Get Mystery Box with random crypto!

#ሼር_ፖስት! አማርኛ ቋንቋ እንደሆነ የራሡ የሆነ ሥርዓተ ድህፈት (Orthography) ያለው፣ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

#ሼር_ፖስት! አማርኛ ቋንቋ እንደሆነ የራሡ የሆነ ሥርዓተ ድህፈት (Orthography) ያለው፣ ከፍተኛ የሆነ የሰዋሠው (Grammar) እና የሥነ-ልሣን (Linguistics) ጥናትና ምርምር የተደረገበት፣ በአፍሪካ ምድር በስነ ጽሁፍ ሀብት የበለጸገ ብቸኛውና ነባር ዓለምአቀፍ ቋንቋ ነው።

ከትግራይ ሥርዓተ ትምህርት ብታስወግደው በ2007 ዓ.ም.የአፕል የቴክኖሎጂ ማዕከል አማርኛን ከዓለም ግዙፍ ቋንቋዎች ተርታ መድቦ የቴክኖሎጂ ቋንቋ አድርጎታል።

አማርኛን ከትግራይ ብትፍቀው በ2008 ዓ.ም. የጎግል የቴክኖሎጂ ማዕከል የመተርጎሚያ ቋንቋ አድርጎታል።

እንዲያው አዲስ የጫጉላ ሽርሽር ሆናባችሁ እንጂ አማርኛ በUS አሜሪካ የመንግስት ቋንቋም ነው። በአሜሪካዋ ቨርጂኒያ ግዛት አሌክሳንድሪያ ዳሽ የሚባለው የከተማ አውቶቢስ ላይ "እንኳን ወደ #WESTEND በደህና መጣችሁ!" የሚል ጽሁፍ ማየትም የተለመደ ነው።

Dstv'ም የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፣ የኦሊምፒክ ውድድሮችን ጨምሮ የእንግሊዝ ኘሪሚየር ሊግ ፣ የስፔን ላሊጋ ፣ የጣሊያን ሴ ሪ ኤ እንዲሁም ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎችን በአማርኛ ቋንቋ እንዲተላለፉ ከወሰነ አመት አስቆጥሯል።

ከጀርመን ታዋቂ ከሆኑት ዩኒቨርስቲዎች አንዱ የሆነው ሀምቡርግ ዩንበርሲቲ የአማርኛ ት/ ት ማስተማር ከጀመረ መቶ ዓመት አልፎታል።

ቻይና አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ዲግሪ እያስተማረች ነው። ትምህርቱ እየተሰጠ ያለው በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) ነው።

በቅርቡ ደግሞ የፑቲን ሀገር ሩሲያ የአማርኛን ቋንቋ በሩሲያ ትምህርት ቤቶች ማስተማር ልትጀምር መሆኗን ይፋ እንዳደረገች የምናስታውሰው ነው።

እነዚህ የግንጠላ አራማጅ ዘውጌዎች ተፈራረሙ አልተፈራረሙ የሚመጣ ለውጥ የለም። ከትግራይ ሥርዓተ ትምህርት ተወገደ አልተወገደ የሚጎዳቸው እራሳቸውን እንጂ ማንንም አይጎዱም። አማርኛ እንደሆነ እንደ ሰሜን አሜሪካ የመሣሠሉ ታላላቅ ሀገሮች ውስጥ በኦፊሻል ቋንቋነት መንግሥታት እየተቀበሉት የመጣ ቋንቋ ነው።አሜሪካ ከ500 ሺህ በላይ ተናጋሪ ላለው ለተጨማሪ የሥራ ቋንቋነት በማጨት ከ10 ዓመት በፊት ነበር አማርኛ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ያደረገችው።

እነዚህ ስብስቦች ግን ከኢትዮጵያ ለመሸሽ የግእዝ/አማርኛን ፊደል በመጤ የላቲን ፊደል የተኩ የማ*ህ*ይ*ም መጨረሻዎች ናቸው። የኦሮምኛ ቋንቋ አህጉር ተሻግሮ በመጣ የላቲን ፊደል እንዲተካ የተደረገው በ1984 ዓ.ም. ነው። ይህን ያደረጉት የግዕዝ/አማርኛ ፊደል የዐማራ ብቻ ስለመሰላቸውና በዐማራ፣ በአማርኛና በግዕዝም ላይ በነበራቸው ጥላቻ የተነሣ ነው።

ዛሬ በአለም ላይ የራሳቸው የሆነ የጽህፈት ስርዓት ወይም ፊደላት አላቸው ከሚባሉት ቻይና፣ ሕንድ፣ ፋርስ፣ ግሪክ፣ ሮም፣ እስራኤል፣ ባቢሎን እና ግብፅ መካከል ኢትዮጵያ አንዷ የሆነችው ግእዝ ከሚናገሩ አግዓዝያን እና አማርኛ ከሚናገሩ ዐማራዎች የተገኘ ነው። የግዕዝ ፊደል የሚባሉት 24ቱ' ፥ሀ፥ ለ፥ ሐ፥ መ፥ ሠ፥ ረ፥ ሰ፥ ቀ፥ በ፥ ተ፥ ኀ፥ ነ፥ አ፥ ከ፥ ወ፥ ዐ፥ ዘ፥ የ፥ ደ፥ ገ፥ ጠ፥ ጸ፥ ፀ፥ ፈ፥ ናቸው። እነዚህ የግዕዝ ፊደል ኆኅያት ለአማርኛ ቋንቋ በቂ ሆኖ ስላልተገኘ የዐማራ የትምህርቱ ኀላፊዎች ከግእዝ ፊደል ተጨማሪ ምልክትና ተጨማሪ ኆኄያትን መፍጠር ስላስፈለጋቸው፣ የኆኄዎች ምንጮች የቶቹ የግዕዝ ኆኄዎች እንደሆኑ አጥንተው ፦
ግዕዝ አማርኛ
ከ “ደ” “ጀ”ን
ከ“ጠ” “ጨ”ን
ከ“ሰ” "ሸ”ን
ከ"ነ" ”ኘ”ን
ከ “ተ” “ቸ” ን
ከ"ከ" "ኸ"ን
ከ"ዘ" "ዠ"ን አስወለዱ።

እነዚህ ሰባት ግንደ ፊደላት ከእንዚሮቻቸው ጋር ሲደመሩ 49 ይሆናሉ። የኢትዮጵያ የፊደላት ቁጥር ከግዕዝ ኆኄዎች 24'ቱ ከግሪኮች ኆኄዎች 2'ቱ ፊደላት ከአማርኛ ኆኄዎች 7' ቱ ፊደላት ተደምረው ወደ 33 ኆኄዎች ሊያድግ ችሏል።

ኢትዮጵያ በነዚህ ፊደላት አማካኝነት ልጆቿን አስተምራለች፣ ለወግ ለማዕረግ አብቅታለች፣ ታሪኳንና ማንነቷን ፅፋበታለች፣ ነገሥታቶቿ እና ደራሲዎቿ አያሌ ጉዳዮችን ፅፈውባቸዋል። የኢትዮጵያ የማንነት ሐውልት የተገነባውና የቆመው በእነዚህ ፊደላት ነው። እንደ አኩስም፣ እንደ ላሊበላ፣ እንደ ጎንደር ኪነ-ሕንፃዎች አባቶቻችን ያወረሱን ድንቅዬ ቅርሶች፣ የማንነታችን መገለጫ ሀብቶች ናቸው።

ነገርግን በአልባኒያ የኮሚኒዝም ፍልስፍና የሰከሩና
የጐሣ ዕፀ ፋርስ ያሳበዳቸው እንደ ኦሮሞ ነፃነት ግንባር ያሉ ቡድኖች የግእዝ/አማርኛ ፊደል አንፈልግም ብለው ባህር ማዶ ተሻግረው የላቲንን አምጥተዋል። በግእዙ በሁለት ፊደል "ቄሮ" ብሎ ከመጻፍ በላቲን 7 ፊደል "Qeerroo" ብለን ነው የምንጽፈው አሉ ይሄው እየደረደሩት ነው።


ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut