Get Mystery Box with random crypto!

Yalelet Wondye Gebeyehu

የቴሌግራም ቻናል አርማ yaleletwondyegebeyehu — Yalelet Wondye Gebeyehu Y
የቴሌግራም ቻናል አርማ yaleletwondyegebeyehu — Yalelet Wondye Gebeyehu
የሰርጥ አድራሻ: @yaleletwondyegebeyehu
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.00K

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-26 21:26:26
እንኳን ለመስቀል በዓል አደረሳችሁ!
ፈጣሪ ታርቆን አገራችንን ሰላም እንዲያደርግልን እመኛለሁ!
1.4K views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 14:58:58
የጋዜጠኞቹ የችሎት ውሎ
*******************
ፍ/ቤቱ በጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድና ጎበዜ ሲሳይ እና አሳዬ ደርቤ ላይ ተጨማሪ ቀጠሮ ሰጠ።

ዛሬ መስከረም 16/2015 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀረቡት ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድና ጎበዜ ሲሳይ ለቀጣዩ አርብ መስከረም 20/2015 ዓ.ም ተቀጥረዋል፡፡
ጋዜጠኞቹ ለአርብ የተቀጠሩት ዓቃቤ ህግ በባለፈው ችሎት በተሰጠው የአምስት ቀን የጊዜ ቀጠሮ ውስጥ“ መረጃ ሰብስቤ ስላልጨረስኩ ክስ መመስረት አልቻልኩም ፣ ስለዚህ ተጨማሪ ቀን ይሰጠኝ” ማለቱን ተከትሎ ነው፡፡

አቃቤ ህግ ይህንን ያለው” በመሃል ቅዳሜና እሁድ ስለነበር ግዜ አጥሮኛል፣ በዚህም ያልተመለከትኳቸው የቪዲዮ ማስረጃዎች አሉ” በማለት እንደሆነ የጋዜጠኞቹ ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ለሮሃ ቲቪ ተናግረዋል፡፡

የጋዜጠኞቹ ጠበቆች ይህንን የአቃቤ ህግ ጥያቄ በመቃውም መከራከራቸውን የገለጹት አቶ ሄኖክ ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በኋላ ለመስከረም 20/2015 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በተያያዘ አሳዬ ደርቤ ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን መርማሪ ፓሊስ የምርመራ ጊዜዬን ጨርሻለው ክስ ለመመስረት ጊዜ ይሰጠኝ ባለው መሰረት ለዓርብ 20/1/2015 ተቀጥሯል!!
2.3K views11:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 13:55:00 ትህነግ/ህወሓትን ከ4 ኪሎ ቤተመንግስት ያስባረረው የአማራ ህዝብ ቁልፍ ጥያቄዎች ምን ምን ነበሩ?

ዋና ዋናዎቹን ለማስታወስ ያህል፤

~ የህገ-መንግስት ማሻሻያ ፣
~ የተዛባ የታሪክ ትርክት፣
~ የወሰንና የማንነት ጉዳይ፣
~ የህዝብ ቁጥር (የተዛባ የህዝብ አቆጣጠር)፣
~ የሰላምና ደህንነት (በህዝብ ላይ የሚፈጸም ማንነት ተኮር ጥቃትን ማስቆም)፣
~ የአዲስ አበባ ጉዳይ፣
~ ፍትሀዊ የፓለቲካ ውክልና ፣
~ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል (የኑሮ ውድነት ማቃለል) ወዘተ ናቸው::

ትህነግ/ህወሓት ከ4 ኪሎ ቤተመንግስት ከተባረረ 4 ዓመት ሆነው:: ከላይ የተዘረዘሩት ውስጥ አንዱም እስከአሁን አልተፈታም!! እንደውም ተባብሰው የቀጠሉ ችግሮች ውስጥ እንገኛለን::

ችግሮቹም ተባብሰው የቀጠሉበት ሁኔታም እንደሚከተለው ነው!!

~ ሱዳን በአልፋሽጋ በኩል የጎንደርን መሬት ከ60 ኪሎሜትር በላይ ወረራ ፈጽማለች።

~ ትህነግ/ህውሓት በህዝብ ትግል ከህዝብ ጫንቃ ላይ ወርዶ ከ4 ኪሎ ከተባረረ በኋላ ነፍጥ አንስቶ ጦርነት ከፍቶብናል፣ በዚህም የተነሳ አማራ ክልል 288 ቢሊዮን ብር የሚገመት ውድመት አስተናግዷል፣ በሺዎች የሚቆጠሩ አማራዎች ውድ ህይወታቸው አጥተው ከ13ሺህ በላይ ህጻናት ወላጅ አልባ ሲሆኑ በርካታ አዛውንቶችም ያለጧሪ ቀርተዋል፣ በጦርነቱ የተፈናቀሉ አማራዎች በየመጠለያው የስቃይ ኑሮ እየገፉ ነው።

~ ኦነግን የአማራ ህዝብን ከመጨፍጨፍና ከማፈናቀል የሚያስቆመው አልተገኝም፣ ከኦሮሚያ እና ከቤኒሻንጉል ከሞት የተረፉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አማራዎች በየመጠለያው የስቃይ ኑሮ እየገፉ ነው።

~ የጉሙዝ እና የቅማንት ታጣቂ ጊዜ የሚጠብቁ ናቸው።

~ የኑሮ ውድነት፣ ድህነት እና ዝርፊያ (የሙስና ወንጀል ) ከምንግዜውም በከፋ ሁኔታ ተባብሶ ቀጥሏል።

ታዲያ ብልጽግና ወይም ለውጡ ለአማራ ህዝብ ምን ለውጥ ፈጠረለት? ምንም!!

ይህ ሁሉ ችግር ያለበት ህዝብ አካል የሆኑት የአማራ ሊሂቃን እስካሁን በጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ናቸው::

ሲሳይ አውግቸው ወንድምተገኝ እንዳስታወሰን!
2.7K viewsedited  10:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 21:07:02
የወሎ ሽለላ እና ፉከራ !

ጎጃም ሀሳብ ገባው ከሳ መነመ፤
በፊት በእነ በላይ አሁን በዘመነ።
    
ያ ዘመነ ካሴ አንድ ሰው ሁኖብኝ፤
እሱን የማይበት አይኔ ደከመብኝ።

እናቱ መነኩሴ ዘወትር አስቀዳሽ፤
ልጅየው አርበኛ የተማረ ተኳሽ።
2.2K views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 21:17:49 "ውሻህ አንተ ላይ መጮህ ሲጀምር ሌላ ሰው እየመገበው እንደሆነ ተረዳ"
1.9K views18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 21:04:19
ጎጃም ጎንደር ወሎ ሽዋ ጉልላቱ
በጥቅሻ ሚግባባ አንድ ነዉ አንገቱ
አንድ ኢትዮጵያ ማለት ነዉር ከሆነማ
ነዉር ይሁንብኝ ማነንም አልሰማ
ነፃነት ነዉ እንጅ ልብ አይታሰርም
ለጊዜዉ ቢያናቅፍ ገል ብረት አይሰበርም
የድሮ ናፋቂዉ ቀድሞ የዘመነዉ
ጥንትም ፋኖ ነበር ዛሬም ያሳምነዉ
ጥቁሬ ነኝ የዘሜ ወንድም

@ ዳኘ ዋለ (የጨነቀለት)
3.4K views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 21:29:19
የውሻ ቀዳዳ እየከፈቱ የቀን ጅብን ከሚያስገቡ አደረጃጀቶች እራሳችሁን ጠብቁ። የአዛኝ ቅቤ አንጓቾች መቀለጃ ሆነን እስከመቼ ነው የምንቀጥለው?
4.3K views18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 20:52:12 አፄ ቴዎድሮስን ያስበላ የባንዳ ቅሪት በዚህ ዘመን መኖሩን ሳይ ማመን አቃተኝ
እግዚኦ
4.6K views17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 20:15:22
በአንድ ዘመነ ካሴ እረፍት ያጣችው ሀገር ይሄን ሁሉ ጉድ ተሸክማ እንደምትኖር እናውቃለን!
6.0K viewsedited  17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 16:16:07
በዘመነ ካሴ መታሰር ብዙም አትናደዱ! የታቀደለት ሞት ነበረና።
ዘመነ ካሴ ታሰረም አልታሰረም ለውጥ የለውም። ይልቁንም ዘመነ ካሴን የ "ይገደል" ዘመቻ የጀመሩ ሰዎችን/ቡድን ያሳፈረ ነው። ትላንት ጀግናው አሳምነው ፅጌን አስገድለን በብዙ ተጎድተናል።
ዛሬም ዘመነ ካሴ ባለመገደሉ ደስ ሊለን ይገባል። በመታሰሩ የምናጣው ጥቂት የምናተርፈው ብዙ ነውና።

ችግሩ ግን በዘመነ መታሰር አማራን ከፋፍሎ መጠቀም የሚፈልግ 3ኛ ወገን መኖሩ ነው፤ (ለዚህ ተግባርም ብዙ አማራዎች ተሳታፊ እንደሆኑ እናውቃለን)።
ስለዚህ እንረጋጋ!
አማራ ክልል በተለይም ባህር ዳር ከተማ ውስጥ በፍፁም ሰላም አናደፈርስም። ዘመነ በታሰረበት ፖሊስ ጣቢየም መረበሽ የለብንም። ብልጽግና በባህር ዳር ብዙ ቀይ ለባሾችን ማሰማራቱም የታሰበልልን የሚያሳይ ነው።
ትግላችን ስልታዊ እና የተገመገመ ይሁን። ትላንት ሰሜን ላይ በጦርነት ማግደው መሃል አገር ምን እየሰሩ እንደነበር እናውቃለን። የቅርብ ግዜው እንኳን እነሱ በ 10 ሺዎች ጄኔሌተር ለአርሶ አደራቸው ሲያከፈፍሉ ለእኛ የእህል ጣሳ አሰራጩልን፣ የግዕዝን ፊደል ለ Greece በመስጠት፣ በላይ ዘለቀን ማወረም፣ ወዘተ።
..
ሌላው ባህር ዳር ላይ ዘመነን ለማስለቀቅ የምናደርጋቸው ሙከራዎች ሁሉ እንደ ምክንያት ተቆጥረው ዘመነ ካሴን ወደ አዲስ አበባ ለመውሰድ እንደሚያስቡ መገንዘብ አለብን።

በአጭሩ ዋናው ነገር የዘመነ ካሴ በህይወት መኖር ነው።

#ነገር_ግን አርበኛ ዘመነ ካሴን ወደ አዲስ አበባ ለመላክ መሞከር ትልቅ ዋጋ እንደሚያስከፍል መገንዘብ ተገቢ ነው። የአማራ ክልል ፖሊስ ዛሬ ካወጣው መግለጫ አፈንግጦ ወደ አዲስ አበባ አሳልፎ እንደማይሰጠው ተስፋ አደርጋለሁ።

የእንዳላማው ክንዴ ሃሳብና አቋም የኔም ሃሳብና አቋም ነው።
4.5K views13:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ