YeneTube

የቴሌግራም ቻናል አርማ yenetube — YeneTube
ርዕሶች ከሰርጥ:
Marakischolarshipcenter
Artland
Event
Gaming
Chewatacon
Shegerhive
Chewata
Addisababaethiopia
Yenetube
Artland
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @yenetube
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 129.20K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-11-30 11:15:42
የታጠቁ ኃይሎች በሰላም አፈላላጊዎች ጥረት ወደ ምክክር ሊመጡ እንደሚችሉ ተገለጸ!

የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የታጠቁ ኃይሎች በሰላም አፈላላጊዎች ጥረት ወደ ምክክር ሊመጡ እንደሚችሉ አስታወቀ።ኮሚሽኑ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ያከናወናቸውን የሥራ አፈጻጸሞች አስመልክቶ ትናንት ኀዳር 21/2015 መግለጫ ሰጥቷል፡፡በመግለጫውም የታጠቁ ኃይሎችን ወደ ምክክሩ ለማምጣት መንግሥት የሚሰራው ሥራ አለ ያለ ሲሆን፤ የታጣቁ ኃይሎች በመንግሥት በኩል በሚሰሩ ሥራዎች፣ በሰላም አፈላላጊዎች እንዲሁም በአገር ሽማግሌዎች ጥረት ወደ ምክክሩ ይመጣሉ የሚል እምነት እንዳለው አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ በመገባደድ ላይ በሚገኘው በዚህ ወር ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቀውን ምክክር አራዝሟል፡፡ ኮሚሽኑ የምክክር አጀንዳዎችን ከሕዝብ ሰብስቦ ከቀረጸ በኋላ፣ በ2015 አጋማሽ ምክክር እንደሚጀመር የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ጠቁመዋል፡፡ በምክክሩ ሂደቱ ማንኛውም የማኅበረሰብ ክፍል ሳይወከል እንዳይቀር ኮሚሽኑ አበርክሮ እንደሚሰራም ጠቁሟል፡፡የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክክሩን አካታች የማድረግ ኃላፊነት በአዋጅ የተሰጠው ሲሆን፣ የታጠቁ ኃይሎች በአገራዊ ምክክሩ ሊሳተፉ የሚችሉት ትጥቅ ፈተው ወደ ውይይት ከመጡ ነው የሚል አቋም አለው፡፡

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
3.6K views08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-30 10:39:18
በስልጤ ዞን በተደረገ ድንተኛ ፍተሻ ከ450 በላይ የሺሻ ማጨሻ እቃዎች ተወገዱ !!

በጉዳዩ ላይ የተሳተፉ አካላት ጉዳያቸው በህግ ተይዟል !!

በሰልጤ ዞን ሚቶ ወረዳ በ5 ዙር በተደረገው ድንገተኛ የቤት ለቤት ፍተሻ 450 የሚሆኑ የሺሻ ማጨሻ እቃዎች እንደተወገዱ ብስራት ሰምቷል።

ሰባት በሚሆኑ ህገ ወጥ ማስጨሻ ስፍራዎች ላይ በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ እቃዎቹ ከመያዛቸው በተጨማሪ በጉዳዩ የተጠረጠሩ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ አቶ ጌታሁን ተከተል ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

ማስጨሻ እቃዎቹ በገበያ ስፍራ መሀል እንዲቃጠሉ መደረጋቸው ማህበረሰቡን ለማስተማር ሲባል የተወሰደ እርምጃ ነው።

መሰል ህገ ወጥ ተግራባት በወረዳው መበራከቱን ያነሱት አቶ ጌታሁን በዋነኛነት ወጣቱ የዚህ ሰለባ እየሆነ ይገኛል ሲሉ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።Via: ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
4.5K viewsedited  07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-30 10:37:55
የስራ ጉዞ ወደ # moldova
የሚሰራበት አገር - moldova
የስራ ቀናት - 6 ቀናት/ week
የስራ ሰዓት - ከ8- 10hr/day
የስራዉ ዓይነት ፋብሪካ ዉስጥ ስራዎች
የወር ደሞዝ - €500-700 and more
ፆታ - ወንድ እና ሴት
ዕድሜ - 20 እስከ 45
መኖሪያ ቤት - በነፃ
ምሳ - በነፃ
OT - ይቻላል
ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ ከ በ 1 ወር ነው

#Requirements

Passport
2 photographs
በቀላሉ ከሰዎች ለመማር ዝግጁ የሆነ
በጋራ ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ

#Urgent
የምንፈልገው የአመልካች ብዛት 50

Contact:
@Sabinavisa
@Sabinavisa2
@Sabinascholar

+251118683939
0930550011
0930552233
0936363639

ለበለጠ መረጃ

ወደ ቢሮአችን ይምጡ !
ሃያ ሁለት የአብ ሕንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር እና 507 እና 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር  702

https://t.me/sabinaadvisor

www.sabinaadvisors.com

https://www.facebook.com/sabinaadvisor

ከታላቅ አክብሮት ጋር   !!!
1.2K views07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-30 10:37:55
መፍትሔ ስራይ ወአይነጥላ
መሪጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ማእከል
የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድለኒቾች ፍቱን ህክምናወችን
እንሰጣለን ።
ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ባለበት ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስቆም ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
በሌሊት ለሚሸና
ለነገረ በትን
ሆዱን ለሚያመው
ለስኳር ህመም መቀነሻ
ለሁሉም ቁርጥማት
ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
ለማንኛውም ቁስል ማድረቂያ
ለፊት ማድያት
ለሳል በሽታ
ለግርማሞገስ ለህዝብ መስተፋቅር
ለማህጸን እንፌክሽን
ለአእምሮ ጭንቀት
ለወገብ ህመም
ለነርብ
ለራስ ህመም
ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
ፍቅረኛ ላጣ
የሚጥል በሽታ
ገንዘብ ለሚበተንበት
ስራ አልሳካለት ላለ
ገብያ ለሚገረግረው ለገብያ
ለመፍትሔ ስራይ
ለአይነጥላ ለገርጋሪ
ለስንፈተወሲብ ሲገናኝ ለሚቸኩልበት
ለአስም (ሳይነስ)

እንዲሁም የተለያዩ
መድኀኒቶቻችን እንቀምማለን

እኛ ጋር ለሚአገኙት ማንኛውም አይነት
አገልግሎቶቻችን ውጤት እንዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ።
እነዚህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን
መድሀኒቱን ባሉበት መላላክ ይቻላል

ለበለጠ መረጃ አድራሻ ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በኮብሉ መጨረሻ ንግድ ባንኩ ላይ።

ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አደይ አበባ

ይደውሉ
0917040506
0912718883


https://t.me/mergatah
አድራሻ :- ባህርዳር የሚለውን

ቻናሉን በመቀላቀል
ሊንኳን በመጫን ጤናወ በቤትወ የእጽዋት የህቡ ስም የጠልሰም ጥቅሞችን ይጋሩ ይፈወሱ
1.2K views07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-30 10:37:46
Dave Security Camera

ምን ይፈልጋሉ የቴክኖሎጂ አይነት እና የሴኩሪቲ እቃዎችን ከዴቭ የደህነት ካሜራዎች ጥራታቸውን የጠበቁ  ዘመናዊ እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ጋር ማግኘት ይችላሉ።

መኖሪያ ቤትዎን እና የስራ ቦታዎን ከስርቆት ይከላከላሉ  የደህንነት ካሜራ ያስገጥሙ
25% ቅናሽ

ለሱቅ
ለፋርማሲ
ለቡቲክ
ለፋብሪካ
ለባንክ
ለሬስቶራንት
ለመኖሪያ ቤት

የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል የምናስመጣቸውን አዳዲስ እቃዎችን ማየት ይችላሉ

https://t.me/Dawitengineering

አድራሻችን
መገናኛ 3M City Mall
+251920757958

inbox :- @Dawit7579
3.7K views07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 21:51:45
በጅቡቲ ከኢንተርኔት መቋረጥ ጋር ተያይዞ የኢትዮ ሳት ቻናሎች ስርጭት ተቋርጧል!

በጅቡቲ ከኢንተርኔት መቋረጥ ጋር ተያይዞ የኢትዮ ሳት ቻናሎች ስርጭት መቋረጡን ኤስ ኢ ኤስ ኢትዮጵያ አስታወቀ፡፡የኢንተርኔት መቋረጡ ሁሉንም አገልግሎቶች አስተጓጉሏል ያሉት የተቋሙ የምሰራቅ አፍሪካ ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ መነን አገኘሁ ችግሩን ለመፍታት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡እስካሁን ባለው ሂደትም አንዳንድ አገልግሎቶችን መመለስ ተችሏል ያሉት ኋላፊዋ፣ ሁሉንም አገልግሎቶች ወደነበሩበት ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አሳውቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
10.1K views18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 20:47:19 የተሽከርካሪ ነጋዴዎች “አጠራጣሪ ግብይቶች” ሲያጋጥሟቸው፤ ለፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት እንዲያሳውቁ የሚያስገድድ መመሪያ ተዘጋጀ!

የባለሞተር ተሽከርካሪ ነጋዴዎች የደንበኞቻቸውን ማንነት ለመለየትና ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የአሰራር ስርዓቶችን እንዲያዘጋጁ እና አጠራጣሪ ግብይቶች ሲያጋጥሟቸው ለፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ተቋም ሪፖርት እንዲደርጉ የሚያዝ መመሪያ ተዘጋጀ። በመመሪያው መሰረት፤ የተሽከርካሪ ነጋዴዎች ስለደንበኞቻቸው የሰበሰቧቸውን መረጃዎች ለ10 ዓመታት የማከማቸት ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

በፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ተቋም የተዘጋጀው ይህ መመሪያ፤ “በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ወይም ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብንና ሽብርተኝነት በገንዘብ መርዳትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር” በ2008 ዓ.ም. የወጣውን አዋጅ መሰረት አድርጎ ነው። መንግስታዊው ተቋም መመሪያውን ያወጣው፤ “የባለሞተር ተሽከርካሪዎች” ግዢን በመጠቀም በአዋጁ የተጠቀሱ ወንጀሎች እንዳይፈጸሙ ለመከላከል መሆኑን በአገልግሎቱ የሱፐርቪዥን ቡድን መሪ የሆኑት ሙሉጌታ ተመስገን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

መመሪያው “የባለሞተር ተሽከርካሪዎች” በሚል ምድብ ውስጥ የሚያስቀምጣቸው፤ የግል አውቶሞቢል፣ የሕዝብ ማመላለሻ፣ የጭነት ማመላለሻ፣ ጎታች መኪና፣ ባለሞተር ብስክሌት እና ልዩ ተንቀሳቃሽ መሳሪያዎችን ነው። እነዚህ ተሽከርካሪዎች በመካኒካል ወይም በኤሌክትሪክ ኃይል የሚንቀሳቀኑ ሊሆኑ እንደሚችሉ በመመሪያው ሰፍሯል። አዲሱ መመሪያ የሚመለከታቸው “የተሽከርካሪ ነጋዴዎች”፤ የባለሞተር ተሽከርካሪዎችን የሚያመርቱ፣ ከውጭ ሀገራት የሚያስመጡ፣ ወደ ውጭ ሀገራት የሚልኩ፣ የሚያከፋፍሉ፣ የሚቸረችሩ፣ የሚያከራዩ፣ ለሽያጭ የሚደለድሉ እና ከዘርፉ ጋር ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦች መሆናቸው በመመሪያው ተቀምጧል። በ2008 ዓ.ም. የወጣው አዋጅ መሰረት፤ የተሽከርካሪ ነጋዴዎች “ፋይናንስ ነክ ያልሆኑ፤ የተሰየሙ የንግድ እና የሙያ ስራዎች” ዘርፍ ውስጥ የሚወድቁ ናቸው።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
11.3K views17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 18:12:02
የኮዬ ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ጥያቄ በህዳር ወር መጨረሻ ምላሽ ያገኛል ተባለ

ኮዬ ፈጬ 2 ተብሎ በሚጠራው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለባለ እድለኞች ከተላለፉ በኃላ ኑሯቸውን በእዚያ ያደረጉ ነዋሪዎች ለከፍተኛ ችግር ተዳርገናል ሲሉ ለብስራት ሬዲዮ ቅሬታቸውን ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

ነዋሪዎቹ የቤት ባለ እድል መሆናቸውን ካረጋገጡ በኋላ ያለው የኤሌክትሪክ ችግር እስከ መስከረም ወር ይፈታላችኋል ቢባሉም ችግሩ ዛሬም ድረስ ሳይቀረፍ እንደቀረ ይገልጻሉ፡፡

ጉዳዩን በሚመለከት ብስራት ሬድዮ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፤ የአዲስ አበባ ኮንዶሚኒዬም ኤሌክትሪፍኬሽን ፕሮጀክት ኃላፊ አቶ ሰለሞን አበራ የነዋሪዎቹን ቅሬታ ትክክለኛ መሆኑን በማንሳት ችግሩ እስከ ህዳር ወር መጨረሻ ድረስ ይቋጫል ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

ስፍራው ከፍተኛ የተባለ ግንባታ የሚከናወንበት በመሆኑ ለመስመር ዝርጋታ አዳጋች አድርጎብናል ያሉት ኃላፊው ፤ የተቋራጮቾች የግንባታ መጓተት ሌላኛው ችግር እንደነበር ጠቁመዋል፡፡

ለስፍራው 22 የሚሆኑ ትራንስፎርመሮች እንደሚያስፈልጉ የተናገሩት አቶ ሰለሞን እስከ አሁን ባለው ሂደት 11 ትራንስፎርመሮችን ተከላ አጠናቀናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ከእዚህ ባለፈ 788 ገደማ ህንፃዎችን የያዘ ሰፊ አካባቢ በመሆኑ ግንባታው በአፋጣኝ እንዳይጠናቀቅ አድርጓል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

እስከ ህዳር ወር መጨረሻ ድረስ ስራውን በማጠናቀቅ የነዋሪዎቹን ቅሬታ ለመቅረፍ እንሞክራለን ያሉት ሓላፊው ይህንኑ እቅድ ለተቋራጩ በማስረዳት ወደ ተግባር ገብተናል ነዋሪዎቹ በትዕግስት ሊጠብቁን ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Via:- ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
13.2K views15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 15:26:09 የአዲስ አበባ ፖሊስ 16 የእጅ ቦንብ፣ 9 ሽጉጥ እና 83 የተለያዩ የሽጉጥ ጥይቶችን ከ11 ተጠርጣሪዎች ጋር በመያዝ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ አስታወቀ!

በመዲናዋ አዲስ አበባ ከሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ በርካታ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር እየዋሉ እንደሚገኙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ፖሊስ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በጦር መሳሪያ ዝውውር በተጠረጠሩ ግለሰቦች መኖሪያ ቤት በተደረገ ብርበራ 9 ሽጉጦች እና በተሽከርካሪ ውስጥ ተደብቆ ሲጓጓዝ የነበረ 16 ቦንብ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር ከነተጠርጣሪዎቹ ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 እና 14  ከሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ጋር በተያያዘ 4 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራ እነደሚገኝ ያስታውቋል ፖሊስ፤ ሕብረተሰቡ በሰጠው ጥቆማ እና በፖሊስ  ክትትል በተጠቀሱት ወረዳዎች ነዋሪ በሆኑ እና በወንጀሉ በተጠረጠሩ 2 ግለሰቦች መኖሪያ ቤት በተደረገ ብርበራ 5 የተለያዩ ሽጉጦች  እና 53 ልዩ ልዩ የሽጉጥ ጥይቶች መያዛቸውን አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ሚኪሊላንድ ኮንደሚኒየም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ የጋራ መኖሪያ ቤት ውስጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረጉት ክትትል 4 ሽጉጥ ከ30 መሰል ጥይት እና 1 የእጅ ቦንብ  በብርበራ መያዙ ተገልጿል፡፡ በዚህ ወንጀል የተጠረጠሩ 4 ግለሰቦችም በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 በተለምዶ ፊናንስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረጉት ክትትል የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 5-01928 አ.አ በሆነ ፒካፕ ተሽከርካሪ አካል ውስጥ ተደብቆ ሲጓጓዝ የነበረ 15 የእጅ ቦንብ ከ3 ተጠርጣሪዎች ጋር  በቁጥጥር ሥር ውሏል።

በአጠቃላይ 16 የእጅ ቦንብ፣ 9 ሽጉጥ እና 83 የተለያዩ የሽጉጥ ጥይቶችን ከ11 ተጠርጣሪዎች ጋር ይዞ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ በሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ላይ የሚያደርገውን ክትትል እና ቁጥጥር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።ሕብረተሰቡም አሁንም አካባቢውን ከፀረ ሰላም ሃይሎች በንቃት እንዲጠብቅ እና ጥቆማና መረጃ በመስጠት ለፀጥታ አካላት እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
4.5K views12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 11:50:08
ሶማሊያ፡ ሆቴል ከበው ሰዎችን አግተው የነበሩት የአልሸባብ ታጣቂዎችን በመጨረሻም በወታደሮች ተገለው እገታው አብቅቷል

ሞቃዲሾ በሚገኘው ቪላ ሮዝ ሆቴል ላይ አማፂያን ከከበቡ በኋላ 9 ሰዎች - 8 ሲቪሎች እና አንድ ወታደር ተገድለዋል።

ለ12 ሰአታት 60 ንፁሀን ዜጎች ስልሳ ንፁሃን በታጣቂዎች ከመገደል ድነዋል ።

Via:- ሮይተርስ
@Yenetube @Fikerassefa
8.2K viewsedited  08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ