Get Mystery Box with random crypto!

የኮዬ ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ጥያቄ በህዳር ወር መጨረሻ ምላሽ ያገኛል | YeneTube

የኮዬ ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ጥያቄ በህዳር ወር መጨረሻ ምላሽ ያገኛል ተባለ

ኮዬ ፈጬ 2 ተብሎ በሚጠራው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለባለ እድለኞች ከተላለፉ በኃላ ኑሯቸውን በእዚያ ያደረጉ ነዋሪዎች ለከፍተኛ ችግር ተዳርገናል ሲሉ ለብስራት ሬዲዮ ቅሬታቸውን ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

ነዋሪዎቹ የቤት ባለ እድል መሆናቸውን ካረጋገጡ በኋላ ያለው የኤሌክትሪክ ችግር እስከ መስከረም ወር ይፈታላችኋል ቢባሉም ችግሩ ዛሬም ድረስ ሳይቀረፍ እንደቀረ ይገልጻሉ፡፡

ጉዳዩን በሚመለከት ብስራት ሬድዮ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፤ የአዲስ አበባ ኮንዶሚኒዬም ኤሌክትሪፍኬሽን ፕሮጀክት ኃላፊ አቶ ሰለሞን አበራ የነዋሪዎቹን ቅሬታ ትክክለኛ መሆኑን በማንሳት ችግሩ እስከ ህዳር ወር መጨረሻ ድረስ ይቋጫል ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

ስፍራው ከፍተኛ የተባለ ግንባታ የሚከናወንበት በመሆኑ ለመስመር ዝርጋታ አዳጋች አድርጎብናል ያሉት ኃላፊው ፤ የተቋራጮቾች የግንባታ መጓተት ሌላኛው ችግር እንደነበር ጠቁመዋል፡፡

ለስፍራው 22 የሚሆኑ ትራንስፎርመሮች እንደሚያስፈልጉ የተናገሩት አቶ ሰለሞን እስከ አሁን ባለው ሂደት 11 ትራንስፎርመሮችን ተከላ አጠናቀናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ከእዚህ ባለፈ 788 ገደማ ህንፃዎችን የያዘ ሰፊ አካባቢ በመሆኑ ግንባታው በአፋጣኝ እንዳይጠናቀቅ አድርጓል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

እስከ ህዳር ወር መጨረሻ ድረስ ስራውን በማጠናቀቅ የነዋሪዎቹን ቅሬታ ለመቅረፍ እንሞክራለን ያሉት ሓላፊው ይህንኑ እቅድ ለተቋራጩ በማስረዳት ወደ ተግባር ገብተናል ነዋሪዎቹ በትዕግስት ሊጠብቁን ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Via:- ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa