Get Mystery Box with random crypto!

የሰሊጥ ሽያጭ በኩንታል እስከ 2,000 ብር መቀነሱ ተገለጸ! የሰሊጥ ገበያ ካለፈው ዓመት ጋር ሲ | YeneTube

የሰሊጥ ሽያጭ በኩንታል እስከ 2,000 ብር መቀነሱ ተገለጸ!

የሰሊጥ ገበያ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በኩንታል እስከ 2,000 ብር ድረስ መቀነሱን አምራች አርሶ አደሮች ገለጹ።

በአማራ ክልል ወልቃይት፣ መተማ፣ ሁመራ አርማጭሆ እና ቋራ አካባቢዎች ሰሊጥ የሚያመርቱ አርሶ አደሮች እንደተናገሩት፣ ዘንድሮ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ሰሊጥ እየተገበያዬ ያለው በኩንታል ከ8,000 እስከ 8,400 ብር ነው። ባለፈው ዓመት አንድ ኩንታል ሰሊጥ እስከ 10 ሺሕ ብር ይሸጥ እንደነበር ጠቅሰው፣ የዘንድሮው መሸጫ ዋጋ ግን የተመረተበትን ወጭ እንኳን እንደማይሸፍን ገልጸዋል።

በዘንድሮው ዓመት ለምርት ከፍተኛ ወጭ አውጥተናል ያሉት አርሶ አደሮቹ፣ የጉልበት ሠራተኛ ዋጋ ከባለፈው ዓመት አንጻር ከሶስት እጥፍ በላይ ጨምሯል፣ የሚታረሰውም በትራክተር በመሆኑ ለዚህ የምናወጣው ወጪ አምስት እጥፍ ነው የጨመረው ሲሉ ተደምጠዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa