Get Mystery Box with random crypto!

በጾመ ነነዌ ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ ጸሎታችሁን አድርሱ ስትል የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን | YeneTube

በጾመ ነነዌ ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ ጸሎታችሁን አድርሱ ስትል የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥሪ አቀረበች!

የፊታችን ሰኞ በሚገባዉ እና ለሶስት ቀናት በሚቆየዉ የነነዌ ጾም ምዕመኑ ጥቁር ልብስ በመልበስ ምህላ እንዲይዝ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪ አቅርቧል።ቅዱስ ሲኖዶስ በመግለጫዉ ፤ጥቁር ልብስ የምንለብሰው በመከራ መጽናት ለመግለጽ ነው ፤ ከእውቀት በላይ የሆነውን አምላካችንን በመማፀን ፈተናዉ ከዚህም ማንም ሊያናውጽን እንደማይችል የምናረጋግጥበት ነዉ ብሏል።

በተጨማሪም ጥቁር የእውነት ምልከት ነው ያለዉ መግለጫው ፤ ዳኞች እውነት እንፈርዳለን ሲሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ፤ እኛም መከራው የሚያሰቅቀን ሳይሆን ይበልጥ ልንጸናና ልንበረታ የሚገባ መሆኑን ለዓለም ሕዝብ የምናሳይበት በመሆኑ ከጥር 29 እስከ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ለሦስት ቀናት በጾምና በጸሎት በአንድ ልብ በመሆን ወደ ፈጣሪያችንን እንድትጮሁ ሲል በመግለጫው ጥሪ ማቅረቡን ብስራት ራዲዮ ተመልክቷል።

ቅድስት ቤተ ክርስቲያኗ በተከሰተው ሃይማኖታዊ ፣ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ መዋቅሮቿን በመጣስ መፈንቅለ ሲኖዶስ በማድረግ በሕገወጥ መንገድ ኤጲስ ቆጶስነት ሢመት በሰጡትና በተሾመ ግለሰቦች ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥር 18 ቀን 2015ዓ.ም. ቃለ ውግዘት ማስተላለፉ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ እነዚህ ሕገወጥ ያለቻቸዉ ቡድኖች ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ካለመቻላቸውም በላይ በመንግሥት ኃይሎች በመታገዝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታስተዳድራቸውን መንበረ ጵጵስናዎችንና ቢሮዎችን በኃይል በመውረርና በመስበር ከፍተኛ ጥፋት እያደረጉ ከመሆኑም በላይ የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችን ሠራተኞች ካህናትና ምእመናን በማሰርና በማንገላታት ላይ ይገኛል ብሏል መግለጫው፡፡

መንግሥትም ሕግ ከማስከበር ይልቅ ለሕገ ወጥ ቡድኖች ድጋፍ በመስጠት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግና መብት ሊያስከብር አልቻለም ያለዉ ሲኖዶሱ ፤ ሁሉን ማድረግ ወደሚቻለው አምላካችን በመማፀን ጸሎትና ምሕላ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ተረድቷል ብሏል።በመሆነም ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንዲያቀርቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa