Get Mystery Box with random crypto!

ምን ብዬ እንደምጽፍም ግራ ገባኝ'ኮ (ዘካሪያስ ኪሮስ) እናቷን አባቷን ባለቤቷን ሶስት ልጆቿ | Muktarovich Ousmanova

ምን ብዬ እንደምጽፍም ግራ ገባኝ'ኮ
(ዘካሪያስ ኪሮስ)
እናቷን አባቷን ባለቤቷን ሶስት ልጆቿን እህቷን ከአራስ ልጇ ጋር ወንድሟን ከአራት ልጆቹ ጋር በአጠቃላይ ሃያ አንድ ቤተሰቦቿን በግፈኞች የተገደሉባት ምስኪን እህታችን ናት ። ጠይባ ሁሴን መሐመድ ትባላለች ።

ጠይባ ሁሴን መሐመድ በዱባይ ለሰባት ዓመታት ፣ በሳዑዲ አረቢያ ደግሞ ለስምንት ዓመታት ሰርታለች ። በሰው አገር የተንከራተችላቸው ቤተሰቦቿ ወለጋ ጊቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ
ውስጥ ምንም ባላወቁት ሁኔታ ተገድለውባታል ።

በ1977 ዓ/ም ከኮምቦልቻ እና ከከሚሴ እናት እና አባቷ ወደ ወለጋ እንደሄዱም ሰምቻለሁ ። ጠይባ የተወለደችው ወለጋ ነው ።

ምን ብለን የትኛውስ ኃይለ ቃል ነው የሚያጽናናት !?


ዘሀበሻ