Get Mystery Box with random crypto!

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ለአያክስ የሴቶች ቡድን ለመጫወት ፈረመች ሚያዝያ 16/2015 (ዋልታ) ኢትጵ | Muktarovich Ousmanova

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ለአያክስ የሴቶች ቡድን ለመጫወት ፈረመች

ሚያዝያ 16/2015 (ዋልታ) ኢትጵያዊቷ እግር ኳስ ተጫዋች ሊሊ ዮሃንስ ለአያክስ አምስተርዳም ክለብ ፕሮፌሽናል የሴቶች ቡድን ለመጫወት ፈረመች፡፡

ሊሊ የመጀመሪያውን ፕሮፌሽናል የተጫዋችነት ውል የፈረመችው ባለፈው ሐሙስ ሲሆን በስምምነቱ መሰረትም እ.ኤ.አ. ከሰኔ 30/2023 እስከ ሰኔ 30/2026 በአያክስ እንደምትቆይ ክለቡ በድረ-ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል፡፡

በአሜሪካ ስፕሪንግፊልድ በ2007 የተወለደችው ሊሊ ዮሃንስ ከባለፈው ዓመት የእግር ኳስ መርኃ ግብር መጀመሪያ ጀምሮ በአያክስ የሴቶች ታለንት ቡድን ውስጥ እየተጫወተች እንደምትገኝ መረጃው ያመለክታል፡፡

ሊሊ ለክለቡ 17 የሊግ ጨዋታዎችን አድርጋ አራት ግቦችን በማስቆጠር እና ስድስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ማቀበሏን መረጃው ጠቁሟል፡፡

ሊሊ በመጭው ዓመት የጨዋታ መርኃ ግብር መጀመሪያ ላይ ቡድኑን ትቀላቀላለችም ተብሏል::

ሊሊ ዮሐንስ በዜግነት አሜሪካዊ ስትሆን ለአሜሪካ ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን እንደምትጫወት ተመልክቷል፡፡