Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች፤ በቀጣዩ 2016 የትምህርት ዘመን በተማሪ | Muktarovich Ousmanova

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች፤ በቀጣዩ 2016 የትምህርት ዘመን በተማሪዎች ወርሃዊ ክፍያ ላይ ጭማሪ ለማድረግ የሚያስችላቸውን “ፕሮፖዛል” አዘጋጅተዋል። ወደ አንድ ሺህ ገደማ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች፤ በሚያደርጉት የክፍያ ጭማሪ ላይ ከተማሪ ወላጆች ጋር ውይይት ማካሄዳቸውም ተነግሯል።

በእነዚህ ውይይቶች ላይ “ከስምምነት ላይ ተደርሶባቸዋል” የተባሉ የዋጋ ጭማሪ “ፕሮፖዛሎች”፤ ለአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት እና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ማቅረባቸውም ተገልጿል። “ፕሮፖዛሎቹ” ከ20 እስከ 100 በመቶ የሚደርሱ የዋጋ ጭማሪ የያዙ መሆናቸውን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።

ባለስልጣኑ በትላትናው ዕለት ለትምህርት ቤቶቹ ባሰራጨው ደብዳቤ፤ ጭማሪውን በተመለከተ “ከወላጆች ጋር በቂ መግባባት ላይ ሳይደርሱ” ተግባራዊ ማድረግ እንደማይችሉ አስጠንቅቋል። በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ የግል ትምህርት ቤቶች “በምን ያህል መጠን ወርሃዊ ክፍያ ለመጨመር አቅደዋል?” የሚለውን ለመመልከት ከላይ የተያያዘውን መረጃ ይመልከቱ። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

* ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ:- https://ethiopiainsider.com/2023/10883/