Get Mystery Box with random crypto!

መንግሥት በአስቸኳይ መልስ የማይሰጥ ከሆነ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገ | YeneTube

መንግሥት በአስቸኳይ መልስ የማይሰጥ ከሆነ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እሑድ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በመላው ዓለም ተፈጻሚ የሚሆን የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ አደረገ።

መንግስት የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል ለተነሱ ወራሪ ቡድኖች ድጋፍ እየሰጠ የሚገኝ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶሱ ጾመ ነነዌን መላው ኦርቶዶክሳውያን ጥቁር ልብስ በመልበስ እና ወደ እግዚአብሔር በመፀለይ እንዲያሳልፉ ያዘዘ መሆኑ ይታወሳል።

ሆኖም መንግስት በተከታታይ 7 ቀናት ውስጥ ተግባራዊ ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ ከሁሉም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት መነሻቸውን ያደረጉ እና ወደ መስቀል አደባባይ እና ወይም ወደ ባሕረ ጥምቀት ሐድረሻቸውን ያደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች እንዲደረጉ መመሪያ ሰጥቷል።

[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa