Get Mystery Box with random crypto!

በሰሜናዊ ሶሪያ ሰሞኑን በደረሰው የመሬት ነውጥ በፍርስራሽ ውስጥ ተቀብራ የነበረችዋ ገና የተወለደች | YeneTube

በሰሜናዊ ሶሪያ ሰሞኑን በደረሰው የመሬት ነውጥ በፍርስራሽ ውስጥ ተቀብራ የነበረችዋ ገና የተወለደች ጨቅላ አተራረፍ አጀብ እያሰኘ ነው፡፡

በነውጡ ወቅት ምጥ ሲያፋፍማት የነበረችዋ እናት በዛው ወቅት ሴት ልጇን ተገላገለች፡፡

የነበሩበት ሕንፃ ተደረማመሰ፡፡
በፍርስራሽ ውስጥ ተቀበሩ፡፡

ስለ አደጋው የሰማ ዘመዳቸው ወደ ስፍራው ፈጠነ፡፡

ከፍርስራሽ ውስጥ የጨቅላ ሕንፃን ድምፅ ሰሙ፡፡

ገና የተወለደችዋን ሕፃን ከፍርስራሽ ውስጥ አወጧት፡፡

የጨቅላዋ እናት እና አባት ፣ አራት እህት እና ወንድሟ እንዲሁም አክስቷ እዛው በአደጋው ስፍራ ሞተው አስከሬናቸው ተገኘ፡፡ከፍርስራሽ ስር የወጣችዋ ጨቅላ ሆስፒታል ገብታ በመልካም ጤንነት ላይ ትገኛለች መባሉን ያወራው ቢቢሲ ነው፡፡

[BBC/Sheger]
@YeneTube @FikerAssefa