Get Mystery Box with random crypto!

በጅማ ፣ የየም ፣ ኮንታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን የሚያገለግሉት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ዛ | Natnael Mekonnen

በጅማ ፣ የየም ፣ ኮንታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን የሚያገለግሉት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ዛሬ በጅማ ዞን ፖሊስ ታስረው መዋላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስታወቀች

በዕለቱ በሊቀ ጳጳሱ ላይ በተፈጸመው ሕገ ወጥ ድርጊት ቤተክርስቲያኗ በአሁኑ ሰዓት በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ እየተሰጠች ነው። መግለጫውን መልአከ ሕይወት አባ ወልደ ኢየሱስ ሠይፉ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የቋሚና ጊዜያዊ ፕሮጀክቶች መምሪያ ኃላፊ የሰጡ ሲሆን ከሃያ ዓመታት በላይ በጅማ የም ኮንታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን የሚያገለግሉት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ዛሬ በጅማ ዞን ፖሊስ ታስረው መዋላቸውን ገልጸው ድርጊቱን አውግዘዋል።

በአሁኑ ሰዓት ሊቀ ጳጳሱ በግዳጅ ከጅማ እንዲወጡ መገዳቸውን ከሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለ የኢትዮጵያን የሃይማኖት ተቋማት ጠቅላይ ጸሐፊ ጋር ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪ በሕገ ወጥ ከተሾሙ አባቶች መካከል ይቅርታ ጠይቀው የተመለሱትና ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታቸውን የተቀበለው መጋቤ ሐዲስ አባ ጸጋዘአብ አዱኛ ከመንበረ ፓትርያርክ ማረፊያ ተይዘው ወዳልታወቀ ሥፍራ መወሰዳቸውን ገልጸዋል።

በመግለጫው መንግሥት ሕግ የማስከበር ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀው ቅዱስ ፓትርያርኩ በሚገኙበት ግቢ አፈና መፈጸሙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኦርቶዶክሳውያንን ያሳዘነ መሆኑን ገልጸዋል።