Get Mystery Box with random crypto!

ሁለት ዜናዎች 1፤ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ዛሬ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ታንዛኒያ መ | Muktarovich Ousmanova

ሁለት ዜናዎች

1፤

ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ዛሬ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ታንዛኒያ መግባታቸውን የመንግሥት ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ደመቀ ዛሬ በታንዛኒያ የወደብ ከተማ ዛንዚባር ከአገሪቷ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሳሉሁ ጋር በኹለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደተወያዩ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴርን ጠቅሰው ዘግበዋል።  ደመቀ ዛሬ ታንዛኒያ የገቡት፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ መንግሥታቸው ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር በታንዛኒያ አስተናጋጅነት ነገ ማክሰኞ የሰላም ድርድር እንደሚጀምር በገለጡ ማግስት ነው። ደመቀ ከታንዛኒያ ቀጥሎ በኮሞሮስ፣ ቡሩንዲ እና ኡጋንዳ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተገልጧል።

2፤

የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት ዛሬ ባዋለው ችሎት በ"ኡትዮ ንቃት" የዩትዩብ ጣቢያ ባለቤት መስከረም አበራ ላይ ተጨማሪ 10 የምርመራ ቀናት መፍቀዱን የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። መርማሪ ፖሊስ ባለፉት 13 ቀናት ከተጠርጣሪዋ እጅ ያዝኳቸው ባላቸው የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች ላይ ምርመራ እንዲደረግለት ለሚመለከተው አካል ልኮ የምርመራ ውጤቱን መቀበሉን፣ የተጠርጣሪዋን የገንዘብ ዝውውር ለማወቅ ለባንክ ደብዳቤ መጻፉን፣ ከመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን ማስረጃ ለማግኘት ጥያቄ ማቅረቡንና ሌሎች ቀሪ የምርመራ ሥራዎችን እያከናወነ መኾኑን ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። ፖሊስ መስከረምን ከሁለት ሳምንት በፊት በቁጥጥር ስር ያዋላት፣ "ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት" ወንጀል ጠርጥሬያታለሁ በማለት ነበር።
ዘገባው የዋዜማ ነው