Get Mystery Box with random crypto!

በሽብር ወንጀል የተጠረጠረው ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረበ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለ | Muktarovich Ousmanova

በሽብር ወንጀል የተጠረጠረው ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረበ

ፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለበት ጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ ባለፈው ቅዳሜ ምሽት መግባቱ የተነገረው ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፤ ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 1፤ 2015 ፍርድ ቤት ቀረበ። ጎበዜ ከሌሎች አምስት ግለሰቦች ጋር ፍርድ ቤት የቀረበው፤ በሽብር ወንጀል ተጠርጥሮ መሆኑን የፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

ፖሊስ ይህን የገለጸው የእነ ጎበዜን ጉዳይ ለመመልከት ዛሬ ተሰይሞ ለነበረው፤ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው። ጋዜጠኛ ጎበዜን ጨምሮ ስድስት ተጠርጣሪዎች የቀረቡበት የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ የተከፈተው የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ መምህር በሆኑት በአቶ ሲሳይ አውግቸው ስም ነው።

ስድስቱን ተጠርጣሪዎች ችሎት ፊት ያቀረባቸው የፌደራል ፖሊስ፤ ግለሰቦቹ “የሽብር ድርጊት ተግባር በመፈጸም በንጹሃን ህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሳቸው በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው” በእስር ላይ እንደሚገኙ ገልጿል። ፖሊስ ስድስቱን ተጠርጣሪዎች “ህገ መንግስቱን እና ህግ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመቀየር በመንቀሳቀስም” ወንጅሏቸዋል።

ጋዜጠኛ ጎበዜን ወክለው ችሎት ፊት የቀረቡት ጠበቃ አዲሱ አልጋው፤ ፖሊስ “ማን በየትኛው የወንጀል ድርጊት የተሳተፈ እንደሆነ የገለጸው ነገር የለም” ሲሉ የተጠርጣሪዎች የወንጀል ተሳትፎ ፖሊስ በጽሁፍ ባቀረበው የጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ ላይ አለመገለጹን ተናግረዋል። አቶ አዲሱ አክለውም ደንበኛቸው “ጥፋት ፈጽመዋል ከተባለ እንኳን በሚዲያ ስራቸው አማካኝነት ነው። ስለሆነም የምርመራ ሂደቱ መመራት ያለበት በመገናኛ ብዙሃን አዋጁ ነው” የሚል መከራከሪያ አቅርበዋል።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2023/10862/