Get Mystery Box with random crypto!

የአርቲስት አሊ ቢራ የክብር ሽኝት በነገው ዕለት ይካሄዳል! የክብር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ የ | YeneTube

የአርቲስት አሊ ቢራ የክብር ሽኝት በነገው ዕለት ይካሄዳል!

የክብር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ የክብር የአሸኛኘት ሥነስርዓት በነገው ዕለት በወዳጅነት አደባባይ ይካሄዳል።የቀብር አሰፈጻሚው ኮሚቴ፤ አስክሬኑ ቢሾፍቱ ከሚገኘዉ የአርቲስት አሊ ቢራ መኖሪያ ቤት ወደ ወዳጅነት አደባባይ እንደሚመጣ ገልጿል፡፡

የአሸኛኘት ፕሮግራሙ በወዳጅነት አደባባይ ከ3፡00 ጀምሮ በተለያዩ ሥነ ስርዓት ይከናወናል፡፡በወዳጅነት አደባባይ የክብር እና የጀግና ስንብት ከተደረገለት በኋላም ወደ ድሬዳዋ አስክሬኑ እንደሚሸኝም ተገልጿል።

በድሬዳዋ ስታዲየም የሽኝት መርሐ ግብር ከተካሄደ በኋላም የቀብር ሥነስርዓቱ በለገሀሬ የሙስሊም መቃብር እንደሚፈጸም ከወጣው መርሐ ግብር ማወቅ መቻሉን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa