ዘሪሁን ገሠሠ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zerihunkocha — ዘሪሁን ገሠሠ
ርዕሶች ከሰርጥ:
Стоп
Oromia
Caution
Amhara
Usa
Jan
Comment
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @zerihunkocha
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.10K
የሰርጥ መግለጫ

በመረጃ እንቀራረብ! በመረጃ እንተሳሰር!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-02-03 21:51:48
እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ!!!

#ኦሮሚያ_ልዩ_ዞን

ያው እንግዲህ "ብአዴን" በ11ኛው ሰአትም ቢሆን ይሰማኛል ብዬ ስለማላስብ ፥ በአከባቢውና በዙሪያው ያላችሁ ወገኖቻችን ፥ የልዩ ሀይልና የፋኖ አባላት እንዲሁም ለተለያዩ ተግባራት በትራንስፖርት የሚንቀሳቀሰውን ጨምሮ መላው ህዝባችን ፥ ምንም ዝርዝር ሳያሻው ከወትሮው የተለየ እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ ለማሳሰብ እወዳለሁ!
7.3K views18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 20:41:09
በትናንትናው እለት በ25/05/2015 ዓ.ም ንጋት ላይ ፥ በምስራቅ ወለጋ ዞን ፥ ጎቡ ሰዮ ወረዳ  በአኖ  ከተማ በአሰቃቂ ሁኔታ የተጨፈጨፉትና አስከሬናቸው የተገኘው አማራዎች እነዚህ ናቸው!

ወለጋ ጧት ማታ በንፁሃን ደም የምትታጠብ ምድራዊ ሲኦል!
4.5K views17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 17:31:36
4.4K views14:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 17:31:27 ከእንግዲህ ፦ መንግስት መር ለሆነው የወገኖቻችን ጭፍጨፋ ፤ ፈጣሪን እንጂ መንግስትን "ድረስላቸው!" አልልም!

የክፋትና ሀገር የማፍረስ አጀንዳቸውን ለማጣፋት የሚሞክሩትም ፥ በሌላ የክፋትና የጭካኔ አጀንዳ ነው!

በትናንትናው እለት በምስራቅ ወለጋ ዞን፥ ጎቡ ሰዮ ወረዳ በአኖ ከተማ የተለመደው አሰቃቂ ማንነትን መሠረት ያደረገ የዘር ፍጅት መፈፀሙ ታውቋል፡፡ እስካሁን ባለው መረጃ በጨፍጫፊው ቡድን ታግተው ከተወሰዱት 50 ሰዎችና አስከሬናቸው ካልተነሱት ውጪ ፥ አንድ ጭፍጨፋውን የተቃወመ የኦሮሞ ብሄር ተወላጅን ጨምሮ 23 ሰዎች በስም የታወቁ የጭፍጨፋው ሰለባ መሆናቸው ተገልፇል፡፡

የሟቾቹ ስም ዝርዝር ፦

1. አብዱ ሱፍያን
2. አማን ሰይድ
3. አብዱ ሰይድ
4. ጋሻው ክብረት
5. ከማል መሀመድ
6. ደምሴ ምስጋናው
7. ሰይድ ሙላት
8. ኢብራሂም ሰይድ
9. ሽህ/ ሰይድ ውሴን
10. መሀመድ ቃሲም
11. ካሳዬ ገዛኸኝ
12. መሀመድ አደም
13. ማርዬ እንድሪስ
14. እማዋይ ይመር ከእነ ቧሏ
15. መሀመድ እስማኤል
16. አሊ ሲራጅ
17. አለባቸው -----?
18. መሀመድ ሸኪ
19. ካሳዬ ታደሰ?
20. የኑስ ሰይድ
21. ሱፍያን ሰይድ
22. መሀመድ ይብሬ
23. ጉተታ ዘንባባ (የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ የሆነ ሲሆን የተገደለው ለምን ንፁሀን ወንድሞቻችን ትገድላላቹህ?" ብሎ ቁጣውን በመግለፁና ተፈናቃይ ወገኖችን ሲደግፍ ሲያበረታታ ተስፋ ሲሰጥ የነበረ በመሆኑ የተገደለ ነው፡፡

ጥቃቱ ጥር 25/2015 ንጋት ላይ ከመፈጸሙ ቀደም ብሎ በጥር 24/2015 በአካባቢዉ ሰፍሮ የነበረዉ መከላከያ ሰራዊት በአቅራቢያው ወደምትገኘው ስቡበስሬ ከተማ የተወሰደ ሲሆን ፥ ጨፍጫፊው ቡድን ጥር 25/2015 ዓ.ም ንጋት ላይ ፥ ያለምንም ከልካይ በተሽከርካሪ ተጓጉዞ በመምጣት ፥ ጭፍጨፋ ፈፅሞ ፥ በርካቶችን አግቶ ፥ የመንግስትና የግል ንብረቶችን አውድሞና ጭኖ መሄዱን ነዋሪዎቹ ገልፀዋል፡፡

ከሟቾቹና ከታጋቾቹ መካከል አብዛኞቹ ከግማሽ ክ/ዘመን በላይ ከኖሩበት በጎቡ ሰዮ ወረዳና በ አከባቢዉ ባለፉት አመታት በደረሰባቸው ጥቃት ተፈናቅለው ወደወረዳው ከተማ አኖ የመጡ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡

ጠዋታ ማታ በንፁሐን የደም ጎርፍ በምትታጠበዋ ወለጋ በፍ የተጨፈጨፉትን ወገኖቻችንን ነፍስ ይማር !

አዎ! መንግስት መር ለሆነ ጭፍጨፋ ፈጣሪን እንጂ መንግስትን "ድረስላቸው!" አልልም!
4.2K views14:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 16:10:34
3.7K views13:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 16:10:24 እኔ ሙስሊም ነኝ ፤ ሙስሊምነቴ ግን ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ሀቅን ከመናገር አያግደኝም!

// በጋዜጠኛ - #አብዱራዛቅ_መሐመድ//

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለሀገር የዋለችውን ውለታ ቆጥረን አንጨርሰውም። ኢትዮጵያ እንደሀገር አንድ ሆና እንድትቀጥል ቤተክርስቲያኒቷ ከፍተኛውን ሚና ተጫውታለች። ትልቅ መስዋእትነትም ከፍላለች፤ እየከፈለችም ትገኛለች።

ለቤተክርስቲያኒቷ ውለታዋን መመለስ ባይቻል ማዋከቡ እንደሀገር ዋጋ እንዳያስከፍለን እሰጋለሁ። ቤተክርስቲያኒቷን መንካት ማለት ሀገርን መንካት መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል።

ኢትዮጵያን ለማዳከም አለፍ ሲልም ለማፍረስ የሚፈልጉ የውስጥና የውጭ ኃይሎች ቀድመው ቤተክርስቲያኒቷን ካላፈራረሱ ውጥናቸው እውን እንደማይሆን ያውቃሉ። ታሪክም የሚነግረን አሁንም የምናየው ይህንኑ ነው።

አሁን የተፈጠረው ችግር የቱንም ያህል ከባድ ቢሆን አባቶች ዘንድ መፍትሄ አይጠፋም። ከታሪክ እንደተረዳነው ከዚህ በፊትም ቤተክርስቲያኒቷ ከባባድ ፈተናዎችን አስተናግዳለች። ሆኖም ግን በቅዱሳን አባቶችና በአማኙ ትእግስትና ጥረት ታልፈዋል።

አሁንም የተፈጠረው ችግር ለአባቶችና ለኃይማኖቱ ተከታዮች እንተውላቸው። ችግሩ በፖለቲካዊ ሳይሆን በቤተክርስቲያኒቷ አስተዳደራዊና ቀኖናዊ አካሄዶች እንደሚፈታ ተስፋ አደርጋለሁ።

የሌላ እምነት ተከታዮች ግን በማያገባን እየገባን የምንፈተፍተው ነገር ችግሩን የበለጠ ያባብሰዋል እንጂ መፍትሄ አያመጣም። አማኞቹ እርዳታችን በፈለጉ ሰዓት አለሁ ማለት ኢትዮጵያዊ ባሕላችን መሆኑ ሳንዘነጋ ማለት ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶችና ምእመናን ሀቀኛ ስለመሆናቸው ከዛሬ 1,400 ዓመታት በፊት የአላህ (ሱ.ወ) ቃል በሆነው ቅዱስ ቁርዓን እንዲህ ተመስክሮላቸዋል፦

" ... እነዚያ እኛ ነሳራዎች (ክርስቲያኖች) ነን ያሉት ወደ ሙዕሚኖች (ሙስሊሞች) የቀረቡና የተወደዱ ሆነው በርግጥ ታገኛቸዋለህ። ምክንያቱም በውስጣቸው የተለያዩ ቄሶችና መነኮሳት ስላሉና እነርሱም የማይኮሩና ሀቅ በመጣ ጊዜ የሚቀበሉ በመሆናቸው ነው” (ቅዱስ ቁርዓን ምእራፍ 5 ቁጥር 82)/(ሱረቱል ማኢዳሕ፥82)

#ሼር
3.8K views13:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 15:02:39
የአንተን በኑሮ ውድነት መጠበስና ብስቁልና ካልደረሰባቸው እንዴት ሊረዱልህ ይችላሉ?

እንዳይደርስባቸው ደግሞ ከዘረፋና ምዝበራው ባሻገር በዚህ መልኩ ህግ አውጥተው ራሳቸውን ይታደጋሉ፡፡

☞ በአዲስአበባ ለተሾሙ በየደረጃው ያሉ አመራሮች ከተማ አስተዳደሩ ቤት ያመቻቻል!

ከመደበኛ ደመወዛቸው ውጪ የሚከፈል የኃላፊነት አበልን በተመለከተ ፦

☞ ለከንቲባውና ለምክር ቤት አፈ-ጉባኤ - 18 ሺህ ብር

☞ ለም/ከንቲባውና በምክትል ማዕረግ ለተሾሙ አመራሮች - 17 ሺህ ብር

☞ ለከተማ አስተዳደሩ ካቢኔዎችና በቢሮ ሀላፊነት ደረጃ ለተሾሙ - 16 ሺህ ብር

☞ በም/ኃላፊዎች ፥ ኮሚሽነሮች ወዘተርፈ - 15ሺህ ብር

☞ ፅ/ቤት ኃላፊዎች ፥ የወረዳ ስራ አስፈፃሚዎች ፣ የኮሌጅ ዲኖች ፥ ወዘተርፈ - 14 ሺህ ብር

☞ የወረዳ ም/ኃላፊዎችና መሠሎች - 13ሺህ ብር

☞ የወረዳ ካቢኔ አባላትና በዚያ ደረጃ ለተሾሙ - 12ሺህ ብር ይከፈላቸዋል፡፡

ይቺን አሰራር ክልሎችና በተዋረድ ያሉት መንግስታዊ መዋቅሮችም እንደአዲስአበባ ራሳቸው ህግ አውጥተው በማፅደቅ ሲገለገሉ የሚያሳይ መረጃ ባላገኝም ፥ በግልፅም በውስጥም እንደሚሰሩባት የሚታመን ነው፡፡

ኢትዮጵያ መሪዎቿና ሰፊው ህዝቧ የተራራቁት በዚህ መልኩ ነው! ሠፊው ህዝብ አክርማና ስንደዶ አዋጥቶ የሰፋትን ኢትዮጵያ የተባለች ሞሰብ ፥ የሚመገቡባት ፖለቲከኞች ሲሆኑ የበይ ተመልካች የሆነውና የሚደክምላት ደግሞ ሰፊው ህዝብ ብቻ ነው!
3.1K views12:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 23:31:55
ቻይና በኦሮሚያ የዜጋዋን ግድያ ተከትሎ ለዜጎቿ ማስጠንቀቂያ አወጣች! //BBC//

አንድ ቻይናዊ በኦሮሚያ ክልል ገብረ ጉራቻ ከተማ ከተገደለ በኋላ ቻይና በክልሉ ለሚንቀሳቀሱ ዜጎቿ ማስጠንቀቂያ ሰጠች።

ኤአፍፒ በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲን ጠቅሶ እንደዘገበው ሰኞ ጥር 22/2015 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ በሰሜን አቅጣጫ ገብረ ጉራቻ ከተማ 9 የቻይና ዜጎች በታጣቂ ቡድኖች ተኩስ ተከፍቶባቸው ነበር።

ተኩስ ከተከፈተባቸው ቻይናውያን መካከል አንዱ ሕይወቱ ማለፉን ሮይተርስ እና ኤኤፍፒ የዜና ወኪሎች በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲን ዋቢ አድርገው ዘግበዋል።

ኤምባሲው የዜጋውን መገደል ይፋ ባደረገበት መግለጫው፤ ጥቃቱን ያደረሰው ታጣቂ ቡድን ማን እንደሆነ እንዲሁም የጥቃቱ ዒላማ የሆኑት ቻይናውያን ማንነትንም አልገለፀም።

የቻይኛ ኤምባሲ መግለጫ አንድ ቻይናዊ መገደሉን ከመጥቀስ ውጪ፣ በሌሎች ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ ያለው ነገር የለም።

ከአዲስ አበባ 163 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኘው ከተማ በቻይናውያኑ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ኤምባሲው ባወጣው የጉዞ ማስጠንቀቂያ ላይ፤ “ከፍተኛ የአደጋ ስጋት ባለበት አካባቢ ከሆናችሁ፤ በአስቸኳይ ደኅንነቱ ወደ ተጠበቀ አካባቢ መውጣት አለባችሁ” ብሏል።

ኤምባሲው በኦሮሚያ ክልል እና በአጎራባች ክልሎች በጦር መሳሪያ የታገዘ ጥቃት፣ አፈና እና ዘረፋ የተስፋፋ ነው ብሏል።

ዘገባው ፦ የቢቢሲ ነው!
2.8K views20:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 19:01:24
በሁለት ልብስ አንድ መግለጫ...!

"…ይሄ ቪድዮ ሲቀረጽ አልነበርንም እያሉኝ ነው ሚንስትሩ። በእኛ ፊት እንዲህ ዓይነት ነገር አላነሣም። አልተናገረምም። እኛም ይሄ ማታ ሲቀርብ ደንግጠናል፤ መምህር ዘመድኩን ነው የሚሉኝ።

"…ክቡር ሚንስትር/ ሚኒስትሪት በምን ላረጋግጥ? አልኳቸው።

…የለበስነውን ልብስ እይ መምህር አሉኝ።

~ አየሁት።

"በመጨረሻም በአብይ አህመድ እና በዳኔል ክስረት በአዳራሽ የተወኑት ትወና መሆኑንም አረጋገጥኩ።

//መምህር ዘመድኩን በቀለ//
3.4K views16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 13:50:01
በአንድ ወቅት ብ/ጀነራል አሳምነው ጽጌ

<< …አሁን የገጠመን ፈተና ከዛሬ 500 ዓመት በፊት ከገጠመን ፈተና የከፋ ነው! ….. ይሄ ትውልድ ይሄን ታሪክ ካልተሻገረ ታሪካዊ ስህተት ይፈጸምበታል! .... አባቶች ብትችሉ ልክ እንደአቡነ ጴጥሮስ ሁኑ! >> በማለት መረር አርጎ የተናገረውን ንግግር ፥ አሁን ያለንበትንና የመጪውን ከባድ ጊዜ በቅጡ የተረዳ ሁሉ ፥ ከአዕምሮው ሊያጠፋው አይችልም!
3.5K views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ