Get Mystery Box with random crypto!

አልልም! ‘ሚለው ፥ ዘፈን ስላረጀ አንድ አባት ለልጁ ፥ ይህን ምክር አወጀ። ልጄ ሆይ! አድም | ዘሪሁን ገሠሠ

<<ተማር ልጄ>> አልልም!

<<ተማር ልጄ>> ‘ሚለው ፥ ዘፈን ስላረጀ
አንድ አባት ለልጁ ፥ ይህን ምክር አወጀ።

ልጄ ሆይ! አድምጠኝ…

ደብተርህን ጣለው ፤ ምናባቱ ቀለም
አውቆ እንደቆመ ሰው ፥ የቀለለ የለም
ሐብት መዋያ አጥቶ ፥ መሐይም ላይ ወድቋል
ሊቅ ርካሽ ሆኖ ፥ ልቅ ራት ይነጥቃል።

እኔ ባንተ እድሜ
ተማሪ ፊት ቆሜ
ለአንደኝነቴ ፣
ጭብጨባ ሲያጅበኝ
ሽልማት ስቀበል፣ የነበረኝ ኩራት
መጠሪያ ሸልሞኝ
መጦሪያ ነፍጎኛል
ለቀን ጭንቀት ድሮኝ ፤ ለቁርስ፣ ምሳ ፣ራት።

ምን በወጣህ ልጄ! ፣ እኔን የምትደግም
ጥሩ መኖር ካሻህ፥ ሳትሰስት ለግም!!
ባይሆን ባንተ ጊዜ ፥ በአባትነትህ ወቅት
ለጭንቅላት መክፈል ፥ ከጀመረች አገር
ተማር ልጄ ብለህ ፤ የልጅ ልጄን ምከር!

ገጣሚው ፦ ዶ/ር ሮዳስ ተመስገን / Dr. Rodas Temesgen