Get Mystery Box with random crypto!

NidaTube -ኒዳ ቲዩብ

የቴሌግራም ቻናል አርማ nidatube — NidaTube -ኒዳ ቲዩብ
ርዕሶች ከሰርጥ:
Gondarmassacre
የቴሌግራም ቻናል አርማ nidatube — NidaTube -ኒዳ ቲዩብ
ርዕሶች ከሰርጥ:
Gondarmassacre
የሰርጥ አድራሻ: @nidatube
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.96K
የሰርጥ መግለጫ

ኒዳ ቲዩብ መረጃ እና መማሪያ ቲዩብ
Join ያድርጉን
🦋 🦋 🦋
Telegram → https://t.me/nidatube
Facebook → www.facebook.com/NidaTubeOfficial
Instagram → www.instagram.com/NidaTubeOfficial
Visit → www.nidatube.net
ለማንኛውም አስተየዬት እና መረጃ የፃፉልን →
@nidatubebot

Ratings & Reviews

4.50

0 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-05-08 22:10:27
የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ለምትፈልጉ

በቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ኮሌጅ የዓይን ህክምና ትምህርት ክፍል HCP በተባለ ግብረሰናይ ድርጅት እገዛ 500 የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና /CATARACT SURGERY/ ከ ሰኔ 6-12/2014 ዓ.ም ለማድረግ አስቧል፡፡

ስለሆነም ይህን የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ለማድረግ ቅድመ ምርመራ፣ልየታና ምዝገባ በግንቦት ወር ባሉት ቅዳሜና እሁድ ቀናቶች ማለትም (ግንቦት 6፣7፣13፣14፣20፣21፣27፣28 ) ስለምናደርግ በኮሌጁ የስልክ አገልግሎት 976 በመደወል ለቅድመ ምርመራ፣ ልየታና ምዝገባ ቀጠሮ እንድትይዙ ስንል በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- በስልክ ቀጠሮ ያልተሰጠዉ ታካሚ ቅድመ ምርመራም፣ ልየታም ይሁን ምዝገባ ማድረግ አይችልም፡፡
.................
ሼር በማደርግ ያሰተላለፉት
@nidatube
4.1K views19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 13:30:34 እጅግ በጣም የሚገርመኝ .......

በአቡ ሀይደር

የሆነን ክልል ይጠቅሱና: በክልሉ የተሰራውን ቤተ ክርስቲያን ለማገዝ ከሙስሊሞች በኩል ይህን ያህል ሚሊየን ተለገሰ፣ ለምርቃቱ ደግሞ ይህን ያህል በሬ ተሰጠ! የሚለውን ዜና እንደጉድ ያሰራጩና: በመጨረሻም:– ይህ ነው ኢትዮጲያዊነት! ይህ ነው ጨዋነት! ይህ ነው አንድነት! በማለት መልክቱን ይቋጩታል።

እኔ የምጠይቀው:– የተወራው ነገር እውነት ከሆነና: የኢትዮጲያዊነት ፀባይ አንዱ መገለጫ: የአንዱን የአምልኮ ቦታ ሌላው በእምነት የማይመስለው ወገኑ: ከቻለ በገንዘብ ካልቻለ ደግሞ የምርቃት ቀን የእርድ ከብት ማቅረቡን ከልብ አምናችሁ ከተቀበላችሁት: እናንተስ የሙስሊሙን መስጂድ ከማቃጠልና ከማፍረስ ውጭ ምን ሰርታችሁ ታውቃላችሁ? በመዲናችን አዲስ አበባ እንኳን: በህጋዊ መንገድ ፍቃድ ያገኘንበትን ቦታ በሰላም እንድንገነባ በዝምታ እንኳ መች ተባብራችሁ ታውቃላችሁ? የቱንም ያህል ቢራራቁም: ህዝቡን ለማነሳሳት ከቤ/ክርስቲያን ጎን መስጂድ ሊሰራ ነው ብላችሁ ረብሻ መቀስቀስ፣ ድንጋይ መወርወር፣ ከታቻለም መሳሪያ መተኮስ መገለጫችሁ አይደለምን? ከአንዋር መስጂድ ውጭ የትኛው መስጂድ ነው ደም ሳይፈስ በሰላም የተገነባው? ወይስ ኢትዮጲያዊ ጨዋነትና አንድነት እናንተን አይመለከትም? ወይስ ጨዋነቱና አንድነቱ የሚሰራው ለቤ/ክርስቲያን ግንባታ ሲሆን ብቻ እንጂ ለመስጂድ ግንባታ ግዜ አይሰራም? ኧረ እንደው በራሳችሁ ድርጊት እንድታፍሩ የሚገስጻችሁ የህሊናም ይሁን የሃይማኖት መካሪ የላችሁም? ለቤ/ክ ግንባታ የሙስሊሙን መሳተፍ የኢትዮጲያዊ ጨዋነት መገለጫ መሆኑ እውነት ከታመነበት: እናንተ ምንም ኢትዮጲያዊ ጨዋነት እንደሌላችሁ መስክራችኋል ማለት ነው። ሙስሊሞች ለቤ/ክርስቲያናችን ለግንባታው እና ለምርቃቱ ይህን አደረጉልን እንጂ እኛ ለነሱ መስጂድ ይህን አደረግንላቸው ብላችሁ የምታወሩት ምንም የላችሁም። አድርጋችሁብን እንጂ አድርጋችሁልን አታውቁምና!!

አል–ሐምዱ ሊላህ ዓለሰ ኒዕመቲል ኢስላም
@nidatube @nidatubebot
3.6K views10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 21:44:49
ክርሰቲያን ወንድማችን ጥያቄ ያቀርባል
@nidatube
3.5K views18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 20:56:47
የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ!
ከነገ ሚያዚያ 30 ጀምሮ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደርጓል።
በዚህም መሰረት፦
ቤንዚን በሊትር 36 ብር ከ87 ሳንቲም ፣
ነጭ ናፍጣ በሊትር 35 ብር ከ43 ሳንቲም፣
ኬሮሲን በሊትር 35 ብር ከ43 ሳንቲም፣
ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 52 ብር ከ45 ሳንቲም፣
ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 51 ብር ከ78 ሳንቲም
የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 78 ብር ከ87 ሳንቲም ሆኗል።
@nidatube
3.5K views17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 17:48:29
@nidatube
3.6K views14:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 20:09:50
በጎንደርና በደባርቅ ጥቃት አድራሾች በሽብርተኝነት ሊፈረጁ ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ማኅበር በሲያትል ጠየቀ
@nidatube
4.6K views17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 10:19:52
4.2K views07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-30 14:33:19
የጎንደር አሥተዳደር መስጊድ ላይ ድራማ መሥራትን መርጧል!
—————————
.ኢስሀቅ እሸቱ

የጎንደር አሥተዳደር በታጠቁ አሸባሪዎች ደሙ ሲፈስ፣ አጥንቱ ሲከሰከስ የቆየውን የጎንደር ሙስሊም ከለላ በመስጠት ፈንታ ድራማ ይሠራበት ጀምሯል። ጌሾ ሠፈር አቅራቢያ የሚገኘውና በ3 አቅጣጫ በጥይት ሲደበደብ የከረመው መስጊድ ላይ አዲስ ❝ጂሐዳዊ ሐረካት❞ መሰል ድራማ መሥራትን መርጧል።
.
በትናንትናው ዕለት በመስጊዱ ጀርባ ባሉ ቤቶች በኩል ገጀራዎችን እና መሣሪያዎችን ከውጭ በማስገባት ❝መስጊድ ውስጥ ተገኘ❞ በሚል የሐሰት ዶኩመንተሪ ሲቀርጹ መዋላቸውን ማወቅ ተችሏል። ለድማራው ግብዓት እንዲሆንም የሃይማኖት አባቶችን በማምጣት ❝ሙስሊሙ ጥፋቱን አምኖ ቤተ ክርስትያንን ይቅርታ ይጠይቅና ሠላም ይውረድ ይህንን ካደረጋችሁ የዒድ ሶላት እንድትሰግዱ ይፈቀድላችኋል❞ የሚል እጅግ አሳፋሪ ጥያቄ አቅርበዋል።
.
መንግሥት ❝በቁጥጥር ሥር ውለዋል❞ ካላቸው 380 ሰዎች አብዛኛዎቹ ሙስሊሞች መሆናቸውንም ማወቅ የተቻለ ሲሆን ልክ በሞጣው ጥቃት እንዳደረጉት ሙስሊሙን ራሱ ተጠያቂ ለማድረጎ ቆርጠው እየሠሩ ይገኛሉ።
.
ይህንን ተበዳይን በዳይ አስመስሎ የማቅረብ ነውረኛ ፕሮፓጋንዳ መከላከል የምንችለው እኛው ነን! ሁላችንም ኢ-ሰብዓዊውን በደል በማጋለጥ ከተበዳይ ጎን እንቁም! ሐሽታጎቹን ተጠቅመን እንጻፍ! በዝምታ የምናሣልፋት እያንዳንዷ ሰከንድ በጎንደር ሙስሊሞች አንገት ሸምቀቆው እንዲጠብቅ እንደምታደርግ አንዘንጋ! ሼር በማድረግና በራሳችን በመጻፍ እንረባረብ!
.
#የጎንደርጭፍጨፋ #GondarMassacre #ደባርቅ #ሙስሊምጠልነት #ፋኖ
6.4K views11:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 23:15:14 በጎንደር ሙሰሊም ላይ ያነጣጠረ ግደያ የሁለት ሃይማኖቶች ግጭት ለማስመሰል የምትጋጋጡ ሚዲያዎች ተቆጠቡ ፣ ጥቃቱ ሙሰሊም ላይ ብቻ የተደረገ የአንድ ወገን ጥቃት ነው።

share ...share...share
6.3K viewsedited  20:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 22:39:24 ለመሸፋፈን ብንለፋ አልሸፈን ያለን ነውር ዛሬም ራሱን ገልጧል

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን! የሞቱትን ለጀነት፣ ለቆሰሉት ፈጣን ፈውስ፣ ንብረታቸውን ላጡ የተሻለ ካሳ ከአላህ እማፀናለሁ

መተባበርና መተዛዘን በሚጠበቅባቸው ግዚያትና ቦታዎች ማጥቃት ቀላል የሆነላቸው ድንገተኛ ክስተት ሆኖ አይደለም

በቀላሉ ሊቆም የሚችልን ችግር እንደሰደድ እሳት ያስፋፉት ከአቅም በላይ ሆኖ አይደለም፣

በመቃብር ስፍራ ላይ ያስጀመሩትን ጥቃት ወደመኖሪያ ቤት፣ የንግድ ማእከላትና መሳጂዶች ያዛመቱት ድንገት ከጃቸው ወጥቶ አይደለም

ትንሽ መስለው ሰፊውን ህዝብ የሚያውኩት ክፋታቸው በቁጥራቸው ብቻ የሚገለፅ ሆኖ አይደለም

ብዙዎቹ ነገሮች ሁሌ ለመስጠት እንደምንሞክረው ቀና መላምት፣ ለህዝቦች አብሮነት እንደምንለፋው አልሳካ ያሉት ለመሸፋፈን የምንጥረው ነውር ራሱን ደግሞ ደጋግሞ እየገለጠ ነው።

ይህንን ነውር የጎንደር ህዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ሊጠየፈው ይገባል። ከውስጡ የበቀሉ የነውረኛ ሥብስቦችን ነቅሎ ለመጣል የሚከፈለውን ዋጋ ሁሉ ቢከፍል ለጎንደር ህዝብ የቆየ ሰላማዊነትና ለነገዋ ጎንደር እፎይታ እጅግ የሚገባ አንገብጋቢ ስራ ነው። የአካባቢው ባለስልጣናትና የክልሉ መንግስት አካባቢውን እና ክልሉን እረፍት የለሽ ሁከት ውስጥ እየከተቱ ክልሉን የነውረኞች መሸሸጊያ እንደሆነ የሚሰሩትን ሳያቃልል እና ምንም ምክንያት ሳይደረድር ሊያስቆምና ሊቀጣ ይገባል። አመራሩ የሚወስደው የማያዳግም እርምጃ ለሰላሙ ብቻ ሳይሆን ነውረኞች በአመራሩ ውስጥ ሰርገው አለመግባታቸውን ማስተማመኛ የሚሰጥ ነው።

ነውረኞች የመጨረሻ ግባቸው የህዝባችን ቋንቋ እና ምግባር በነሱ ደረጃ ወርዶ የነሱ ህግ ገዢ እንዲሆን ነው የሚሹት። ትንሽ ቢሆኑም በነውራቸው ብዙውን ሊበክሉ እንደሚችሉ በማመን ወደሜዳቸው ነው ሊጠሩን የሚመኙት፣ እረፍታቸው የሚመነጨው አለመረጋጋት በመፍጠር ስለሆነ ከሰከነ መንፈሳዊነትና ከተረጋጋ አውድ እንድንወጣ ነው የሚለፉት

ለነርሱ የምንደረድረው የይሆናል ምክንያት አልቆብን ግልፁን መናገር ብንጀምርም ያስነሱትን የነውር መንገድ በጎንደርም ሆነ በተቀረው አካባቢ እንዲሰፍን ግን ፈፅሞ አንፈቅድላቸውም። የተቀረውን አካባቢ ሰላም እንዲጠበቅ እየሰራን እነርሱን ነቅሎ ለመጣል ከጎንደር ህዝብና የሀገር ሽማግሌዎች፣ ከአካባቢው አመራሮች፣ ከክልሉና ከፌዴራል መንግስት ጋር በትብብር እንሰራለን። እንደምናሸንፋቸውም ሙሉ እምነት አለን!

ኡስታዝ አቡበክር አህመድ
ሚያዝያ 18/2014
5.7K views19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ