Get Mystery Box with random crypto!

የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በሸገር ከተማ ቢያንስ ሰባት መስጊዶች መፍረሳቸውን ገለጸ! | YeneTube

የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በሸገር ከተማ ቢያንስ ሰባት መስጊዶች መፍረሳቸውን ገለጸ!

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በኦሮሚያ ክልል፣ ሸገር ከተማ ቢያንስ ሰባት መስጊዶች መፍረሳቸውን ለቢቢሲ ገለጸ።ምክር ቤቱ ባለፉት ሳምንታት አዲስ በተቋቋመው በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ በሚገኘው የሸገር ከተማ አስተዳደር ውስጥ ፈረሱ ስላላቸው መስጊዶች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ጽፏል።ሸገር ከተማ ተብሎ በኦሮሚያ ክልል እንደ አዲስ በተዋቀረው አካባቢ ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ ከመስጊዶች በተጨማሪ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው መኖሪያ ቤቶች እየፈረሱ መሆኑ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ እስካሁን በሸገር ከተማ ውስጥ ቢያንስ ሰባት መስጊዶች መፍረሳቸውን ተናግረዋል።“እስካሁን በሸገር ከተማ ውስጥ የፈረሱት ቢያንስ ሰባት መስጊዶች ናቸው። እነዚህም በሰበታ አምስት፣ በቡራዩ ሁለት መስጊዶች መፍረሳቸውን ነው ሪፖርት የደረሰኝ” ሲሉ ገልጸዋል።

“ለምን እንደፈረሰ አፍራሹን ክፍል ነው መጠየቅ፣ እኛ ፈረሰብን እንጂ አፍራሽ ክፍልን አግኝተን በምን ምክንያት ፈረሰ ብልን አልጠየቅንም” ሲሉ መስጊዶቹ ለምን እንደፈረሱ ማወቅ እንዳልተቻለ ሼኽ ሐጂ ኢብራሒም አስረድተዋል።ከፈረሱት መስጊዶች መካከል ቅድመ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው እና በድንገት የፈረሱ እንዳሉ መስማታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።በጉዳዩ ላይ የሸገር ከተማ ባለሥልጣናትን ለማነጋጋር ቢቢሲ በተደጋጋሚ ያደረገው ጥረት ስልካቸው ባለመነሳቱ አልተሳካም።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa