Get Mystery Box with random crypto!

ኦነግ ሸኔ በምዕራብ እና በምስራቅ ሸዋ ዞን የመንግሥት ጦር ሰራዊት ጥቃት ከፍቶብኛል አለ ===== | Muktarovich Ousmanova

ኦነግ ሸኔ በምዕራብ እና በምስራቅ ሸዋ ዞን የመንግሥት ጦር ሰራዊት ጥቃት ከፍቶብኛል አለ
=======#=======

እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ በሚጠራውና በመንግሥት "ኦነግ ሸኔ" ተብሎ በሚጠራው ቡድን፤ ከትላንት ሚያዚያ 30/2015 ማለዳ ጀምሮ በመንግሥት ጦር አዲስ ጥቃት ተከፍቶብኛል ሲል በቡድኑ ቃል አቀባይ በኩል አስታውቋል።

የቡድኑ ቃል አቀባይ አዳ ታርቢ በቲውተር ገፃቸው እንዳሰፈሩት፤ የመንግሥት ጦር በምዕራብ ሸዋ ዞን ጀልዱ እና በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳሚ ቱሉ በኩል ጥቃት ተከፍቶብናል ብለዋል።

በመንግሥት እና በኦነግ ሸኔ መካከል ለዘጠኝ ቀናት ያህል በታንዛኒያ የተካሄደው የሰላም ውይይት ባለመግባባት መጠናቀቁን አዲስ ማለዳ ከዚህ ቀደም መዘገቧ ይታወሳል። ትላንት ተከፈተ ስለተባለው ጥቃት ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ከመንግሥት በኩል ምንም የተባለ ነገር የለም።