Get Mystery Box with random crypto!

የአሜሪካ የእንደራሲዎች ምክር ቤት ትውልደ ሱማሊያዊቷን ኢልሃን ኦማርን በጠባብ ድምጽ ብልጫ ከውጭ | YeneTube

የአሜሪካ የእንደራሲዎች ምክር ቤት ትውልደ ሱማሊያዊቷን ኢልሃን ኦማርን በጠባብ ድምጽ ብልጫ ከውጭ ጉዳይ ኮሚቴ አባልነታቸው አንስቷል። ሪፐብሊካን ፓርቲ አብላጫ መቀመጫ የያዘበት ምክር ቤት፣ የሚኖሶታ ግዛት ተወካይዋን ኦማርን ከወሳኙ ኮሚቴ ያነሳቸው፣ ቅድም ሲል "እስራኤል ጠል" የሆኑ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል በማለት ነው። የኦማር ፓርቲ የዲሞክራቲክ ፓርቲው አባላት ግን፣ የኦማርን ከኮሚቴው መነሳት በሙሉ ድምጽ ተቃውመውታል። ኦማር ውሳኔው፣ ሪፐብሊካን ፓርቲው በፖለቲካ ተቀናቃኞቹ ላይ የወሰደው የበቀል ርምጃ ነው በማለት ውሳኔውን አውግዘውታል።

@YeneTube @FikerAssefa