Get Mystery Box with random crypto!

ትህነግ/ህወሓትን ከ4 ኪሎ ቤተመንግስት ያስባረረው የአማራ ህዝብ ቁልፍ ጥያቄዎች ምን ምን ነበሩ? | Yalelet Wondye Gebeyehu

ትህነግ/ህወሓትን ከ4 ኪሎ ቤተመንግስት ያስባረረው የአማራ ህዝብ ቁልፍ ጥያቄዎች ምን ምን ነበሩ?

ዋና ዋናዎቹን ለማስታወስ ያህል፤

~ የህገ-መንግስት ማሻሻያ ፣
~ የተዛባ የታሪክ ትርክት፣
~ የወሰንና የማንነት ጉዳይ፣
~ የህዝብ ቁጥር (የተዛባ የህዝብ አቆጣጠር)፣
~ የሰላምና ደህንነት (በህዝብ ላይ የሚፈጸም ማንነት ተኮር ጥቃትን ማስቆም)፣
~ የአዲስ አበባ ጉዳይ፣
~ ፍትሀዊ የፓለቲካ ውክልና ፣
~ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል (የኑሮ ውድነት ማቃለል) ወዘተ ናቸው::

ትህነግ/ህወሓት ከ4 ኪሎ ቤተመንግስት ከተባረረ 4 ዓመት ሆነው:: ከላይ የተዘረዘሩት ውስጥ አንዱም እስከአሁን አልተፈታም!! እንደውም ተባብሰው የቀጠሉ ችግሮች ውስጥ እንገኛለን::

ችግሮቹም ተባብሰው የቀጠሉበት ሁኔታም እንደሚከተለው ነው!!

~ ሱዳን በአልፋሽጋ በኩል የጎንደርን መሬት ከ60 ኪሎሜትር በላይ ወረራ ፈጽማለች።

~ ትህነግ/ህውሓት በህዝብ ትግል ከህዝብ ጫንቃ ላይ ወርዶ ከ4 ኪሎ ከተባረረ በኋላ ነፍጥ አንስቶ ጦርነት ከፍቶብናል፣ በዚህም የተነሳ አማራ ክልል 288 ቢሊዮን ብር የሚገመት ውድመት አስተናግዷል፣ በሺዎች የሚቆጠሩ አማራዎች ውድ ህይወታቸው አጥተው ከ13ሺህ በላይ ህጻናት ወላጅ አልባ ሲሆኑ በርካታ አዛውንቶችም ያለጧሪ ቀርተዋል፣ በጦርነቱ የተፈናቀሉ አማራዎች በየመጠለያው የስቃይ ኑሮ እየገፉ ነው።

~ ኦነግን የአማራ ህዝብን ከመጨፍጨፍና ከማፈናቀል የሚያስቆመው አልተገኝም፣ ከኦሮሚያ እና ከቤኒሻንጉል ከሞት የተረፉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አማራዎች በየመጠለያው የስቃይ ኑሮ እየገፉ ነው።

~ የጉሙዝ እና የቅማንት ታጣቂ ጊዜ የሚጠብቁ ናቸው።

~ የኑሮ ውድነት፣ ድህነት እና ዝርፊያ (የሙስና ወንጀል ) ከምንግዜውም በከፋ ሁኔታ ተባብሶ ቀጥሏል።

ታዲያ ብልጽግና ወይም ለውጡ ለአማራ ህዝብ ምን ለውጥ ፈጠረለት? ምንም!!

ይህ ሁሉ ችግር ያለበት ህዝብ አካል የሆኑት የአማራ ሊሂቃን እስካሁን በጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ናቸው::

ሲሳይ አውግቸው ወንድምተገኝ እንዳስታወሰን!