Get Mystery Box with random crypto!

በዘመነ ካሴ መታሰር ብዙም አትናደዱ! የታቀደለት ሞት ነበረና። ዘመነ ካሴ ታሰረም አልታሰረም ለው | Yalelet Wondye Gebeyehu

በዘመነ ካሴ መታሰር ብዙም አትናደዱ! የታቀደለት ሞት ነበረና።
ዘመነ ካሴ ታሰረም አልታሰረም ለውጥ የለውም። ይልቁንም ዘመነ ካሴን የ "ይገደል" ዘመቻ የጀመሩ ሰዎችን/ቡድን ያሳፈረ ነው። ትላንት ጀግናው አሳምነው ፅጌን አስገድለን በብዙ ተጎድተናል።
ዛሬም ዘመነ ካሴ ባለመገደሉ ደስ ሊለን ይገባል። በመታሰሩ የምናጣው ጥቂት የምናተርፈው ብዙ ነውና።

ችግሩ ግን በዘመነ መታሰር አማራን ከፋፍሎ መጠቀም የሚፈልግ 3ኛ ወገን መኖሩ ነው፤ (ለዚህ ተግባርም ብዙ አማራዎች ተሳታፊ እንደሆኑ እናውቃለን)።
ስለዚህ እንረጋጋ!
አማራ ክልል በተለይም ባህር ዳር ከተማ ውስጥ በፍፁም ሰላም አናደፈርስም። ዘመነ በታሰረበት ፖሊስ ጣቢየም መረበሽ የለብንም። ብልጽግና በባህር ዳር ብዙ ቀይ ለባሾችን ማሰማራቱም የታሰበልልን የሚያሳይ ነው።
ትግላችን ስልታዊ እና የተገመገመ ይሁን። ትላንት ሰሜን ላይ በጦርነት ማግደው መሃል አገር ምን እየሰሩ እንደነበር እናውቃለን። የቅርብ ግዜው እንኳን እነሱ በ 10 ሺዎች ጄኔሌተር ለአርሶ አደራቸው ሲያከፈፍሉ ለእኛ የእህል ጣሳ አሰራጩልን፣ የግዕዝን ፊደል ለ Greece በመስጠት፣ በላይ ዘለቀን ማወረም፣ ወዘተ።
..
ሌላው ባህር ዳር ላይ ዘመነን ለማስለቀቅ የምናደርጋቸው ሙከራዎች ሁሉ እንደ ምክንያት ተቆጥረው ዘመነ ካሴን ወደ አዲስ አበባ ለመውሰድ እንደሚያስቡ መገንዘብ አለብን።

በአጭሩ ዋናው ነገር የዘመነ ካሴ በህይወት መኖር ነው።

#ነገር_ግን አርበኛ ዘመነ ካሴን ወደ አዲስ አበባ ለመላክ መሞከር ትልቅ ዋጋ እንደሚያስከፍል መገንዘብ ተገቢ ነው። የአማራ ክልል ፖሊስ ዛሬ ካወጣው መግለጫ አፈንግጦ ወደ አዲስ አበባ አሳልፎ እንደማይሰጠው ተስፋ አደርጋለሁ።

የእንዳላማው ክንዴ ሃሳብና አቋም የኔም ሃሳብና አቋም ነው።