Get Mystery Box with random crypto!

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxmezmur — ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxmezmur — ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit
የሰርጥ አድራሻ: @ortodoxmezmur
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 135.25K
የሰርጥ መግለጫ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
. #ዝማሬ_ዳዊት
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ።
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት
@zmaredawit_messengerbot ላይ
ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-03-19 13:07:24 ቅያሜው ይቅርና

ቅያሜው ይቅርና አምላክ ሆይ ታረቀን
አንተ ስለራከን ሞት ነው የከበበን /2/

እስከመቼ ድረስ ህዝብህ ተጎሳቁሎ
በረከሰ መንፈስ በርኩሰት ተጥሎ
ምድር እያለቀሰች ደም እየሸተታት
እባክህ አምላኬ ኢትዮጵያን ታረቃት
እባክህ አምላኬ ሀገሬን ታረቃት

የዘመኑ ጣዖት ገንዘብ እያሳተን
ይህ ደካማ ስጋ አምላክን አስተወን
ግብዝነት ሞልቶት ፈራሹ አካል
በነፍስ በሽታ ህዝባችን ታሟል /2/

ክንፋችን ተመትቶ መብረር አቅቶናል
በመንፈስ በሽታ ህዝባችን ታውኳል
ራዕይ የሌለው ተራ ሰው ስለሆን
እባክህ ጌታችን በፍጥነት ታረቀን /2/

ጸጋህ የተለየን ባዶነት የሞላን
ፍቅር የተነፈግን ሰላም የጎደለን
ሆነን ስለቀረን እግዚአብሔር ታረቀን
ጽድቅን አድለን ጽድቅ እንደተመኘን/2/

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
12.9K viewsedited  10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-19 00:05:09 ​​+ " በዓለ መስቀል " +

በዚች እለት የክብር ባለቤት ጌታችን አምላካችንና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል የተገለጠበትና የተገኘበት ነው። የዚህም የከበረ ዕፀ መስቀል መገለጡና መገኘቱ ሁለት ጊዜ ሆኗል። መጀመሪያ የፃድቁ ንጉስ የቆስጠንጢኖስ እናት በሆነች በንግስት ህሌኒ እጅ ነው።

እርሷ ለእግዚአብሄር ተስላ ነበርና ልጇ ቆስጠንጢኖስ ወደ ክርስቲያን ሀይማኖት ቢገባ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዳ መስቀሉን እስከ አገኘችው ድረስ ልትፈልግው በኢየሩሳሌም ያሉ ቅዱሳት መካናትንና አብያተ ክርስቲያናትን ልታንፃቸው ነው።

ከዚህ በኃላ ልጇ አምኖ የክርስትና ጥምቀትን በተጠበቀ ጊዜ እሌኒ ቅድስት ወደ ኢየሩሳሌም ሄደች ከእረሷ ጋርም ብዙ ሰራዊት ነበር ደርሳም ስለ ከበረ መስቀል መረመረች የሚያስረዳት አላገኘችም የአይሁድ ወገን የሆነ አንድ ሽማግሌ ሰው አስራ በርሀብና በጥማት አሰቃየችው ።

በተጨነቀም ጊዜ ለንግስት እሌኒ የጉልጎታን ኮረብታ አስጠርጊ ብሎ ነገራት እርሷም ይጠርጉ ዘንድ አይሁድን አዘዘቻቸው። ቤቱን የሚጠርግ ሰው ሁሉ ጥራጊውን በውስጡ የከበረ መስቀል በአለበት በጌታችን መቃብር ላይ እንዲጥል አይሁድ አስቀድመው አዝዘው ነበርና ንግስት እሌኒ እስከ ደረሰችበት ጊዜ ከሁለት መቶ አመት በላይ ጥራጊያቸውን ሲጥሉበት ኖሩ ኮረብታም ሆነ።

አይሁድም በጠረጉ ጊዜ ሶስት መስቀሎች ተገለጡ የክብር ባለቤት ክርስቶስ የተሰቀለበት የትኛው እንደሆነ አላወቁም። የሞተ ሰውም አግኝተው አመጡ ። አንዱንም መስቀል አምጥተው በሞተው ሰው ላይ አኖሩት አልተነሳም ደግሞ ሌላውን መስቀል አምጥተው በሙቱ ላይ አኖሩ አሁንም አልተነሳም ከዚህም በኃላ ሶስተኛውን መስቀል አምጥተው በሙቱ ላይ አደረጉት ያንጊዜ የሞተው ሰው ተነሳ እሌኒም የክርስቶስ መስቀል እንደሆነ አውቃ ሰገደችለት የክርስቲያንም ወገኖች ሁሉ ሰገዱለት።

ለልጅዋ የላከችው ይህ መስቀል ነው የሚል በሌላ መፅሀፍ ይገኛል የቀረው ግን ግንዱ በውስጡ ተተክሎበት የነበረው ከእርሱም እኩሌታውን ከቅንዋቱ ጋራ ወደ ልጅዋ የላከችው ነው። ከዚህም በኃላ ስራአታቸውና የህንፃቸው ነገር በመስከረም ወር በአስራ ሰባት ተፅፎ የሚገኝ አብያተ ክርስቲያናትንና የከበሩ ቦታዎችን አነፀች።

ሁለተኛው በሮሙ ንጉስ በህርቃል ዘመን የሆነው ሲሆን የፋርስ ሰዎች በግብፅ አገር ሳሉ ወደ አገራቸው ሊመለሱ ወደዱ። ከሹማምንቶቻቸው አንዱ የጦር መኰንን ተነጥሎ ወደ ኢየሩሳሌም አልፎ ደረሰ ወደ ከበረ መስቀል ቤተ ክርስቲያንም ገባ። መስቀሉም በላዮ በተተከለበት ግንድ ፊት ታላቅ ብርሀን ሲበራ አይቶ ሊያነሳው እጁን ዘረጋ። እሳትም ወጥታ እጁን አቃጠለችው።

ከክርስቲያን በቀር ማንም ሊነካው እንደማይችል የመስቀልን የክብሩን ነገር ሰዎች ነገሩት። ሁለት ዲያቆናትንም ይዞ የከበረ መስቀልን እንዲሸከሙ አዘዛቸወወ ከኢየሩሳሌምም ብዙ ሰዎችን ማርኮ ወደ አገሩ ተመለሰ።

የፋርስ ሰዎች ኢየሩሳሌምን እንዳጠፏት ብዙዎች ሰዎችንም እነድ ማረኩና የከበረ የክርስቶስንም መስቀሉን እንደ ወስዱየሮም ንጉስ ህርቃል በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ። ስለርሱም እንዲፆሙ ምእመናንን አዝዞ ወደፋርስ ዘምቶ ወጋቸው ብዙዎችንም ገደላቸው የከበረ እፀ መስቀልንም እየፈለገ በሀገራቸው ሁሉ ዞረ ግን አላገኘውም።

ያ ዲያቆናቱና መስቀሉን የወሰደ መኰንን ከቦታዎች በቤቱ አነፃር ባለ በአንድ ቦታ ላይ ወስዷቸው ጥልቅ ጉድጓድ እንዲቆፍሩ አዝዞ በዚያ የከበረ መስቀልን አስቀበረ እነዚያንም ዲያቆናት ገደላቸው።

ነገር ግን ያ መኰንን የማረካት የካህናት ወገን የሆነች በእርሱ ቤት የምትኖር አንዲት ብላቴና ነበረች። እርሷም የከበረ መስቀልን ሲያስቀብርና ሁለቱን ዲያቆናት ሲገድላቸው በቤቱ ውስጥ ሁና በመስኮት ትመለከት ነበር ወደ ንጉስ ሕርቃልም ሂዳ መኰንኑ ያደረገውን ሁሉ ነገረችው።

ይህንንም ንጉስ ሰምቶ እጅግ ደስ አለው ያቺ ብላቴናም መራችው ከእርሱም ጋራ ብዙ ሰራዊት ሆኖ ኤጲስቆጶሳትና ካህናትም ነበሩ ።ወደ ቦታውም እስከምታደርሳቸው ያቺን ልጅ ተከተሏት ቅፍረውም የከበረ እፀ መስቀልን አገኙት ከአዘቅቱም አወጡት ንጉሱና ሰራዊቱም ሰገዱለት።

በልብሰ መንግስቱም አጐናፀፈው ታላቀወ ክብርንም አከበረው እጅግም ደስ አለው ከሰራዊቱ ጋር። የዚህም መስቀል ሁለተኛ የተገለጠበትና የተገኘበት በዚች ቀን በመጋቢት አስር ነው። ከዚህ በኃላ ንጉሱ የከበረ እፀ መስቀልን ተሸክሞ ወደ ቁስጥንጥንያ ከተማ ወሰደው።

መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ካረገ ከዓመታት በሁዋላ አይሁድ በአንድ ነገር ተቸገሩ:: የክርስቶስን ሐዋርያት እያሳደዱ ቢገድሉም ከመስቀሉና ሥጋ ክርስቶስ አርፎበት ከነበረው ጐልጐታ ላይ የሚደረገውን ተአምር ግን መግታት አልተቻላቸውም::

+ መቼም ለተንኮል አያርፉምና ቅዱስ መስቀሉን ሽፍቶቹ ከተሰቀሉባቸው ጋር ደርበው አርቀው ቀበሩት:: አካባቢው የጉድፍ መጣያ እንዲሆንም አዋጅ ነገሩ:: ለክፋት ሲሆን ተባባሪው ብዙ ነውና ለ300 ዓመታት ያህል ቆሻሻ ቢጥሉበት
ተራራ ሆነ::

+ ከዚህ ሁሉ ነገር በሁዋላ እናታችን ቅድስት እሌኒ (ሔለና) በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት: በቅዱስ ኪራኮስ መሪነት: በቅዱስ ሚካኤል ረዳትነት ደመራ አስደምራ: እጣን አጢሳ መካነ
መስቀሉን አገኘች::

+ መስከረም 17 ቀን የተጀመረው ቁፋሮ መጋቢት 10 ቀን ተጠናቆ: ንጹሕ መስቀሉ ወጥቶ ብርሃን በርቷል: ሙታን ተነስተዋል:: ከ10 ዓመት በሁዋላም የመስቀሉ ቤተ መቅደስ ታንጾ መስከረም 17 ቀን ተቀድሷል::

+ይህ ቅዱስ ዕፀ መስቀልም በደጉ አፄ ዳዊት ዘመን ወደ ሃገራችን መጥቶ: በጻድቁ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ አማካኝነት በደብረ ከርቤ (ግሸን ማርያም) ተለብጦ ተቀምጧል::

አምላከ ቅዱሳን በኃይለ መስቀሉ: በሞገሰ መስቀሉ ይጠብቀን:: ከበረከቱ አሳትፎ በዓሉን የሰላም ያድርግልን::

መጋቢት 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ዕፀ መስቀል
2.ቅድስት ዕሌኒ ንግሥት
3.ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ
4.ቅዱስ መቃርስ ዘኢየሩሳሌም

ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ ንጉሥ
4.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
5.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)

"+ የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት: ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና . . . መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ:: የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ:: እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን:: +" (1ቆሮ. 1:18-23)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
ዝክረ ቅዱሳን
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
14.6K views21:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-18 19:25:16 #አረ_አንቺ_አለም
የበገና ዝማሬ

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
14.1K views16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-18 11:51:54 ✣ የዓቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ✣

╔════●◉❖◉●══════╗
ቅድስት
╚════●◉❖◉●══════╝
✢ Share ✢
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
15.3K views08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-18 07:18:16 ወዴት ወድቆ ይሆን
የበገና ዝማሬ

እንክርዳድ ኑፋቄን ገበሬው ለይቶ
መልካም ዘር ሲዘራ ወደ ማሳው ወጥቶ
ለአጨዳው ምጽአት ለበጋው አዝመራ
ወዴት ወድቆ ይሆን ክረምት የተዘራ /2/

ዘወድቀ ውስተ ፍኖት ሲዘራ ያለቀው
አእዋፍ ሰማይ መሳጤ ነጠቀው
ዘወድቀ ዲበ ኮክሕ ጥልቅ አፈር ከሌለው
በደስታ እየሰማ በችግር የካደው
ዘወድቀ ውስተ ሦክ ተጨንቆ እንዳይወጣ
በዓለም ትካዜ በስፍጠተ ብዕል ታንቆ ፍሬ አጣ

ውስተ ምድር ሠናይ የወደቀም ነበር
ዘወሀበ ፍሬ ሰምቶ ሚተገብር
ጌታዬ ከአራቱ ስፍራዎች በምሳሌ ካልከው
ወዴት ወድቆ ይሆን ከእኔ ልብ የላከው
እባክህ ጎተራ አበጅተህ ለአጨዳ ስትመጣ
ከፍሬያማው ክምር ዕድል እንዳላጣ

ከእሾህ ከጭንጫ ላይ ከመንገድ እንዳልቀር
ልቤ ልብ አግኝቶ በምግባር እንዲኖር
ራሴን መስማት ትቼ ላንተ ፈቃድ ልደር

ዲ/ን ቀዳሜጸጋ
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
13.3K views04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-17 00:08:58 #ሰንበተ_ክርስትያን

በኩር ናት የበዓላት
ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት
በእሷ ደስ ይበለን
በሰንበተ ክርስቲያን

በዝማሬ እንበርታ በገናውን እንያዝና
መልካም ስራ የሚሰራባት
ሰንበት ቅድስት ናት እና
ከጨለማ ብርሀን ከመገዛት ነፃነት
እግዚአብሔር ይህን ሰጠን
ደስ ይበለን በሰንበት
#አዝ
ለአብርሃም ተገልጣለች
ለሙሴም በደብረ ሲና
በነቢያት የታወቀች
ሰንበት ዳራዊት ናት እና
በሳምንቱ ሰለጠነች
ተሰበከች በሐዋርያት
ሃሌ ሉያ ዕለተ ሰንበት
ተሰጠችን ልናርፍባት
#አዝ
በእልልታ እንሞላ እንደ ነቢዩ አሳፍር
በከበረች የሰንበት ቀን ኑ ለቅኔ እንሰለፍ
በመቅደሱ ናቸው እና ቅዱስነትና ግርማ
ውዳሴያችን ይሰማልን
ከምድር እስከ እዮር እራማ
#አዝ
እግዚአብሔር አብ የባረካት
እግዚአብሔር ወልድ የቀደሳት
ከእለታት ሁሉ መርጦ
መንፈስ ቅዱስ ከፍ ያደረጋት
በእርሷ ሀሴት እናድርግ
እናክብራት እንድንከብር
የደጀሰላሙ ታዛ በመቅደሱ እንሰብሰብ

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
15.3K views21:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-16 21:15:44
ድሮ ድሮ እናቶች በልጆቻቸው በጣም ሲበሳጩ እንዲህ ይሉ ነበር " ምናለ አንተን ከምወልድ መኃን ሆኜ በቀረው"

ዘንድሮ የልጆች ተራ ሳይሆን አልቀረም!
በአባት እንደማዘን፣ እንደማፈር እና እንደመሸማቀቅ የሚያሳዝን ነገር የለም።

ጾሙ ከእህል መራብ ብቻ ሆነ

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
15.3K views18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-16 19:28:43 ​​​​ቅድስት (የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት)

«ቅድስት» ማለት የዘይቤ ፍችው « የተቀደሰች የተለየች » ማለት ነው። ምስጢራዊ መልእክቱ ግን የምስጢረ አድኅኖት ታላላቅ ሥራውን ለመጀመር መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶሰ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ ከቆመ ሳያርፍ፣ ከዘረጋ ሳያጥፍ የጾማት የአርብዓው ቀንና ሌሊት ልዩ የሆነችና ክብርት ጾም የምትጀመርበትን ሁለተኛ ሳምንት ከልብ ያሳስበናል፡፡ ማቴ. 4-2

ቅድስት የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ስያሜውም ከኢትዮያዊው የዜማ ሊቅ ከቅዱስ ያሬድ የተገኘ ነው። ከዚህ ሰንበት ዋዜማ ጀምሮ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ይዘመራል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ሰንበቱን ስለ ቅድስና ልጆቿን ታስተምርበታለች ፡፡

በቅዳሴ ጊዜ የሚሰበከው ምስባክ ፤ የሚነበቡ መልዕክታት ፤የሐዋርያት ሥራ ና ወንጌል ስለ ቅድስት የሚያስተምሩ ናቸው፡፡

‹‹ቅዱስ›› ማለት ልዩ፤ ክቡር ማለት ነው፡፡እግዚአብሔር አምላካችን በባሕርዩ ቅዱስ ነው፡፡ ይህም ቅድስና ከማንም ያላገኘው የባሕርይ ገንዘቡ ነው። መጻሕፍትም የባሕርይ ቅድስናውን ተባብረው መስክረዋል፡፡ ባባሕርዩ ቅዱስ ስለሆነ ‹‹ቅዱስ፡ቅዱስ፡ቅዱስ›› እየተባለ ይመሰገናል፡፡ ( ኢሳ 6፡1-3፤40፡25 ራዕ 15፡4 ፤ 1ሳሙ2፡2-3፡፡) እኛም ቅዱስ ልጁ በሥጋ ተገልጦ እንዳስተማረን በየዕለት ጸሎታችን ‹‹ስምህ ይቀደስ›› እንለዋለን፡፡

የቅድስና ምንጭ ፡ ቅድስናን የሚሰጥ እርሱ ብቻ ነው፡፡ ‹‹ ቅዱስ ›› የሚለው ቃል ለሰዎች ፡ለመላእክት ፡ ለቦታ ፡ለዕቃ: ለዕለታት … ቢቀጸልም ቅድስናቸው በባሕርይው ቅዱስ ከሆነው ከእግዚአብሔር የተገኘ ነው፡፡ ይህም የጸጋ ቅድስና ይባላል፡፡

እግዚአብሔር ቅዱስ ስለሆነ በመልኩና በምሳሌው አክብሮ የፈጠረንን እኛም ቅዱሳን እንድንሆን ይፈለጋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁን›› ተብሎ ስለተጻፈ የጠራቸው ቅዱስ እንደሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ ›› ያለንም
ይህንን ሲያስተምረን ነው። ከመፈጠራችን አስቀድሞ መጠን በሌለው ፍቅር የወደደን እግዚአብሔር ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣን ፤ ለውርደት ሳይሆን ለክብር፤ ለርኩሰት ሳይሆን ለቅድስና፤ ለሞት ሳይሆን ለሕይወት ነው፡፡ የመፈጠራችንም ዓላማ በፊቱ በፍጹም ምግባርና ሃይማኖት በመመላለስ ከእርሱ ጋር እንድንኖር ነው፡፡ ብርሃን ከጨለማ፡ ጽድቅ ከኃጢአት፡ ጋር ኅብረት የለውምና ከእርሱ ጋር ለዘላለም ነግሰን ለመኖር በቅድስና መኖር ይጠበቅብናል፡፡

ቅድስናችን በኑሮአችን ሁሉ እንዲሆን ታዘናል (1ጴጥ1፡15)፡፡ ስለዚህ በተሰማራንበት የሥራ መስክ ፣ በማኅበራዊ ኑራአችን ፣በምንበላው ምግብ ፣በምንለብሰው ልብስ ፣ በንግግራችንና በመሳሰለው ሁሉ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኘውን በማድረግ እግዚአብሔርን በሚሞት ሥጋችን እናክብረው፡፡ ‹‹እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ የኃጢአትንም ጭንቀት ከእኛ አስወግደን በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግስት እንሩጥ፡፡

የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን እንከተለው፤ እርሱ ነውርን ንቆ ፣ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል ›› ተብሎ እንደተጻፈ ደምን እስከ ማፍሰስ ድረስ ተጋድሎ አድርገን ከኃጢአት ርቀት በቅድስና እንድንኖር ይገባናል (ዕብ 12፡1)።

ሥጋዊ ምኞታችንንና መሻታችንን ሰቅለን አሮጌው ሰዋችንን አስወግደን ንስሐ ገብተን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለን በቅድስና እንድናኖር ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
17.2K views16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-16 15:27:31 8/07/16 ዓ.ም
ቅድስት

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ፡፡

የዕለቱ ምስባክ፦ መዝ ፺፭፥፭
እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ
አሚን ወሠናይት ቅድሜሁ
ቅድሳት ወዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ

ትርጉም
እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ፈጠረ
እምነትና በጎነት በፊቱ ናቸው
ቅድስና እና የክብር ገናንነት በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።

የዕለቱ ወንጌል፦
ማቴ ፮፥፲፯ - ፳፭
ቅዳሴ፦ ዘኤጲፋንዮስ

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
14.7K viewsedited  12:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-16 09:28:49
መመዝገብ ለምትፈልጉ ኦርቶዶክሳዊያን
በ0956861468
በ0912085085
በ0965083251 ደውለው ይመዝገቡ

እንዲሁም በቴሌግራም ለመመዝገብ ለምትፈልጉ
@Orthodoxtewahed0

በእዚህ ሊንክ በውስጥ ማውራት ትችላላችሁ

ያለው ቀሪ ቦታ ውስን ስለሆነ ቶሎ እንድትመዘገቡ እንጠይቃለን

መማሪያ ሰዓቶች
ከሰኞ-አርብ 11:00-1:00

ቅዳሜ እና እሑድ
3:00-5:00
6:00-8:00
9:00-11:00

ክፍያ የ6ወሩ በወር 500ብር
        የ3ወሩ በወር 1000ብር ነው ሁለቱም ዋጋቸው እኩል ነው አጠቃላይ 3000ብር ነው የሚመጣው። መመዝገቢያ 100ብር ይጨምራል።


ከበሮ አለን የ1 ወር እና የ1 ሳምንት
የ1 ሳምንቱ ሙሉ ሳምንት ሲሆን
ከ8:00-10:00 እና 9:00-11:00 አለ
የአንድ ወሩ ከሆነ በሳምንት 2 ቀን ነው የምትማሩት። ሁለቱም ክፍያቸው ተመሳሳይ ነው 1100ብር ነው
16.7K views06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ