Get Mystery Box with random crypto!

 አንጋፋዋ ድምፃዊት ሂሩት በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች አንጋፋዋ ድምፃዊት ሂሩት በቀለ ባደረ | YeneTube

 አንጋፋዋ ድምፃዊት ሂሩት በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

አንጋፋዋ ድምፃዊት ሂሩት በቀለ ባደረባት ሕመም በ83 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።

ድምፃዊቷ ወደ ሙዚቃው ዓለም በ1949 ዓ.ም እንደገባች እና ረጅም የሙዚቃ ጊዜዋን በፖሊስ ሠራዊት ኦርኬስትራ እንዳሳለፈች የሕይወት ታሪኳ ያስረዳል።

ሂሩት በቀለ በተለይ “ኢትዮጵያ” በሚል የተጫወተችው ዘፈን በአገር አቀፍ ደረጃ የሚታወቅ እና ትንሽ ትልቁ በሀገር ፍቅር ስሜት የሚያዜመው ነው።
@Yenetube @Fikerassefa