Get Mystery Box with random crypto!

የቆመው የህዳሴ ግድብ ድርድር አፅዕኖት እንዲሰጠው ግብፅ ለፈረንሳይ መንግስት አስታወቀች! የግብፅ | YeneTube

የቆመው የህዳሴ ግድብ ድርድር አፅዕኖት እንዲሰጠው ግብፅ ለፈረንሳይ መንግስት አስታወቀች!

የግብፅ ከፍተኛ ባለስልጣናት በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከፈረንሳይ ባለስልጣናት ጋር ውይይት እንዳደረጉ የተገለፀ ሲሆን በግድቡ ዙሪያ ለጊዜው ቆሞ ላለው ድርድር ግብፅ ኢትዮጵያን ተጠያቂ በማድረግ ወቅሳለች።

ግብፃውያኑ ባለስልጣናት የግድቡ ጉዳይ የግብፃውያን የህልውና ጥያቄ ስለሆነ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል ሲሉ አፅዕኖት ሰጥተውታል ተብሏል።የባለስልጣናቱ ውይይት በአፍሪካ የውሃ ሃብት አጠቃቀም፣ በህዳሴው ግድብ ላይ ግብፅ ባላት አቋም እና ለጊዜው በቆመው ድርድር ላይ ትኩረት እንዳደረገ ታውቋል።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa