Get Mystery Box with random crypto!

'በአዋሽ አርባ ዛሬ የተመለከትነው የተቀናጀ የውጊያ ልምምድ ኢትዮጵያ ጦርነትን የሚያስቀር ሀይል | Natnael Mekonnen

"በአዋሽ አርባ ዛሬ የተመለከትነው የተቀናጀ የውጊያ ልምምድ ኢትዮጵያ ጦርነትን የሚያስቀር ሀይል መገንባቷን ነው"- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "በአዋሽ አርባ ዛሬ የተመለከትነው የተቀናጀ የውጊያ ልምምድ ኢትዮጵያ ጦርነትን የሚያስቀር ሀይል መገንባቷን ነው" ሲሉ ገለጹ፡፡
በውጊያ ልምምዱ አየር ሀይል ፣ ከባድ መሳሪያ ፣ልዩ ሀይል እና እግረኛ ተቀናጅቶ ውጊያን በአጭር የሚያስቀርባቸውን መንገዶች መመልከታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው አስፍረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየቀኑ አይናችንን ከምንፈልገው ህልም እና ተግባራችን እንድናነሳ የሚሹ ሀይሎች ስላሉ የጦር መኮንኖች ዋና ተግባር የሚሆነው ጦርነትን የሚያስቀር ሀይል መገንባት ነው ብለዋል።