Get Mystery Box with random crypto!

የጋዜጠኞቹ የችሎት ውሎ ******************* ፍ/ቤቱ በጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድና ጎበዜ ሲሳ | Yalelet Wondye Gebeyehu

የጋዜጠኞቹ የችሎት ውሎ
*******************
ፍ/ቤቱ በጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድና ጎበዜ ሲሳይ እና አሳዬ ደርቤ ላይ ተጨማሪ ቀጠሮ ሰጠ።

ዛሬ መስከረም 16/2015 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀረቡት ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድና ጎበዜ ሲሳይ ለቀጣዩ አርብ መስከረም 20/2015 ዓ.ም ተቀጥረዋል፡፡
ጋዜጠኞቹ ለአርብ የተቀጠሩት ዓቃቤ ህግ በባለፈው ችሎት በተሰጠው የአምስት ቀን የጊዜ ቀጠሮ ውስጥ“ መረጃ ሰብስቤ ስላልጨረስኩ ክስ መመስረት አልቻልኩም ፣ ስለዚህ ተጨማሪ ቀን ይሰጠኝ” ማለቱን ተከትሎ ነው፡፡

አቃቤ ህግ ይህንን ያለው” በመሃል ቅዳሜና እሁድ ስለነበር ግዜ አጥሮኛል፣ በዚህም ያልተመለከትኳቸው የቪዲዮ ማስረጃዎች አሉ” በማለት እንደሆነ የጋዜጠኞቹ ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ለሮሃ ቲቪ ተናግረዋል፡፡

የጋዜጠኞቹ ጠበቆች ይህንን የአቃቤ ህግ ጥያቄ በመቃውም መከራከራቸውን የገለጹት አቶ ሄኖክ ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በኋላ ለመስከረም 20/2015 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በተያያዘ አሳዬ ደርቤ ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን መርማሪ ፓሊስ የምርመራ ጊዜዬን ጨርሻለው ክስ ለመመስረት ጊዜ ይሰጠኝ ባለው መሰረት ለዓርብ 20/1/2015 ተቀጥሯል!!