Get Mystery Box with random crypto!

ኢዜማ የፀጥታ ኃይሎች በቤተ ክርስትያኗ ላይ እየወሰዱት ያለው እርምጃ አሳስቦኛል አለ! ከሰሞኑ | YeneTube

ኢዜማ የፀጥታ ኃይሎች በቤተ ክርስትያኗ ላይ እየወሰዱት ያለው እርምጃ አሳስቦኛል አለ!

ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህሕዶ ቤተ ክርስትያን ውስጥ የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ የፀጥታ ኃይሎች እየወሰዱት ያለው እርምጃ እና ጣልቃ ገብነት እንደሚያሳስበው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አስታወቀ።

ኢዜማ ዛሬ ባወጣው መግለጫ “በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህሕዶ ቤተ ክርስትያን የውስጥ ጉዳይ ላይ ከተለያዩ አቅጣጫዎች እየተስተዋሉ ያሉ ጣልቃ ገብነቶች መዘዛቸው ከባድ ነው፤ ችግሩን አባብሰው ደም አፋሳሽ ግጭት ሊያስከትሉ የሚችሉ አዝማሚያዎችም እየተስተዋሉ ነው” ብሏል። መንግስት ከተለያዩ አቅጣጫዎች እየተስተዋሉ ያሉ ጣልቃ ገብነቶችን መዘዛቸውን ተረድቶ በአስቸኳይ ሕግ እና ሥርዓትን አክብሮ እንዲያስከብር ሲልም ፓርቲው አሳስቧል።

የኢዜማ መግለጫ አክሎም “የሃይማኖት ተቋማት ላይ በማናቸውም ወገን የሚደረግ ጣልቃ ገብነት መዘዙ ብዙ ስለሆነ፤ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሁሉ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እናሳስባለን” ብሏል።

በኢፈድሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 11 መሰረት መንግስት በሃይማኖት ላይ፣ ሃይማኖት ደግሞ በመንግስት ላይ ጣልቃ እንደማይገባ በግልጽ ተደንግጎ ይገኛል።በኦሮሚያ ክልል በወሊሶ ከተማ የተደረገውን የጳጳሳት ሹመት ቅዱስ ሲኖዶስ “ሃይማኖታዊ ክህደት፣ ቀኖናዊ ጥሰት እና አስተዳደራዊ ግድፈት የታየበት” ነው በማለት ማውገዙ ይታወሳል።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa