በጅቡቲ ከኢንተርኔት መቋረጥ ጋር ተያይዞ የኢትዮ ሳት ቻናሎች ስርጭት ተቋርጧል! በጅቡቲ ከኢንተር | YeneTube

በጅቡቲ ከኢንተርኔት መቋረጥ ጋር ተያይዞ የኢትዮ ሳት ቻናሎች ስርጭት ተቋርጧል!

በጅቡቲ ከኢንተርኔት መቋረጥ ጋር ተያይዞ የኢትዮ ሳት ቻናሎች ስርጭት መቋረጡን ኤስ ኢ ኤስ ኢትዮጵያ አስታወቀ፡፡የኢንተርኔት መቋረጡ ሁሉንም አገልግሎቶች አስተጓጉሏል ያሉት የተቋሙ የምሰራቅ አፍሪካ ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ መነን አገኘሁ ችግሩን ለመፍታት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡እስካሁን ባለው ሂደትም አንዳንድ አገልግሎቶችን መመለስ ተችሏል ያሉት ኋላፊዋ፣ ሁሉንም አገልግሎቶች ወደነበሩበት ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አሳውቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa