Get Mystery Box with random crypto!

'ከፕሮቴስታንት ፓስተሮችና ደህንነቶች ጋር አገኘኋቸው።' '.... 'አንተ ጥሩ ሰው ነህ እባክህ | YeneTube

"ከፕሮቴስታንት ፓስተሮችና ደህንነቶች ጋር አገኘኋቸው።"

".... 'አንተ ጥሩ ሰው ነህ እባክህ ሽማግሌ ሁንና አስታርቀን' ብለው ደውለውልኝ ልምጣና በአካል እንነጋገር ብያቸው አዲስ ከበባ ወሰን አካባቢ ቀጥረውኝ ወዳሉበት ስፍራ ሂጄ ነበር። ከእሳቸው ጋር ወደ 6 የሚሆኑ የፕሮቴስታንት ፓስተሮችና ደህንነቶች አብረዋቸው ነበር። ደህንነቶችም ' አንተ ነፍጠኛ አይደለህ ለምን መጣህ? በማለት አፋጠጡኝ እኔ ግን በዘር፣ በቋንቋና በብሄር ሳይሆን በእጄ በያዝሁት መጽሃፍ ቅዱስ ብቻ እንደማምን ነገርኳቸው። ከብዙ ወከባ በኋላ ተመልሼ ሄድኩ።

በማግስቱ ለጳጳሱ ደወልኩና ሌላ ስፍራ እንገናኝና እንወያይ ስላቸው 'ተው አይሆንም ደግሞ ከጴንጤ ጋር ታዬ ተብዬ ሌላ ችግር ልፍጠር' አሉኝ። እውነት ለመናገር ሁሉም አፈንጋጮች ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ የሚመሩትን ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታ ጠይቀው ወደ ቤታቸው መመለስ ይፈልጋሉ፣ ነገር ግን ልክ ወጥመድ ውስጥ እንደገባች አይጥ መውጫ አጥተዋል።....

"ይሁን እንጂ የብልጽግና መንግስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ያወቃት አይመስለኝም። ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መከራ በመጣባት ጊዜ ሁሉ ይበልጥ የምትፀና፣ በሯ በተንኳኳ ቁጥር አጥብቃ የምትቆልፍ ረቂቅ ቤተክርስትያን መሆኗን መረዳት ነበረበት። አሁን በኦርቶዶክስ ላይ እየሆነ ያለውን ሁሉ ሁላችንም አጥብቀን የምናወግዘው ከመሆኑም ባሻገር ከቤተክርስትያኒቷ ጎን በመቆም አብሮነታችንን መግለጽ እንፈልጋለን።"

ፓስተር ቢንያም
@Yenetube @Fikerassef