በስልጤ ዞን በተደረገ ድንተኛ ፍተሻ ከ450 በላይ የሺሻ ማጨሻ እቃዎች ተወገዱ !! በጉዳዩ ላይ | YeneTube

በስልጤ ዞን በተደረገ ድንተኛ ፍተሻ ከ450 በላይ የሺሻ ማጨሻ እቃዎች ተወገዱ !!

በጉዳዩ ላይ የተሳተፉ አካላት ጉዳያቸው በህግ ተይዟል !!

በሰልጤ ዞን ሚቶ ወረዳ በ5 ዙር በተደረገው ድንገተኛ የቤት ለቤት ፍተሻ 450 የሚሆኑ የሺሻ ማጨሻ እቃዎች እንደተወገዱ ብስራት ሰምቷል።

ሰባት በሚሆኑ ህገ ወጥ ማስጨሻ ስፍራዎች ላይ በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ እቃዎቹ ከመያዛቸው በተጨማሪ በጉዳዩ የተጠረጠሩ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ አቶ ጌታሁን ተከተል ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

ማስጨሻ እቃዎቹ በገበያ ስፍራ መሀል እንዲቃጠሉ መደረጋቸው ማህበረሰቡን ለማስተማር ሲባል የተወሰደ እርምጃ ነው።

መሰል ህገ ወጥ ተግራባት በወረዳው መበራከቱን ያነሱት አቶ ጌታሁን በዋነኛነት ወጣቱ የዚህ ሰለባ እየሆነ ይገኛል ሲሉ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።Via: ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa