Get Mystery Box with random crypto!

ማነው በፍጡራኑ ሁሉ፣ በቅጠላቅጠሉ ሁሉ፣ በነፍሳቱ ሁሉ ላይ የሚገራርሙ ዲዛይኖችን፣ የሚገራርሙ አለ | Muktarovich Ousmanova

ማነው በፍጡራኑ ሁሉ፣ በቅጠላቅጠሉ ሁሉ፣ በነፍሳቱ ሁሉ ላይ የሚገራርሙ ዲዛይኖችን፣ የሚገራርሙ አለሮችን experiment ያደረገው?

ማነው.. በቢሊየን የሚቆጠሩ የዚችን ዓለም ፍጥረታት.. ከደቃቋ ኢምንቷ ፍጥረት እስከ ግዙፋኑ ፍጡራን ድረስ.. ዲዛይናቸውን ቁጭ ብሎ ያለመታከት የነደፈው? ማነው ይሄ አስገራሚ ታላቅ አርቲስት?

ማነው የዚች ጉደኛ ዓለምና ሞላዋ አርኪቴክት? ማነው ይሄ ግራንድ ማስተር? እጅግ ይደንቀኛል! ተደምሜ አላበቃም!

በባህሩ፣ በአየሩ፣ በአፈሩ፣ በሠማይ በምድሩ ላይ በእንዴት ያለ ዲዛይን ስንቱን መዓት ፍጡር ነው በዲዛይኑ የተራቀቀበት? በስንቱ የአዕዋፍ ገላ ላይ? በስንቱ አበባ?..

በዳመናው በከዋክብቱ... ተቆጥረው በማያልቁ ቀለማቱ... በስንቱ ነገር ነው የተራቀቀው ይሄ አርቲስት? እጅግ.. እጅግ.. እጅግ ያስደንቀኛል!

ተደምሜ አላባራም...!
Via Assaf Hailu