Get Mystery Box with random crypto!

Muktarovich Ousmanova

የቴሌግራም ቻናል አርማ muktarovichousmanova — Muktarovich Ousmanova
ርዕሶች ከሰርጥ:
Wazemaalert
Ebc
Pmoethiopia
Westandwithendf
Londonmarathon
Berlinmarathon
Inbox
Fastmereja
Ethiopia
Southafrica
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @muktarovichousmanova
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 72.83K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopia forever

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-04-27 10:53:15
መቀሌ ጎዳና ሽመልስ ከነዳ
ተሳፋሪ ሆኖ ጌታቸው ረዳ
እኛስ ደስ ይለናል የሞተ ተጎዳ
:
19/08/15

ከወሎ ሰፈር አደባባዩ ጋር ካለው ጎሚስታ ማዶ ጫማዬን እያስቦረሽኩ :ታክሲ የሚጠብቁትን ሰዎችም እያየሁ አንድ ሰውዬ ሰላም ሲሉኝ አይ እሳቸውን ከማወራ ስልኬን ብጎረጉር ይሻላል ብዬ ጎንበስ ስል እና ይሄን ፎቶ አይቼ ቀና ስል የመጣልኝ ግጥም

Andualem Buketo Geda
24.8K views07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 19:25:15
ከአያት አፓርታማ ለመግዛት ትክክለኛ ጊዜ!    

ያሉንን አፓርታማዎቹን ወደ ማስረከብ  ሂደት ላይ ሰለ ሆንን የመጨረዎቹን የአያትን   አፓርታማዎች በመግዛት ተጠቃሚ ይሁኑ ::   

ለተወሰነ ጊዜ በሚቆይ በ15%ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤት ባለቤት ይሁኑ    

እንደ አከፋፈልዎ እስከ 30% የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተንሎታል    

የ ነገ እቅድዎን ዛሬ ያሳኩ !!!      

ለበለጠ መረጃ 
https://t.me/nvhfjnfdhnojbfedgjn

+251912287354 / +251904444670 በቀጥታ ወይንም በቴሌግራም ፣ ዋትሳፕ ፣ ኢሞ ይደውሉ
7.5K views16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 19:24:36
ሁለት ዜናዎች

1፤

ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ዛሬ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ታንዛኒያ መግባታቸውን የመንግሥት ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ደመቀ ዛሬ በታንዛኒያ የወደብ ከተማ ዛንዚባር ከአገሪቷ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሳሉሁ ጋር በኹለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደተወያዩ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴርን ጠቅሰው ዘግበዋል።  ደመቀ ዛሬ ታንዛኒያ የገቡት፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ መንግሥታቸው ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር በታንዛኒያ አስተናጋጅነት ነገ ማክሰኞ የሰላም ድርድር እንደሚጀምር በገለጡ ማግስት ነው። ደመቀ ከታንዛኒያ ቀጥሎ በኮሞሮስ፣ ቡሩንዲ እና ኡጋንዳ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተገልጧል።

2፤

የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት ዛሬ ባዋለው ችሎት በ"ኡትዮ ንቃት" የዩትዩብ ጣቢያ ባለቤት መስከረም አበራ ላይ ተጨማሪ 10 የምርመራ ቀናት መፍቀዱን የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። መርማሪ ፖሊስ ባለፉት 13 ቀናት ከተጠርጣሪዋ እጅ ያዝኳቸው ባላቸው የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች ላይ ምርመራ እንዲደረግለት ለሚመለከተው አካል ልኮ የምርመራ ውጤቱን መቀበሉን፣ የተጠርጣሪዋን የገንዘብ ዝውውር ለማወቅ ለባንክ ደብዳቤ መጻፉን፣ ከመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን ማስረጃ ለማግኘት ጥያቄ ማቅረቡንና ሌሎች ቀሪ የምርመራ ሥራዎችን እያከናወነ መኾኑን ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። ፖሊስ መስከረምን ከሁለት ሳምንት በፊት በቁጥጥር ስር ያዋላት፣ "ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት" ወንጀል ጠርጥሬያታለሁ በማለት ነበር።
ዘገባው የዋዜማ ነው
7.4K views16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 15:30:00
ማነው በፍጡራኑ ሁሉ፣ በቅጠላቅጠሉ ሁሉ፣ በነፍሳቱ ሁሉ ላይ የሚገራርሙ ዲዛይኖችን፣ የሚገራርሙ አለሮችን experiment ያደረገው?

ማነው.. በቢሊየን የሚቆጠሩ የዚችን ዓለም ፍጥረታት.. ከደቃቋ ኢምንቷ ፍጥረት እስከ ግዙፋኑ ፍጡራን ድረስ.. ዲዛይናቸውን ቁጭ ብሎ ያለመታከት የነደፈው? ማነው ይሄ አስገራሚ ታላቅ አርቲስት?

ማነው የዚች ጉደኛ ዓለምና ሞላዋ አርኪቴክት? ማነው ይሄ ግራንድ ማስተር? እጅግ ይደንቀኛል! ተደምሜ አላበቃም!

በባህሩ፣ በአየሩ፣ በአፈሩ፣ በሠማይ በምድሩ ላይ በእንዴት ያለ ዲዛይን ስንቱን መዓት ፍጡር ነው በዲዛይኑ የተራቀቀበት? በስንቱ የአዕዋፍ ገላ ላይ? በስንቱ አበባ?..

በዳመናው በከዋክብቱ... ተቆጥረው በማያልቁ ቀለማቱ... በስንቱ ነገር ነው የተራቀቀው ይሄ አርቲስት? እጅግ.. እጅግ.. እጅግ ያስደንቀኛል!

ተደምሜ አላባራም...!
Via Assaf Hailu
12.0K views12:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 11:43:33
የምስራች ለመንግስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች

ለመውጫ ፈተና በብቃት የሚያዘጋጅዎ Mock እና Model Exam በ Online ይለማመዱ!

አድቫንስድ የትምህርት ማማከር አገልግሎት ማዕከል ከአተርቴክ የቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ ጋር በመተባበር ፦

➭ በዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሮችና መምህራን የተዘጋጀ፣
➭ የትምህርት ሚኒስቴርን የብቃት መስፈርት መሰረት ያደረገ፣
➭ ተገቢውን ሳይንሳዊ የምዘና ሥርዓት የተከተለ፣
➭ ለአንድ ፕሮግራም ከ1,000 በላይ መለማመጃ ጥያቄዎችን የያዘ፣
➭ ሁሉንም የፈተና ኮርሶች ያካተተ፣
➭ ለእያንዳንዱ ጥያቄ መልስና ማብራሪያ የያዘ፣
➭ በየትኛውም ቦታ በማንኛውም ሰዓት የሚያገኙት የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) መለማመጃ አቀረበልዎ!

ለሙሉ መረጃው፡-

➧ www.http://elts.com.et ይጎብኙ፣
➧ https://t.me/aec_ethiopia ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

#AdvancedEducationalConsultingCenter
14.2K views08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 11:16:13
ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ለአያክስ የሴቶች ቡድን ለመጫወት ፈረመች

ሚያዝያ 16/2015 (ዋልታ) ኢትጵያዊቷ እግር ኳስ ተጫዋች ሊሊ ዮሃንስ ለአያክስ አምስተርዳም ክለብ ፕሮፌሽናል የሴቶች ቡድን ለመጫወት ፈረመች፡፡

ሊሊ የመጀመሪያውን ፕሮፌሽናል የተጫዋችነት ውል የፈረመችው ባለፈው ሐሙስ ሲሆን በስምምነቱ መሰረትም እ.ኤ.አ. ከሰኔ 30/2023 እስከ ሰኔ 30/2026 በአያክስ እንደምትቆይ ክለቡ በድረ-ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል፡፡

በአሜሪካ ስፕሪንግፊልድ በ2007 የተወለደችው ሊሊ ዮሃንስ ከባለፈው ዓመት የእግር ኳስ መርኃ ግብር መጀመሪያ ጀምሮ በአያክስ የሴቶች ታለንት ቡድን ውስጥ እየተጫወተች እንደምትገኝ መረጃው ያመለክታል፡፡

ሊሊ ለክለቡ 17 የሊግ ጨዋታዎችን አድርጋ አራት ግቦችን በማስቆጠር እና ስድስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ማቀበሏን መረጃው ጠቁሟል፡፡

ሊሊ በመጭው ዓመት የጨዋታ መርኃ ግብር መጀመሪያ ላይ ቡድኑን ትቀላቀላለችም ተብሏል::

ሊሊ ዮሐንስ በዜግነት አሜሪካዊ ስትሆን ለአሜሪካ ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን እንደምትጫወት ተመልክቷል፡፡
14.4K views08:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 19:25:37 ሰበር
መንግስትና ኦነግ ሸኔ ከነገ በስቲያ በሀገረ ታንዛኒያ እንደሚደራደሩ ታወቀ። ይህን ጠቅላይ ሚኒስትሩ መናገራቸውን የሚኒስትሮች ምክርቤት ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ዳባ በፌስቡክ ገፃቸው ፅፈዋል። ሸኔ አሸማጋይ ካልገባ በቀር አልደራደርም ብሎ ነበረ።
18.6K viewsedited  16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 17:59:27
በጦርነት ይብቃ
ሰላም ይፅና መርሃግብር ላይ ጌታቸው ረዳ የተናገረው

"የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እንዲፋጠን የጠሚ አብይ አህመድ ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው። አሁንም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፈጣን እርምጃዎች የተጀመረውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ መስራት አለበት እላለሁ።

የትግራይ ህዝብ ጦርነት ሰልችቶታል። ከማንም ጋር ጦርነት መግባት አንፈልግም። ከአማራም ከአፋርም የሚያቀራርብ እንጂ የሚያቃቅር ነገር የለንም።

ትናንት በአፋር በኩል የሰላም ባስ አገር አቋራጭ አልፏል። ሐጂ አወል ይህንን ለማጠናከር መስራት ይገበዋል።

በተመሳሳይ ከአማራ ክልል ጋር በተያያዘም ዶክተር ከፋለ ኃላፊነት ወስደህ መስራት አለብህ ለማለት እፈልጋለሁ።

ዶክተር አብይ በጀመረው እጁ በሌሎች አካባቢዎች የሚታዩ ግጭቶችን በሆደ ሰፊነት ለመፍታት መስራት እንደለበት ለመጠቆም እፈልጋለሁ!

በመጨረሻ ከይዋጣልን መንፈስ ወጥተን የፍቅር፣ የስራ ቋንቋ መጀመር አለብን። ሰላም እንዲፀና የትግራይ ክልል ጊዚያዊ መንግስት የበኩሉን ይሰራል"

አቶ ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ክልል ጊዚያዊ መስተዳድር ፕሬዚደንት
1.8K views14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 15:34:16
ከአያት አፓርታማ ለመግዛት ትክክለኛ ጊዜ!    

ያሉንን አፓርታማዎቹን ወደ ማስረከብ  ሂደት ላይ ሰለ ሆንን የመጨረዎቹን የአያትን   አፓርታማዎች በመግዛት ተጠቃሚ ይሁኑ ::   

ለተወሰነ ጊዜ በሚቆይ በ15%ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤት ባለቤት ይሁኑ    

እንደ አከፋፈልዎ እስከ 30% የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተንሎታል    

የ ነገ እቅድዎን ዛሬ ያሳኩ !!!      

ለበለጠ መረጃ 
https://t.me/nvhfjnfdhnojbfedgjn

+251912287354 / +251904444670 በቀጥታ ወይንም በቴሌግራም ፣ ዋትሳፕ ፣ ኢሞ ይደውሉ
6.1K views12:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 15:33:40
ሠበር

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የአሜሪካ ዜጎችን ሊያወጣ ወደ ሱዳን እየገባ ነው ማለት ነው?

ዘርዘር ያለ ነገር እየፈለግኩ ነው። እመለሳለሁ።

የአሜሪካ ኢምባሲ አመስግኗል ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት።

በሌላ ዜና በሱዳን የሚኖሩ በርካታ የውጭ ሀገር ዜጎች በመተማ በኩል በጦርነቱ ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ድምበር ጥሰው እየገቡ መሆናቸውን የዓለም ዓቀፍ መገናኛ ብዙኀን እየገለፁ ነው።
6.0K views12:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ