Get Mystery Box with random crypto!

ዓለም ዓቀፍ የማዕድን እና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ሊካሄድ ነው! የማዕድን ሚኒስቴር ከመጪው ህዳር 1 | YeneTube

ዓለም ዓቀፍ የማዕድን እና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ሊካሄድ ነው!

የማዕድን ሚኒስቴር ከመጪው ህዳር 1 እስከ 3/2015 ዓ.ም የሚቆይ ዓለም ዓቀፍ የማዕድን እና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ያካሂዳል።የማዕድን ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ ኤክስፖውን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ዓለም ዓቀፍ የማዕድን እና ቴክኖሎጂ ኤክስፖው ኢትዮጵያ ያላትን ያልተነካ ሃብት በማስተዋወቅ ሀብቱን መጠቀም ያስችላል።

በማዕድን ዘርፍ የተሰማሩ የሀገር ውስጥ ባለ ሃብቶች ከውጭ ኩባንያዎች ጋር የገበያ ትስስር ይፈጥሩበታል ብለዋል ሚኒስትሩ።በኤክስፖው በሀገር ውስጥ የሚገኙና ከ90 በላይ የውጭ ኩባንያዎች በኤክስፖው ይሳተፋሉ።ዓለም ዓቀፍ የማዕድን እና ቴክኖሎጂ ኤክስፖው ሐሙስ ህዳር 01 ቀን በሚሊኒየም አዳራሽ ከፍተኛ ባለስልጣናት በዘርፉ የተሰማሩ አምራችና ሻጭ ኩባንያዎች በተገኙቀት ይከፈታል።

[Walta]
@YeneTube @FikerAssefa