የህወሓትና የፌደራል መንግስቱ የሰላም ንግግር እስከ ዕሮብ ተራዘመ! በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ | YeneTube

የህወሓትና የፌደራል መንግስቱ የሰላም ንግግር እስከ ዕሮብ ተራዘመ!

በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያን ጦርነት በሰላም ይፈታል ተብሎ የታመነበት የሰላም ንግግር እስከ ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. መራዘሙ ተሰማ።

ቢቢሲ ምንጮቼ ነገሩኝ ብሎ እንደዘገበው በድርድሩ ስለተነሱ ሃሳቦች ምንም ፍንጭ ማግኘት አልተቻልም ያለ ሲሆን እሮብ ሲጠናቀቅ የጋራ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስነብቧል።

ከአንድ ሳምንት በፊት ጥቅምት 14 ቀን 2015 ዓ.ም. በፌደራል መንግስት እና ህወሓት መካከል የሰላም ንግግር መጀመሩ ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa