Get Mystery Box with random crypto!

የፖለቲካ ተቀናቃኞቹ ኢራን እና አሜሪካ ከ24 ዓመታት በኋላ በኳታሩ የዓለም ዋንጫ በዛሬው ዕለት ይ | YeneTube

የፖለቲካ ተቀናቃኞቹ ኢራን እና አሜሪካ ከ24 ዓመታት በኋላ በኳታሩ የዓለም ዋንጫ በዛሬው ዕለት ይፋለማሉ፡፡

በምድብ ሁለት የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ አያቶላዎቹ ኢራን እና የፖለቲካ ባላንጣዋ አሜሪካ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በአል ቱማማ ስታዲየም ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
ሁለቱ ሀገራት በፈረንጆቹ በ1998 ፈረንሳይ ባዘጋጀችው የዓለም ዋንጫ ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙ ሲሆን ÷ ኢራን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፏ ይታወሳል፡፡

ኢራን ሶስት ነጥብ በመያዝ ከእንግሊዝ በመቀጠል ምድቡን በሁለተኛ ደረጃ ስትመራ አሜሪካ ሁለት ጨዋታዎችን በአቻ ውጤት በማጠናቅቅ ሁለት ነጥብ ይዛ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ከእግርኳስ በላይ ከፍተኛ የፖለቲካ ትርጉም ባለው የሁለቱ ሀገራት ጨዋታ ኢራን አሜሪካን ካሸነፈች ወይም ነጥብ ከተጋራች ወደ ቀጣዩ ዙር የምታልፍ ሲሆን÷ አሜሪካ ባንፃሩ ከምድብ ለማለፍ ኢራንን ማሸነፍ ይጠበቅባታል፡፡

ሀገራቱ በታሪካቸው በዓለም ዋንጫ እና በወዳጅነት የጨዋታ መድረክ እስካሁን ሁለት ጊዜ ብቻ የተገናኙ መሆኑን የጎል ዶት ኮም መረጃ ያመላክታል፡፡
በዚህም ኢራን የማሸነፍ የበላይነቱን ይዛ መቆየቷ ነው የተጠቆመው፡፡

@Yenetube @Fikerassefa