Get Mystery Box with random crypto!

ያሳዝናል!በስተመጨረሻ የTDF አባላት እውነቱን መናገር ጀመሩ። ትርጉም በናትናኤል አስመላሽ ተፃፈ | Natnael Mekonnen

ያሳዝናል!በስተመጨረሻ የTDF አባላት እውነቱን መናገር ጀመሩ። ትርጉም በናትናኤል አስመላሽ

ተፃፈ በዳንኤል ወዲ አቡነ እንድርያስ

"ለካ በህይወት መትረፍ ያሳዝናል"
ሁሌም ፈጣሪዬን ሳመሰግን፣ለኔ ያደረግክልኝ ለማን አደረግክለት እል ነበር፤ ዛሬ ግን ምን ነበር እንደተሰዉት ብሰዋ ኖሮ ለምን በቀላሉ ተመትቼ በህይወት ተረፍኩ ብዬ አምርሬ የቁጭት ለቅሶ አለቀስኩ።መስዋእትነት ተመኘሁ!ግን ማን በሰጠኝ!ወይኔ!እነዛ ከፊቴ የረገፉት ምልምል ወጣቶች ሁሉ ለካ ህዝብን ለማዳን አልነበረም ።
.
.
.
በመሃከላችን የወደቀው ሞርታር ፈንድቶ ለኔ እግሬ ላንተ ደሞ ልብህ ላይ አርፎ ወድያው ክቡር መስዋዕትነት የተቀበልከው የትግል ጓደኛዬ ዛሬ ትዝ አልከኝ፣ካንተ ጋር መስዋእት ሆኜ በነበር ብዬ ተመኘሁ!ግን ማን በሰጠኝ!በምን ዕድሌ!

ክቡር ህይወታችሁን የከፈላቹ ጓደኞቼ እንኳንም አሁን እየሆነ ያለው ነገር አላያችሁ፣ አልሰማችሁ፤ትገረሙ ነበር!ጉድ ነው!
እጃችን፣እግራችን እና የዓይን ብርሃናችን ያጣነው ለዚህ ነበር እንዴ?፣ከ800ሺ ወጣቶች ያጣነው፣እንደ ህዝብ ከሰው በታች የሆንነው ለእናንተ ስልጣን(ወንበር) ነው እንዴ?፣ይሔ ሁሉ ዋጋ ለእናንተ ስልጣን ነው እንዴ?

የትግራይ ህዝብ ሆይ እኔ በግሌ ይቅርታ ልጠይቅህ ፍቀድልኝ፤ታግዬ ነፃነትህ ስላላስጠበቅኩልህ፣ከዚህም አልፎ ማስደፈርያህ እና ማስገደያህ ሆንኩኝ፤ወደ ትግል የወረድኩት እኮ ነፃ ላወጣህ መስሎኝ ነበር፤ግን ለካ እንደዛ አይደለም።ይቅርታ!ይቅርታ አድርግልኝ!

ዘልአለማዊ ክብር ለጀግና ሰማእታት ይሁን