Get Mystery Box with random crypto!

ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ፤ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ እና ደራሲ አሳዬ ደርቤ በነፃ እንዲሰናበቱ የፌደራል | YeneTube

ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ፤ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ እና ደራሲ አሳዬ ደርቤ በነፃ እንዲሰናበቱ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የሕገ መንግስት እና ፀረ ሽብር ችሎት ውሳኔ ሰጠ።

ደራሲና ጋዜጠኞቹ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀውን ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የሚደግፍ ንግግሮች በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች እና በበይነ መረብ አስተላልፋችኋል በሚል ተከሰው ነበር።

በተጨማሪም የአገር ደህንነት ሚስጥር የሆኑ እና መነገር የሌለባቸውን መረጃዎች ለሚዲያ እና ለሕወሓት አሳልፋችሁ ሰጥታችዋል ተብለውም ተከሰው እንደነበር ጠበቃቸው አዲሱ ጌታቸው ተናግረዋል።

ችሎቱ ዛሬ ተቀጥሮ የነበረው ይከላከሉ ወይስ በነፃ ይሰናበቱ በሚል ውሳኔ ለመስጠት ነበር። በዚ መሰረት አቃቤ ህግ እንደ ክስ አቀራረቡ ያላስረዳ ስለሆነ ሶስቱም ተከሳሾች መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ ተሰናብተዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa