Get Mystery Box with random crypto!

Muktarovich Ousmanova

የቴሌግራም ቻናል አርማ muktarovichousmanova — Muktarovich Ousmanova
ርዕሶች ከሰርጥ:
Wazemaalert
Ebc
Pmoethiopia
Westandwithendf
Londonmarathon
Berlinmarathon
Inbox
Fastmereja
Ethiopia
Southafrica
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @muktarovichousmanova
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 72.83K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopia forever

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-04-11 17:21:15
#ሰበር
አቶ ስንታየሁ ቸኮል የዋስ መብት ተፈቀደላቸው።

በ እስር ከሁለት ወራት በላይ የቆዩት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃለፊ እና የስራ አስፈፃሚ አባሉ አቶ ስንታየሁ ቸኮል ዛሬ በልደታ ፍ/ቤት በቀጠሯቸው ቀርበው ነበር። ፍርድ ቤቱም በ10,000 ብር ዋስ እንዲወጡ ፈቅዷል።

በአሁኑ ሰአት የዋስ ብሩ ተከፍሎ የመልቀቂያ ወረቀቱ ታስረው ወደሚገኙበት የፌደራል ፖሊስ ተወስዷል። ቤተሰቦቹ ከእስር ቤቱ እስኪለቀቁ እየጠበቁ ይገኛሉ።
16.1K views14:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 17:14:05
ወላጅ አባቱን በዘነዘና ቀጥቅጦ የገደለው ግለሰብ በዕድሜ ልክ ጽኑ እሥራት ተቀጣ፡፡

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ሀደሮ ጡንጦ ዙሪያ ወረዳ ሌሾ ማዞሪያ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሙጉንጃ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ወላጅ አባቱን የገደለው አቶ መሐሩ ዮሐንስ የተባለ ግለሰብ ነው የከምባታ ጠምባሮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዕድሜ ልክ ጽኑ እሥራት እንዲቀጣ የወሰነው፡፡

ተከሳሽ መሐሩ የሐንስ የተባለ በከምባታ ጠምባሮ ዞን በሀደሮ ጡንጦ ዙሪያ ወረዳ ሌሾ ማዞሪያ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሙጉንጃ ተብሎ በሚጠራበት ቦታ ሟች ዮሐንስ ኬዕሚሶ የተባለ አባቱን የሰበሰብከውን ንብረት አትበላም ብሎ ስዝት ቆይቶ ጥር 2 ቀን 2015 ዓ/ም ከምሽቱ 4 ሰዓት ሟች ተኝቶ ባለበት በዘነዘና ጭንቅላቱን በመቀጥቀጥ ገድሏል ተብሎ በወንጀል ህግ አንቀጽ 539/1/ሀ/ ላይ የቀረበበትን ክስ አቃቤ ህግ በሰውና በሰነድ ማስረጃ አረጋግጦ ተከሳሽ ክሱን እንዲያስተባብል ታዞ መከላከያ ማስረጃ የሌለው መሆኑን በጽሑፍና በቃል ማስረጃ የለኝም ብሎ በማረጋገጡ የከምባታ ጠምባሮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወንጀል ችሎት 03/08/2015 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሹን በዕድሜ ልክ ጽኑ እሥራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

ከምባታ ጠምባሮ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
15.4K views14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 14:10:07
በአልን ምክንያት በማድርግ

➨ ከ 25 - 35% ቅናሽ በእያንዳንዱ አፓርታማዎች ላይ

  የካሬ አማራጮች፦

          107 ካሬ
          110 ካሬ
          115 ካሬ
          120 ካሬ
          127 ካሬ
          138 ካሬ
          145 ካሬ
          161 ካሬ

በተጨማሪ 145 ካሬ G+1

ቤት በአገር ቤት ከአያት

መልካም ትንሳኤ

@Tsion_won

https://t.me/nvhfjnfdhnojbfedgjn

ለበለጠ መረጃ (Whatsapp/direct)፦ በ 0904444670 ወይም 0912287354 ይደውሉ
16.6K views11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 14:09:14
አርቲስት ቴዲ አፍሮ በኢትዮጵያ ከእስራኤል አምባሳደር ጋር ተገናኘ

ኢትዮጵያዊው የሙዚቃ ባለሙያ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር የሆኑትን አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ጋር ተገናኙ።

አምባሳደር አለልኝ በትዊተር ገፃቸው እንዳሰፈሩት ከአርቲስት ቴዲ አፍሮ ጋር በነበራቸው ቆይታ የኢትዮጵያ እና እስራኤልን የባህል ግንኙነት ስለማሳደግ ተወያይተናል ብለዋል። የባህል ግንኙነቱም በዋናነት በፈጠራ ባለሙያዎች እና የጥበብ ሰዎች እንዲታገዝ ለማድረግ ትኩረት ማድረጋቸውንም በኢትዮጵያ የእስራኤል አማባሳደሩ ገልፀዋል።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ቴዲ አፍሮ በ2019 በእስራኤል ሀገር የሙዚቃ ጉዞ በማድረግ የሙዚቃ ስራዎቹን አቅርቦ ነበር።
16.3K views11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 12:20:53
መስከረም አበራ “ለኢ-መደበኛ አደረጃጃቶች ወታደራዊ ስልጠና እና የተኩስ ልምምድ ስትሰጥ ነበር” ሲል ፖሊስ ለፍርድ ቤት ክስ አቅርቧል።ፍርድ ቤቱም ነገሩን ለማጣራት 13 ቀን ቀጠሮ ሰጥቻለዉ ብሏል።

ከጄነራል ተፈራ ጋር ስለታየች መሆኑ ነው።

ጀነራል መስከረም ማስተኮስም ትችላለች ለካ።

አቶ ልደቱ አያሌዉን " የቄሮ አስተባባሪ እና ቄሮን አደራጅቶ አመፅ እንዲቀሰቀስ አድርጓል" ተብሎ ነበረ። ያው ከጃዋር ጋር ከመስከረም 25 በኋላ መንግስት የለም በማለቱ ነበረ።
ክስ ትጠላለህ
18.0K views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 18:20:41
በአማራ ክልል አጣዬ ከተማ፤ “በከባድ መሳሪያ የታገዘ” የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ መሆኑን ነዋሪዎች ገለጹ

በአማራ ክልል፤ ሰሜን ሸዋ ዞን፤ አጣዬ ከተማ ዛሬ ከንጋት ጀምሮ የተከፈተው በከባድ መሳሪያ የታገዘ ተኩስ እስከ አመሻሽ ድረስ መቀጠሉን ስድስት የከተማዋ ነዋሪዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ በከተማዋ ተኩስ እንዳለ ቢያረጋግጡም፤ በየትኛው አካል የተፈጸመ እንደሆነ እስካሁን አለመታወቁን ገልጸዋል።

የኤፍራታና ግድም ወረዳ ዋና ከተማ በሆነችው አጣዬ ከተማ ተኩስ የተከፈተው፤ ዛሬ ሰኞ ሚያዝያ 2፤ 2015 ከንጋቱ 12 ሰዓት ገደማ ጀምሮ መሆኑን የከተማይቱ ነዋሪዎች ተናግረዋል። የመጀመሪያው የተኩስ ድምጽ የተሰማው “አላላ” በተባለው የኤፍራታና ግድም ወረዳ ቀበሌ አካባቢ እንደሆነ ነዋሪዎቹ አስረድተዋል።

የአጣዬ ከተማ ነዋሪዎች “በዲሽቃ እና ሌሎች ከባድ መሳሪያዎች የታገዘ” ሲሉ የጠሩት ተኩስ የተከፈተው፤ የከተማዋን ዙሪያ ከከበቡት ተራሮች ላይ “በሁሉም አቅጣጫ ነው” ይላሉ። የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አሳልፍ ደርቤ፤ “አጣዬ ዙሪያውን ጦርነት አለ” ሲሉ ተኩሱ በሁሉም አቅጣጫ የሚሰማ መሆኑን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጠዋል።

* * ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2023/10574/
15.4K views15:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 18:17:53
ለሃይስኩል እና በዩንቨርስቲ የመጀመሪያ ድግሪ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዚህ ቻናል
1) ለማትሪክ(ESSLCE)ዝግጅት መለማመጃ ፈተና ከሙሉ ማብራሪያ መልሶች፣
2) ለመውጫ ፈተና(Exit Exam) ዝግጅት መለማመጃ ፈተና ከሙሉ ማብራሪያ መልሶች፣
እንዲሁም ጠቃሚ መፅሃፍትና አጫጭር ኖቶች ተዘጋጅቶ እየቀረበ ስለሆነ join በማድረግ ተጠቃሚ ይሁኑ። ለወዳጅ ለጓደኛ ለልጆቻቹ ሼር አርጉላቸው

https://t.me/TutorialPointEth
15.0K views15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 17:47:04
የሶማሌ ክልል ካቢኔ የልዩ ሃይል አባላት ወደ ሌሎች የፀጥታ መዋቅር እንዲገቡ የቀረበውን ሃሳብ በሙሉ ድምፅ ደገፈ።
********
ካቢኔው ዛሬ በደረገው ስብሰባ ልዩ ኃይል አባላትን ወደ ሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች እንዲገቡ ለማድረግ የተወሰነው ውሳኔ ዕቅድ በሙሉ ድምጽ ደግፎታል።

ካቢኔው የሶማሌ ክልሉ ልዩ ኃይል ኢትዮጵያ አስቸጋሪ ፈተና በገጠማት ጊዜ ሕይወታቸውን ሠውተዋል። በክልላቸው መንግስት የተሰጣቸው ግዳጆችን በጀግንነት በመወጣት የሃገራችንን ዳር ድንበር አስከብረዋል ያለ ሲሆን የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ለሀገራችው የሚችሉትን ሁሉ ያደረጉ፤ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በጀግንነት የተወጡ፤ ለወደፊትም በተሻለና ይበልጥ ኢትዮጵያን ማገልገል በሚያስችላቸው ቦታዎች ላይ እንደ የፍላጎታቸው ተመድበው እንዲያገለግሉ የተወሰነው ውሳኔ የክልሉ መንግስት በመደገፍ አስፈላጊ የሆነውን ሙሉ ደጋፍ ይሰጣል ብሏል።

በዚህም መሰረ ካቢኔው ተከታዮቹን ውሳኔዎች አሳልፏል።

የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አመራሮችና አባላት በውሳኔው ላይ እንዲወያዩበት ይደረጋል።

የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይሎች እንደ ምርጫችው ወደ መከላከያ፣ ወደ ፌደራል ፖሊስ ወይም ወደ ክልል ፖሊስ የተለያዩ የጸጥታ መዋቅሮችን እንዲቀላቀሉ ይደረጋል።

ጉዳዩ የትጥቅ መፍታት ጉዳይ ሳይሆን የበለጠ ሥልጠናና ትጥቅ አግኝተው ሀገርን በተሻለ ወደ ሚያገለግሉባቸው መዋቅሮች እንዲገቡ የሚያደርግ መሆኑን በመገንዘብ የክልሉ ካቢኔ በዛሬው ውሎው በሰፊው ውይይት ካደረገበት በኃላ ውሳኔውን በሙሉ ድምጽ መደገፉ ተገልፆአል።

Source
Somali fast Info
16.2K views14:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 17:12:15
ወደ ፊት የሚቋቋሙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች፤ ራስ ገዝ ሆነው እንደሚደራጁ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

በፌደራል መንግስት ወደ ፊት የሚቋቋሙ አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች፤ ራስ ገዝ ሆነው እንደሚደራጁ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ተናገሩ። ወደ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ከሚገቡ ተማሪዎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት፤ ከፍለው የሚማሩ መሆን እንዳለባቸውም ሚኒስቴር ዴኤታው አስታውቀዋል።

ዶ/ር ሳሙኤል ይህን ያሉት፤ ስለ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎችን ለመደንግግ በወጣው የአዋጅ ረቂቅ ላይ በተጠራ የአስረጂ መድረክ ላይ ነው። በተወካዮች ምክር ቤት አዳራሽ ዛሬ ሰኞ ሚያዚያ 2፤ 2015 የተደረገውን ይህን የአስረጂ መድረክ የጠራው፤ የፓርላማው የሰው ሃብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ነው።

የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታው ዶ/ር ሳሙኤል በዚሁ መድረክ ላይ ባቀረቡት ገለጻ፤ ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ የሚሆኑበትን ሂደት አብራርተዋል። “አዋጁ ባስቀመጠው መልኩ ዩኒቨርሲቲዎች መስፈርት ሲያሟሉ፤ ደንቦቻቸው በዚህ አዋጅ መሰረት መልሶ እንዲከለስ ይደረግ እና ራስ ገዝ ሆነው መልሰው ይደራጃሉ” ብለዋል። ለፓርላማው የቀረበው የአዋጅ ረቂቅ፤ “ጠንካራ የፋይናንስ አቅም እና አካዳሚያዊ ተወዳዳሪነት” ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመሆን ከሚያበቁ መስፈርቶች መካከል እንደሚካተቱ አስፍሯል።

ይህ አዋጅ በፓርላማ ከጸደቀ በኋላ “ራስ ገዝ” የሚሆኑት፤ አሁን በትምህርት ሚኒስቴር ስር የሚተዳደሩ ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ አለመሆናቸውን ዶ/ር ሳሙኤል በዛሬው ማብራሪያቸው ጠቁመዋል። “መስፈርቱን አሟልተው የሚፈጠሩ ዩኒቨርሲቲዎች ሲኖሩ፣ ወደፊት አዲስም ቢሆኑ፤ እንደራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ይደራጃሉ” ሲሉ አዋጁ ወደፊት የሚቋቋሙ ዩኒቨርሲቲዎችንም የሚመለከት መሆኑን ሚኒስቴር ዴኤታው አስረድተዋል።
Ethio Insider
15.4K views14:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 13:00:42
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 19ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።
18.8K views10:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ