Get Mystery Box with random crypto!

መንግሥት የዜጎችን መብት እንዲያስከብር ተጠየቀ! መንግስት የዜጎችን በሰላምና በህይወት የመኖር መ | YeneTube

መንግሥት የዜጎችን መብት እንዲያስከብር ተጠየቀ!

መንግስት የዜጎችን በሰላምና በህይወት የመኖር መብታቸውን እንዲያስከብር በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ማህበራት ጥሪ አቀረቡ።በውጭ የሚገኙ፣ሃያ አንድ የኢትዮጵያውያን ማኀበራት ሰሞኑን በአጣዬና ና አካባቢው የተፈጸመውን ግጭት አስመልክቶ ባወጡት የጋራ መግለጫ ላይ፣መንግሥት የሚፈፀመዉን ጥቃት በማስቆም ተጠያቂነት የማስፈን ኃላፊነቱን እና ዜጎች በሠላምና በሕይወት የመኖር መብታቸውን የማስከበር ግዴታውን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

እነዚሁ "ትዕግሥት ገደብ ሲያጣ፣ ጥፋትን ያመጣ"በሚል ርዕስ መግለጫውን ያወጡት ማኀበራት፣በሰሜን አሜሪካ በአውሮፓና በአውስትራሊያ የሚገኙ ናቸው።ማኀበራቱ፣ በአጣየ፣በሸዋሮቢት እና በአካባቢው በሚኖረው ህዝብ ላይ የሚደረሰው ተደጋጋሚ የህብሪት ወረራና የንብረት ውድመት፣ ከፍተኛ ሐዘንና ምሬት እንደፈጠረባቸው በመግለጫቸው ላይ ጠቅሰዋል። መንግስት መሰል ችግሮች ከመከሰታቸው አስቀድሞ የመከላከል አቅሙን በማጎልበት ዜጎቹን ከጥቃት መከላከል ይገባዋል ይላሉ ዶይቸ ቨለ ያነጋግራቸው የማኀበራቱ ተወካይ ኢንጂነር እዝቅኤል እስክንድር።

ጥቃቱ፣መንግስት "ሸኔ"በሚል በአሸባሪነት የፈረጀው፣ ራሱን ግን የኦሮሞ ነጻ አውጭ ሰራዊት በማለት በሚጠራው ኀይል የሚፈጸም መሆኑንም አመልክተዋል። ሰቆቃና ጭፍጨፋው በዚኹ ደረጃ መቀጠሉ ማንኛውንም ቀና ዐሳቢ፣ ሰላም ፈላጊና አገር ወዳድ ህዝብ ሁሉ ሊያሳስብ እንደሚገባ እና ዝም ብሎ ሊታለፍ እንደማይገባም ገልጸዋል።ማዕከላዊ መንግስት፣ማኀበራቱ በአካባቢው ህዝብ ላይ ይፈጸማል ያሉትን የዘር ማጥፋት አረመኔያዊ ዘመቻ በአስቸኳይ ሊያስቆም እና ተጠያቂነት እንዲሰፍን የማድረግ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ማህበራቱ ጠይቀዋል፤ የማህበራቱ ተወካይ ኢንጂነር እዝቅኤል።መንግስት የዜጎችን በሰላምና በሕይወት የመኖር መብታቸውን የማስከበር ግዴታውን እንዲወጣም አበክረው ጠይቀዋል።

ማኀበራቱ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላለፉት መልእክትም፣ በተለይ በዐማራው ማኀበረሰብ ላይ ተከፍቷል ያሉት ማንነት ተኮር ዘመቻ፣ የኢትዮጵያን ሀገራዊ አንድነት እና የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ሰላም በእጅጉ የሚፈታተን እንደሆነ አስገንዝበዋል።በዐማራ ክልል በኦሮሞ ማህበረሰብ አስተዳደርና በሰሜን ሸዋ አዋሳኝ ወረዳዎች ሰሞኑን የተቀሰቀሰውን ግጭት አስመልክቶ ስሙ የተነሳው መንግስት "ኦነግ ሸኔ"በሚል የፈረጀው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ቃል አቀባይ፣አቶ ኦዳ ቶርቢ ባለፈው ሳምንት ስለጉዳዩ ተጠይቀው ለዶይቸ ቨለ በሰጡት ምላሽ ውንጀላውን አስተባብለዋል። አቶ ኦዳ፣ለጥቃቱ የዐማራ ኀይሎችን ነው ተጠያቂ ያደረጉት።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa