዝብ ይዞ በአናሳና በዝቅተኝነት የአስተሳሰብ ጠኔ የሚናውዝ የፖለቲካ ቡድን ጋር ፥ እንዴትስ ተብሎ አንድ ሀገር አቁሞ ፥ በፍቅርና በመከባበር ወደፊት መጓዝ ይቻላል ?

ጎበዝ! የምሬን ነው የምላችሁ ፦ ይህን ሳስብ የኢትዮጵያ ተስፋ ፈፅሞውኑ ይሟጠጥብኛል!