Get Mystery Box with random crypto!

በየመን የበርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አስክሬኖች ማግኘታቸውን ስደተኞች ተናገሩ! በየመን በረሃ | YeneTube

በየመን የበርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አስክሬኖች ማግኘታቸውን ስደተኞች ተናገሩ!

በየመን በረሃ ላይ ሞተው በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የአስከሬናቸው ምስሎች ሲሰራጩ የሰነበቱት ፍልሰተኞች ኢትዮጵያዊያን እንደኾኑ መረጋገጡን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ፍልሰተኞቹ ሕይወታቸው ያለፈው በሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ከየመን ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ በእግር በመጓዝ ላይ ሳሉ መኾኑን የዓይን ምስክር ፍልሰተኞች መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

20 ያህል የሚኾኑት ወንድና ሴት ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ሕይወታቸው ያለፈው፣ በድካም፣ ርሃብና ውሃ ጥም መኾኑን የዓይን ምስክሮቹ መናገራቸውን ዜና ምንጩ አመልክቷል። ዓለማቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት፣ ኢትዮጵያዊያን፣ ኤርትራዊያንና ሱማሊያዊያን ፍልሰተኞች በፑንትላንድ፣ ሱማሌላንድና ጅቡቲ በኩል ወደ የመን የሚሻገሩበት መስመር በርካቶችን ለሞት፣ ለአስገድዶ መደፈርና ድብደባ እያጋለጣቸው የሚገኝ እጅግ አደገኛ መስመር መኾኑን በተደጋጋሚ ይገልጣል።

@YeneTube @FikerAssefa