Get Mystery Box with random crypto!

'ከህብረተሰቡ ባህልና ሞራል ያፈነገጡ ሕገወጥ ድርጊቶች ሲከናወኑባቸው ተገኙ' የተባሉ ቤቶች ታሸጉ! | YeneTube

"ከህብረተሰቡ ባህልና ሞራል ያፈነገጡ ሕገወጥ ድርጊቶች ሲከናወኑባቸው ተገኙ" የተባሉ ቤቶች ታሸጉ!

በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ በተመራ የጋራ ግብረ ሃይል በተወሰደ እርምጃ በቦሌ ክ/ከተማ በቀነኒሳ ሆቴል 59 የሺሻ እቃ እንዲሁም ከህብረተሰቡ ባህልና ሞራል ያፈነገጡ ሕገወጥ ድርጊቶች ሲከናወኑ በመገኘቱ ሆቴሉ እንዲታሸግ መደረጉን ቢሮው ገልጿል።

በተመሳሳይ በማማስ ኪችን ህንፃ በሚገኘውና ዘኬጅ በተሰኘው የምሽት ክበብ ውስጥም 27 የሺሻ እቃ መያዙንና ክበቡም እንዲታሸግ መደረጉን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa