Get Mystery Box with random crypto!

እጅግ በጣም የሚገርመኝ ....... በአቡ ሀይደር የሆነን ክልል ይጠቅሱና: በክልሉ የተሰራውን | NidaTube -ኒዳ ቲዩብ

እጅግ በጣም የሚገርመኝ .......

በአቡ ሀይደር

የሆነን ክልል ይጠቅሱና: በክልሉ የተሰራውን ቤተ ክርስቲያን ለማገዝ ከሙስሊሞች በኩል ይህን ያህል ሚሊየን ተለገሰ፣ ለምርቃቱ ደግሞ ይህን ያህል በሬ ተሰጠ! የሚለውን ዜና እንደጉድ ያሰራጩና: በመጨረሻም:– ይህ ነው ኢትዮጲያዊነት! ይህ ነው ጨዋነት! ይህ ነው አንድነት! በማለት መልክቱን ይቋጩታል።

እኔ የምጠይቀው:– የተወራው ነገር እውነት ከሆነና: የኢትዮጲያዊነት ፀባይ አንዱ መገለጫ: የአንዱን የአምልኮ ቦታ ሌላው በእምነት የማይመስለው ወገኑ: ከቻለ በገንዘብ ካልቻለ ደግሞ የምርቃት ቀን የእርድ ከብት ማቅረቡን ከልብ አምናችሁ ከተቀበላችሁት: እናንተስ የሙስሊሙን መስጂድ ከማቃጠልና ከማፍረስ ውጭ ምን ሰርታችሁ ታውቃላችሁ? በመዲናችን አዲስ አበባ እንኳን: በህጋዊ መንገድ ፍቃድ ያገኘንበትን ቦታ በሰላም እንድንገነባ በዝምታ እንኳ መች ተባብራችሁ ታውቃላችሁ? የቱንም ያህል ቢራራቁም: ህዝቡን ለማነሳሳት ከቤ/ክርስቲያን ጎን መስጂድ ሊሰራ ነው ብላችሁ ረብሻ መቀስቀስ፣ ድንጋይ መወርወር፣ ከታቻለም መሳሪያ መተኮስ መገለጫችሁ አይደለምን? ከአንዋር መስጂድ ውጭ የትኛው መስጂድ ነው ደም ሳይፈስ በሰላም የተገነባው? ወይስ ኢትዮጲያዊ ጨዋነትና አንድነት እናንተን አይመለከትም? ወይስ ጨዋነቱና አንድነቱ የሚሰራው ለቤ/ክርስቲያን ግንባታ ሲሆን ብቻ እንጂ ለመስጂድ ግንባታ ግዜ አይሰራም? ኧረ እንደው በራሳችሁ ድርጊት እንድታፍሩ የሚገስጻችሁ የህሊናም ይሁን የሃይማኖት መካሪ የላችሁም? ለቤ/ክ ግንባታ የሙስሊሙን መሳተፍ የኢትዮጲያዊ ጨዋነት መገለጫ መሆኑ እውነት ከታመነበት: እናንተ ምንም ኢትዮጲያዊ ጨዋነት እንደሌላችሁ መስክራችኋል ማለት ነው። ሙስሊሞች ለቤ/ክርስቲያናችን ለግንባታው እና ለምርቃቱ ይህን አደረጉልን እንጂ እኛ ለነሱ መስጂድ ይህን አደረግንላቸው ብላችሁ የምታወሩት ምንም የላችሁም። አድርጋችሁብን እንጂ አድርጋችሁልን አታውቁምና!!

አል–ሐምዱ ሊላህ ዓለሰ ኒዕመቲል ኢስላም
@nidatube @nidatubebot