Get Mystery Box with random crypto!

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ፤ ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ተወካዮች ጋር ሊወያዩ ነው የአሜሪካ የ | Muktarovich Ousmanova

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ፤ ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ተወካዮች ጋር ሊወያዩ ነው

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሐመር በሎስ አንጀለስ ከሚገኙ የኢትዮ-አሜሪካ ማህበረሰብ አባላት ጋር ሊወያዩ ነው። ልዩ ልዑኩ በሎስ አንጀለስ ቆይታቸው፤ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የሶማሌ እና የትግራይ ማህብረሰብ ተወካዮችን እንደሚያነጋግሩ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ዛሬ ረቡዕ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ማይክ ሐመር ከዛሬ ጀምሮ ለዘጠኝ ቀናት በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ በሚያደርጉት ቆይታ፤ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እንዲያበቃ ያደረገውን የደቡብ አፍሪካ የግጭት ማቆም ስምምነትን ጨምሮ በኢትዮጵያ ስላሉ ወቅታዊ ጉዳዮች እንደሚወያዩ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ገልጿል። የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑኩ ከአሜሪካ ኢትዮጵያውያን ጋር በሎስ አንጀለስ ከተማ የሚያደርጉት ውይይት፤ “ሰላምን በማስፈን እና የሴቶችን አቅም በማጎልበት” የሚያተኩር ነው ተብሏል።

“ዩናይትድ ውመን ኦፍ ዘ ሆርን” በተባለ የሲቪክ ድርጅት የተዘጋጀው ይህ ውይይት የሚካሄደው፤ 500 የሚጠጉ ሰዎችን ማስተናገድ በሚችለው በቦብ ሆፕ ፓትሪዮቲክ አዳራሽ ነው። አምባሳደር ሐመር በሎስ አንጀለስ ቆይታቸው፤ ከከተማይቱ ከንቲባ ካረን ባስ ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ተገልጿል። ካረን ባስ ባለፈው ህዳር ወር ላይ የሎስ አንጀለስ የመጀመሪያዋነበር ሴት ከንቲባ ሆነው ከመመረጣቸው በፊት፤ በኮንግረስ አባልነታቸው ወቅት ኢትዮጵያን በተመለከተ በሚያራምዷቸው ጠንካራ አቋማቸው ይታወቁ የነበሩ ናቸው።

* * ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2023/10892/